Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
“ነገን ዛሬ እንትከል” በሚለዉ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ውብ የተፈጥሮ ገጽታ ባላት የጌዲኦ ዞን ችግኝ በመትከል አሻራችንን አኑረናል። የጌዲኦ ህዝብና አባገዳዎች ላደረጋችሁልን ደማቅ አቀባበል እናመሰግናለን።
ከ141 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
**********
(ኢ ፕ ድ)

የጉምሩክ ኮሚሽን ከሰኔ 2 እስከ 8/ 2015 ባደረገው ክትትል 76 ሚሊዮን የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና ከ64 ሚሊዮን ብር በላይ የወጭ፤ በድምሩ 141 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር የላቀ አፈጻጸም የተመዘገበ ሲሆን በዚህም ጅግጅጋ ፣ ሞያሌ እና አዋሽ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በቅደም ተከተላቸው 21 ሚሊዮን፣ 18 ሚሊዮን እና 11 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በመያዝ ከፍተኛውን ድርሻ ወስደዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋዉሩ የተገኙ ስድስት ግለሰቦች እና አራት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
መንግሥት የቴሌኮም ዘርፉን ለግሉ ዘርፍ ክፍት ማድረጉ የዘርፉን እድገት ለማስቀጠል ይረዳል
- የቴሌኮም ዘርፍ አማካሪ ሚሼል ጉንታ
********
(ኢ ፕ ድ)

መንግሥት የቴሌኮም ዘርፉን ለግሉ ዘርፍ ክፍት ማድረጉ የዘርፉን እድገት ለማስቀጠልና የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር የቴሌኮም ዘርፍ አማካሪው ሚሼል ጉንታ ገለጹ።

አገራዊ ለውጡን ተከትሎ በመንግሥት ብቻ ሲቀርብ የነበረውን አገልግሎት ለዓለም አቀፍ አገልግሎት አቅራቢዎች ክፍት መደረጉ ይታወሳል።

በዚህም ነባሩ አገልግሎት ሰጪ ኢትዮ-ቴሌኮምን ጨምሮ ሁለት አዳዲስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲኖሩ አቅጣጫ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል።

ይህንንም ተከትሎ መንግሥት ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ቀጥሎ ሁለተኛውን አዲስ የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ ለመሥጠት ዝግጅት እያደረገ ነው።

ይህም የመንግሥት ውሳኔ የሚደነቅና ለዘርፉ እድገት በርካታ ጥቅሞች ይዞ እየመጣ መሆኑን ነው የዘርፉ አማካሪ ሚሼል ጉንታ ለኢዜአ የገለጹት።

ይህ ለኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ተሞክሮን በማጋራት አዳዲስ ቴክኖሎጂ በማስረጽ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን እድልና ተስፋ ከፍ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

ያም ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ ጥራት ያለው የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል በኩባንያዎች መካከል ውድድር እንዲዳብር ያስችላልም ነው ያሉት። ይህም ደግሞ የቴሌኮም ዘርፍ ተደራሽነትን ለማስፋት እንደሚያስችል በመጠቆም።

ኢትዮጵያ አሁን እያደረገች ያለው የዲጂታል ሥርዓት ግንባታና የቴሌኮም ዘርፍ እንቅስቃሴ በአፍሪካ ወደ ላቀ ደረጃ የሚወስዳት መሆኑንም እምነታቸውን ገልጸዋል።

እንዲያም ሆኖ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዲጂታል ሥርዓት ግንባታ ይበልጥ በማጠናከር የዘርፉን እድገት ማስቀጠል እንደሚገባ ምከረ ኃሳብ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ቀጥሎ ሁለተኛውን አዲስ የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ ለመስጠት በያዝነው ሰኔ ወር ጨረታ እንደሚወጣ መግለጹ ይታወሳል።
አዲሱ”ዓባይ ፪” መርከብ በነዳጅ ጫኝ መርከቦቻችን ሲደርስብን የነበረውን ኪሳራ ማስቀረት ያስቻለ ነው
***
(ኢ.ፕ.ድ)

👉 በቀን 11 ሺህ ዶላር ገቢ ያስገኛል

አዲሱ “ዓባይ ፪” መርከብ በሁለቱ ነዳጅ ጫኝ መርከቦቹ ሲደርስ የነበረውን ኪሳራ ማስቀረት እንደሚያስችል የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አስታወቀ፡፡

በቀን አስራ አንድ ሺህ ዶላር የተጣራ ትርፍ ገቢ የሚያስገኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምሰው በንቲ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አዲሱ”ዓባይ ፪” ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ

https://press.et/?p=102814
በሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ዙሪያ እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ ውይይት በሐምሌ ወር ይጠናቀቃል
***********
(ኢ.ፕ.ድ)

👉ውይይቱ በሁሉም ክልሎች ይካሄዳል

👉መስከረም ላይ ያለቀለት የፖሊሲ ሰነድ ለሕዝብ ይቀርባል

በሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ዙሪያ እየተካሄደ ያለው ግብዓትን የማሰባሰብ ሃገራዊ ውይይት እስከ መጪው ሐምሌ ወር 2015ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ውይይቱ በሁሉም ክልሎች እንደሚካሄድና መስከረም ወር ላይ ያለቀለት የፖሊሲ ሰነድ ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን ተገልጿል::

በፍትህ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አወል ሱልጣን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን ለማውጣት...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102817