የወል እውነታዎች ላይ በማተኮር ሀገርን ማጽናት እንደሚገባ አፈ-ጉባኤ ታገሠ ጫፎ ገለፁ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)
የወል እውነታዎች ላይ በማተኮር ሀገርን ማጽናት እንደሚገባ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ ገለፁ፡፡
አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ ይህን የተናገሩት ‹‹መፍጠንና መፍጠር፤ የወል ዕውነቶችን የማጽናት ቀጣይ የትግል ምዕራፍ›› በሚል ርዕስ ለምክር ቤት አባላት፣ ለሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤቶች አመራሮችና በለሙያዎች ለሦስት ቀናት ሲሰጥ በነበረው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ማጠቃለያ ላይ ነው፡፡
በዚሁ በተዘጋጀው የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰነድ ላይ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አካላት ማለትም ሥራ አስፈጻሚ፣ የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች እና በየክልሉ የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮችም መሰልጠናቸውንና በቀጣይም ስልጠናው እሰከ ባለሙያዎች የሚወርድ መሆኑን ነው አፈ-ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የጠቆሙት፡፡
የስልጠናው ዓላማም ሀገሪቱ ባለፉት አምስት ዓመታት ባጋጠሟት ፈተናዎች በሀገሪቱ ግጭቶች፣ አለመግባባቶች እና ጥርጣሬዎች መፈጠራቸውን ጠቁመው፤ ለነዚህ ሁሉ ችግሮች መነሻ የወል እውነታዎች ላይ ከማትኮርና የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከመግባባት ይልቅ የተናጠል እውነቶች ላይ በመንጠልጠል የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መግባባት ባለመቻላችን እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ስለሆነም በማያግባቡ ጉዳዮች ላይ በሰከነ መንፈስ በመነጋገር፣ በመመካከር፣ በመተራረም እና የወል የሆነ ዕውነታን በማፅናት ሀገርን ከጋጠማት ችግር ማሻገር ይገባል ብለዋል፡፡
አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሠ አያይዘውም፤ መንግስት አሁን ላይ በሀገሪቱ የሚታዩትን የሠላምና ጸጥታ፣ የኑሮ ውድነት፣ ሙስናን ጨምሮ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ይሰራል ብለዋል።
በአንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩ በተናጠል የሚቀርቡ እውነታዎች የሚፈጥሯቸው የፅንፈኝነት አዝማሚያዎችንም መልክ ማስያዝ ይገባልም ነው ያሉት፡፡
ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ሰነዱ ሀገሪቱ የገጠሟትን ፈተናዎች በትክክል ያስቀመጠና እነዚህን ችግሮች በፍጥነትና በተገቢው ሥራ እንዴት መፍታት እንዳለብን የሚያሳይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ወ/ሮ ሎሚ በዶ አክለውም በቀረበው መረጃ መሠረት በሰነዱ ላይም ከመቼውም ጊዜ የተሻለ መግባባት ላይ የተደረሰበት መሆኑን አንስተው፤ ሰነዱ ወቅቱ የሚጠይቀውን አመራርና ባለሙያ ለማፍራትም ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም ነው ያስረዱት፡፡
የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በበኩላቸው የሥልጠና መድረኩ ዋነኛ ዓላማ በሰነዱ ላይ የተቀመጡ ሐሳቦችን በማስገንዘብና በማሳወቅ የሀገረ-መንግሥት ግንባታና ጠንካራ የፓርቲ ሥርዓት በመፍጠርና አቅምን በመገንባት፣ የጋራ ፖለቲካዊ ዕሳቤዎችን መነሻ በማድረግ የወል ዕውነቶችን ማጽናት፣ መግባባት እና ለቀጣይ ሥራ መነሳሳት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ስለሆነም በግልና በቡድን ዕውነታ ላይ ከማተኮር ይልቅ የወል ዕውነታን በማጽናት በወቅቱ የሚታዩትን ቀውሶች፣ ግጭቶች፣ እና የተለያዩ ችግሮችን ለሕዝብ በተገባው ቃል መሠረት ከምርጫ በፊት የወል እውነቶችን ለማጽናት በጋራ ዕይታ በመፍጠርና በመፍጠን መፍታት የሚገባ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ለቀናት ሥልጠናውን ሲወስዱ የነበሩት የምክር ቤት አባላት እንዲሁም የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጽሕፈት ቤት አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች በቀረበው ሰነድ ላይ ጥልቅ ውይይት አድርገዋል።
በቀረበው የሥልጠናው ገለጻ ላይ ዓለማቀፋዊ፣ አህጉራዊ፣ ቀጠናዊ እና ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን በደንብ የተነተነ፣ በሀገሪቱ የተከናወኑ መልካም ሥራዎችን እና ችግሮችን ከነቀጣይ መፍትሔዎቻቸው በአግባቡ ያስቀመጠ እና ጥልቅ ግንዛቤን የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።
ስልጠናው በሌላ አጀንዳ ላይም የሚቀጥል ይሆናል ሲል ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን በኢኮኖሚ የማስተሳሰር ጠንካራ ስራ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ
******
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን በኢኮኖሚ የማስተሳሰር ጠንካራ ስራ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ።
አለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር ትኩረቱን በአፍሪካ ያደረገ ጉባኤ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው።
የትራንስፓርት ሚኒስቴር የሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ድኤታ አቶ ደንጌ ቦሩ በጉባኤው ላይ እንደገለጹት፤ ትራንስፖርት በአፍሪካ እያደገ መጥቷል። ጠንካራ ፖሊሲ አለመኖር፣ የሰለጠነ የሰው ሃይል እጥረትና የመሰረተ ልማት አለመዘመን የአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ዘርፉን እየጐዳው ነው። ዘርፉን ለማዘመን በጋራ መስራት ያስፈልጋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን በኢኮኖሚ የማገናኘትና የማስተሳሰር ጠንካራ ስራ እየሰራ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፣ እንዲሁም የአፍሪካ አህጉር ከተቀረው አለም ጋር የማስተሳሰር ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የዘርፉን መሰረተ ልማት በማሟላት የኢኮኖሚ ትስስርን ይበልጥ ለማጠናከር በጋራ መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።
የአየር ትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን የኢትዮጵያ መንግስት ቁርጠኛ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ የፖሊስ ማሻሻያዎች እየተወሰዱ መሆኑንና የአፍሪካ ሀገራትን በአየር ትራንስፖርት ማገናኘት የሚለውን የአፍሪካ ራእይ ለመተግበር የኢትዮጵያ መንግስት በትጋት እየሰራ መሆኑን
ጠቅሰዋል።
የአለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊሊ ዋልሽ በበኩላቸው፣ አፍሪካ ከአየር መንገድ ኢንደስትሪው ከፍተኛ ጥቅም ማግኘት በሚያስችላት መንገድ መስራት አለባት ብለዋል።
በዘርፉ የሚስተዋለውን የመሰረተ ልማት ችግር መቅረፍና የሰለጠነ የሰው ሃይልን መጠቀም እንደሚገባም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለበርካታ ሰዎች የስራ እድል የፈጠረና በየአመቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገባ መሆኑንም ገልጸዋል።
በኮንፈረንሱ ላይ የበርካታ ሀገራት የአየር መንገድ ስራ አስፈጻሚዎች ተገኝተዋል።
በሞገስ ጸጋዬ

የመዝናኛውን ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር ኢቢሲ ልዩ ሥራ እና አሰራር ይዞ መምጣቱ ተገለጸ
*******************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከተለያዩ አንጋፋና ወጣት የሀገራችን የጥበብ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ያዘጋጃቸውን የቴሌቪዥን ድራማዎች ትናንት በሸራተን አዲስ ሆቴል በደማቅ ሥነ ስርዓት አስመርቋል።
ድራማዎቹ በተለያየ ዘውግ የተሰሩ ሲሆን ከቀናት በኋላ ማለትም ከሰኔ 18/2015 ዓ.ም ጀምሮ በየሳምንቱ ለህዝብ መቅረብ ይጀምራሉ።
የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍሰሃ ይታገሱ በምርቃ ሥነስርዓቱ ባደረጉት ንግግር ኮርፖሬሽኑ በአሁኑ ወቅት የአድማጭ ተመልካች ፍላጎትን ለማርካት እና የተጣለበትን ማህበራዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ከፍተኛና ሁለንተናዊ ተቋማዊ የሪፎርም ስራዎች በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አድማጭ ተመልካቹ የተሻለ አማራጭ እና ተመራጭ የሚዲያ ይዘት እንዲያገኝ ተቋሙ በተለያዩ ቻናሎቹ ከፍተኛ የለውጥ ሥራዎች እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።በመዝናኛው ዘርፍ ቀዳሚና ግንባር ቀደም የሀገሪቱ ሚዲያ ሆኖ እንዲቀጥል አዳዲስ የፕሮግራም እና የድራማ ይዘቶችን በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በውስጥ አቅም ከሚሰሩ በርካታ ፕሮግራሞች በተጨማሪ በሀገራችን ያሉ ዕንቁ የጥበብ ባለሙያዎችን በማስተባበርና በማሳተፍ የመዝናኛ ኢንዱስትሪውን የላቀ ደረጃ በማድረስ በሀገሪቱ ሁለንተናዊ ለውጥ ውስጥ ኢቢሲ ልዩ ሚና እንደሚወጣ አቶ ፍሰሃ ገልጸዋል።
የኢቲቪ መዝናኛ ቻናል ማኔጂንግ ኤዲተር አቶ ዘካርያስ ብርሃኑ ተመርቀው በየሳምንቱ መታየት የሚጀምሩት ስድስት ድራማዎች ከፍተኛ ልምድና ዝና ያላቸው የሀገራችን የጥበብ ባለሙያዎች እንደተሳተፉበት ገልጸው፤ በይዘትና አቀራረብ ተመልካች እንዲወዳቸውና መርጦ እንዲመለከታቸው ከፍተኛ ጥንቃቄና ጊዜ ተወስዶ ዝግጅት የተደረገባቸው መሆኑን ተናግረዋል።
ትናንት የደመቀ የመክፈቻና የማስመረቂያ ሥነስርዓት የተካሄደላቸው የኢቢሲ አዳዲስ ድራማዎች እና ሳምንታዊ የመተላለፊያ ቀንና ሰዓታቸው የሚከተለው ነው።
"ግራ ቀኝ"... እሁድ ቀን 8 ሰዓት በዜና ቻናል እንዲሁም ማታ 2 ሰዓት በመዝናኛ ቻናል
"በመሐል"...ሰኞ ማታ 2:20 በመዝናኛ ቻናል
"እቴጌ"...በሳምንት ሁለት ጊዜ ረቡዕ እና አርብ ማታ 2:20 በመዝናኛ ቻናል
"ደርዳሬ"(ኮሜድያን ደረጄ ሐይሌ)...እሁድ ቀን 9:30 በመዝናኛ ቻናል
"ሲምቦ"...አርብ ማታ 3:20 በአፋን ኦሮሞ ቻናል
"ሒርኮ"...እሁድ ከሰዓት በኋላ በአፋን ኦሮሞ ቻናል በዳንጋ የመዝናኛ ፕሮግራም እንደሚቀርቡ ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በወላይታ ዞን ድጋሚ የተካሄደው የህዝበ ውሳኔ የመጨረሻ ውጤት ሰኔ 19 ቀን 2015 ይፋ እንደሚደረግ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ
******
(ኢ.ፕ.ድ)
በወላይታ ዞን ድጋሚ በትናንትናው እለት ድጋሜ የተካሄደው የህዝበ ውሳኔ የመጨረሻ ውጤት ሰኔ 19 ቀን 2015 ይፋ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በወላይታ ዞን በድጋሚ የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ህዝበ ውሳኔው በተደረገው ቅድመ ዝግጅት መሰረት በሰላም መጠናቀቁንም ነው ሰብሳቢዋ የገለጹት።
በህዝበ ውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላጋጠሙ መጠነኛ ችግሮች ተገቢ መፍትሄ በመስጠት መራጮች መብታቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ መደረጉን ሰብሳቢዋ ትላንት ምሽት በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል።
የህዝበ ውሳኔው የመጨረሻ ውጤት በተያዘው እቅድ መሰረት ሰኔ 19 ቀን 2015 ይፋ እንደሚደረግ የገለጹት ሰብሳቢዋ ከተቻለም አስቀድሞ ለመግለጽ ቦርዱና ሰራተኞቹ በትጋት እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።
ሰብሳቢዋ በመግለጫቸው እንዳሉት በዞኑ በድጋሚ የተካሄደው ህዝበ ውሳኔ የተሳካ እንዲሆን ቦርዱ በሰው ሀይልና በሎጂስቲክስ በቂ ዝግጅት በማድረግ ወደ ተግባር ገብቷል።
የህዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባና የድምጽ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት በተመሳሳይ ሰዓት የሚካሄድ በሆኑ ለስኬቱ የምርጫ ማዕከላትና ጣቢያዎችን የማስፋት ስራ መከናወኑን ተናግረዋል።
በዚሁ መሰረት ከዚህ ቀደም ከነበረው የምርጫ ማእከላትን ከስምስት ወደ 12 እንዲሁም 1 ሺህ 112 የነበሩትን ምርጫ ጣቢያዎች ወደ 1 ሺህ 812 በማሳደግ ሂደቱ መከናወኑን ጠቅሰዋል።
"9 ሺህ 60 የምርጫ አስፈጻሚዎች ተመልምለውና በቂ ስልጠና ተሰጥቷቸው ሂደቱን አስፈጽመዋል" ብለዋል።
የድምጽ አሰጣጡ መደበኛ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኃላ መብታቸውን መጠቀም የሚገባቸው መራጮች ሰልፍ ላይ ስለነበሩ በህጉ መሰረት ለአንድ ተጨማሪ ሰዓት በማራዘም መከናወኑን ተናግረዋል።
ሰብሳቢዋ አክለውም የምርጫው ሂደት ተአማኒና ዴሞክራሲያዊ መሆኑን የሚታዘቡ ከሀገር ውስጥ ሁለት ተቋማት ከቦርዱ ዕውቅና ተሰጥቷቸው 168 ታዛቢዎችን አሰማርተው ሂደቱን መታዘባቸውን ገልጸዋል።
በዕለቱ የመራጮች ምዝገባና የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በተመሳሳይ ሰዓት መከናወኑን ያነሱት ሰብሳቢዋ በዚህም ቦርዱ ተግባሩን በሚያከናውንበት ጊዜ ያጋጠሙ ችግሮች እንደነበሩ አንስተዋል።
ከችግሮቹ መካከልም በብዙ ጣቢያዎች በአካባቢው ስድስት ወር መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የህግ ቅድመ ሁኔታ የማያሟላና ህጋዊ መታወቂያ ሳይኖራቸው ድምፅ ለመስጠት የመጡ መገኘታቸውን ጠቅሰዋል።
በቦርዱ ህግና መመሪያ መሰረት የመራጮች የመምረጥ መብታቸው እንዲጠበቅ በማሰብ ነዋሪነታቸውን በሶስት ምስክርና በሌሎች ሰነዶች በማረጋገጥ መፍትሄ በመስጠት እንዲሳተፉ መደረጉን ተናግረዋል።
እንዲሁም በተወሰኑ ምርጫ ጣቢያዎች ከ18 ዓመት በታች የሆኑ መራጮች መገኘታቸው ሌላው ችግር እንደነበር አንስተው "ግለሰቦቹ ህጉ ስለማይፈቅድላቸው እንዳይሳተፉ ተደርጓል" ብለዋል።
በተጨማሪም በሶዶ ዙሪያ በሚገኝ ድልቦ አውጥሮ 1 ምርጫ ጣቢያ ላይ ድምፅ ለመስጠት የመጣ አስፈጻሚ ባዶ መታወቂያ እየሞላ ሲያድል እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ መጀመሩን ተናግረዋል።
"በሁምቦ ምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚ ሳይሆን ነኝ በሚል ባጅ አንጠልጥሎ ለመግባት የሞከረ ግለሰብ መያዙንና እንዲሁም በገሱባ 01 ምርጫ ጣቢያ አምስት ስርዝ ድልዝ ያለበት የነዋሪነት መታወቂያ ይዘው የተገኙ ግለሰቦች እንዲመለሱ ተደርጓል" ብለዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ ከፍተኛ የሆነ ጥሰት ሳይገኝ የህዝበ ውሳኔ ድምጽ አሰጣጥ ሂደት በሰላማዊ ሁኔታ ተከናውኖ መጠናቀቁን ሰብሳቢዋ አስታውቀዋል።