በትግራይ የሚገኙት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችላቸው ቁመና ላይ ደርሰዋል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በትግራይ ክልል የሚገኙት አራቱ ዩኒቨርሲቲዎች በአሁኑ ወቅት ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችላቸው ቁመና ላይ መድረሳቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የአስተዳደርና መሰረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሰለሞን አብርሃ ከኢፕድ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፤ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወደ ሥራ መግባታቸው አንዱ ለሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=102976

የወል እውነታዎች ላይ በማተኮር ሀገርን ማጽናት እንደሚገባ አፈ-ጉባኤ ታገሠ ጫፎ ገለፁ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)
የወል እውነታዎች ላይ በማተኮር ሀገርን ማጽናት እንደሚገባ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ ገለፁ፡፡
አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ ይህን የተናገሩት ‹‹መፍጠንና መፍጠር፤ የወል ዕውነቶችን የማጽናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ›› በሚል ርዕስ ለምክር ቤት አባላት፣ ለሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤቶች አመራሮችና በለሙያዎች ለሦስት ቀናት ሲሰጥ በነበረው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ማጠቃለያ ላይ ነው፡፡
በዚሁ በተዘጋጀው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰነድ ላይ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አካላት ማለትም ሥራ አስፈጻሚ፣ የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች እና በየክልሉ የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮችም መሰልጠናቸውንና በቀጣይም ስልጠናው እሰከ ባለሙያዎች የሚወርድ መሆኑን ነው አፈ-ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የጠቆሙት፡፡
የስልጠናው ዓላማም ሀገሪቱ ባለፉት አምስት ዓመታት ባጋጠሟት ፈተናዎች በሀገሪቱ ግጭቶች፣ አለመግባባቶች እና ጥርጣሬዎች መፈጠራቸውን ጠቁመው፤ ለነዚህ ሁሉ ችግሮች መነሻ የወል እውነታዎች ላይ ከማትኮርና የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከመግባባት ይልቅ የተናጠል እውነቶች ላይ በመንጠልጠል የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መግባባት ባለመቻላችን እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ስለሆነም በማያግባቡ ጉዳዮች ላይ በሰከነ መንፈስ በመነጋገር፣ በመመካከር፣ በመተራረም እና የወል የሆነ ዕውነታን በማፅናት ሀገርን ከጋጠማት ችግር ማሻገር ይገባል ብለዋል፡፡
አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሠ አያይዘውም፤ መንግስት አሁን ላይ በሀገሪቱ የሚታዩትን የሠላምና ጸጥታ፣ የኑሮ ውድነት፣ ሙስናን ጨምሮ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ይሰራል ብለዋል።
በአንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩ በተናጠል የሚቀርቡ እውነታዎች የሚፈጥሯቸው የፅንፈኝነት አዝማሚያዎችንም መልክ ማስያዝ ይገባልም ነው ያሉት፡፡
ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ሰነዱ ሀገሪቱ የገጠሟትን ፈተናዎች በትክክል ያስቀመጠና እነዚህን ችግሮች በፍጥነትና በተገቢው ሥራ እንዴት መፍታት እንዳለብን የሚያሳይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ወ/ሮ ሎሚ በዶ አክለውም በቀረበው መረጃ መሠረት በሰነዱ ላይም ከመቼውም ጊዜ የተሻለ መግባባት ላይ የተደረሰበት መሆኑን አንስተው፤ ሰነዱ ወቅቱ የሚጠይቀውን አመራርና ባለሙያ ለማፍራትም ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም ነው ያስረዱት፡፡
የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በበኩላቸው የሥልጠና መድረኩ ዋነኛ ዓላማ በሰነዱ ላይ የተቀመጡ ሐሳቦችን በማስገንዘብና በማሳወቅ የሀገረ-መንግሥት ግንባታና ጠንካራ የፓርቲ ሥርዓት በመፍጠርና አቅምን በመገንባት፣ የጋራ ፖለቲካዊ ዕሳቤዎችን መነሻ በማድረግ የወል ዕውነቶችን ማጽናት፣ መግባባት እና ለቀጣይ ሥራ መነሳሳት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ስለሆነም በግልና በቡድን ዕውነታ ላይ ከማተኮር ይልቅ የወል ዕውነታን በማጽናት በወቅቱ የሚታዩትን ቀውሶች፣ ግጭቶች፣ እና የተለያዩ ችግሮችን ለሕዝብ በተገባው ቃል መሠረት ከምርጫ በፊት የወል እውነቶችን ለማጽናት በጋራ ዕይታ በመፍጠርና በመፍጠን መፍታት የሚገባ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ለቀናት ሥልጠናውን ሲወስዱ የነበሩት የምክር ቤት አባላት እንዲሁም የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጽሕፈት ቤት አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች በቀረበው ሰነድ ላይ ጥልቅ ውይይት አድርገዋል።
በቀረበው የሥልጠናው ገለጻ ላይ ዓለማቀፋዊ፣ አህጉራዊ፣ ቀጠናዊ እና ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን በደንብ የተነተነ፣ በሀገሪቱ የተከናወኑ መልካም ሥራዎችን እና ችግሮችን ከነቀጣይ መፍትሔዎቻቸው በአግባቡ ያስቀመጠ እና ጥልቅ ግንዛቤን የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።
ስልጠናው በሌላ አጀንዳ ላይም የሚቀጥል ይሆናል ሲል ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን በኢኮኖሚ የማስተሳሰር ጠንካራ ስራ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ
******
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን በኢኮኖሚ የማስተሳሰር ጠንካራ ስራ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ።
አለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር ትኩረቱን በአፍሪካ ያደረገ ጉባኤ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው።
የትራንስፓርት ሚኒስቴር የሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ድኤታ አቶ ደንጌ ቦሩ በጉባኤው ላይ እንደገለጹት፤ ትራንስፖርት በአፍሪካ እያደገ መጥቷል። ጠንካራ ፖሊሲ አለመኖር፣ የሰለጠነ የሰው ሃይል እጥረትና የመሰረተ ልማት አለመዘመን የአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ዘርፉን እየጐዳው ነው። ዘርፉን ለማዘመን በጋራ መስራት ያስፈልጋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን በኢኮኖሚ የማገናኘትና የማስተሳሰር ጠንካራ ስራ እየሰራ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፣ እንዲሁም የአፍሪካ አህጉር ከተቀረው አለም ጋር የማስተሳሰር ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የዘርፉን መሰረተ ልማት በማሟላት የኢኮኖሚ ትስስርን ይበልጥ ለማጠናከር በጋራ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።
የአየር ትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን የኢትዮጵያ መንግስት ቁርጠኛ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ የፖሊስ ማሻሻያዎች እየተወሰዱ መሆኑንና የአፍሪካ ሀገራትን በአየር ትራንስፖርት ማገናኘት የሚለውን የአፍሪካ ራእይ ለመተግበር የኢትዮጵያ መንግስት በትጋት እየሰራ መሆኑን
ጠቅሰዋል።
የአለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊሊ ዋልሽ በበኩላቸው፣ አፍሪካ ከአየር መንገድ ኢንደስትሪው ከፍተኛ ጥቅም ማግኘት በሚያስችላት መንገድ መስራት አለባት ብለዋል።
በዘርፉ የሚስተዋለውን የመሰረተ ልማት ችግር መቅረፍና የሰለጠነ የሰው ሃይልን መጠቀም እንደሚገባም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለበርካታ ሰዎች የስራ እድል የፈጠረና በየአመቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገባ መሆኑንም ገልጸዋል።
በኮንፈረንሱ ላይ የበርካታ ሀገራት የአየር መንገድ ስራ አስፈጻሚዎች ተገኝተዋል።
በሞገስ ጸጋዬ