ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ በንግድና ኢንቨስትመንት ዙርያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ከዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ሚኒስትር አቶ ናይጄል ሆድልስተን ጋር በመወያየት በንግድና ኢንቨስትመንት ዙርያ አብሮ ለመስራት የሚስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ስምምነቱ በዋናነት ኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እያደረገች ያለውን ሁሉን አቀፍ ዝግጅት በፋይናስና በቴክኒክ ለማገዝ የሚረዳ ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ እስካሁን የአለም አቀፉ የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ረጅም ጉዞ መጓዟን ያነሱት ሚኒስትሩ ይህን ብቻውን ግብ ባለመሆኑ አለም አቀፍ ኢንቨስትመንትን በማሳደግ ተወዳዳሪ ሆኖ መገኝት ይገባል ብለዋል፡፡
የዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ሚኒስትር አቶ ናይጄል ሆድልስተን በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ጋር ረጅም አመታትን ያስቆጠረ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰው፤ ኢትዮጵያ እንደ ሰፊ የሰው ሀብትና የቆዳ ስፋት ባለቤትነቷ ከአፍሪካ ትልቁን ኢኮኖሚ ይዛ እስካሁን በአለም የንግድ ድርጅ ውስጥ አባል ለመሆን መዘግየቷ ተገቢ ባለመሆኑ ይህንን ለማሻል በዩናይትድ ኪንግደም በኩል ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው ይበልጥ ተጠቃሚ እድትሆን ለማድረግና የንግድ ሚዛኑን ለማሻሻል በሚቻልበቻው ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በጋራ ለመስራትና ለመደገፍ የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም መናገራቸውንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት አስራ አንድ ወራት ከሶስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
ባለፉት አስራ አንድ ወራት ከ ሶስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን አስታወቀ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን በ2015 በጀት ዓመት አስራ አንድ ወራት ሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰበሰብ አቅዶ ባከናወናቸው ስራዎች ከሶስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መለሰ ኪዊ ገልፀዋል።
ባለስልጣን መ/ቤቱ ከቀጥተኛ ታክስ ሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን፣ ቀጥተኛ ካልሆኑ የታክስ አይነቶች 726 ሚሊዮን፣ ታክስ ካልሆኑ 161 ሚሊዮን እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ 170 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡንም አቶ መለሰ አስታውቀዋል።
የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ942 ሚሊዮን ብር ብልጫ እንዳለውም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ለተመዘገበው የአፈጻጸም መሻሻል አስተዋጽዖ ያበረከቱ በየደረጃው የሚገኙ ግብር ከፋዮችን እንድሁም ግብር ሰብሳቢ ተቋማትና ባለሙያዎችን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መለሰ ኪዊ አመስግነዋል።
በቀጣዩ የ2016 በጀት ዓመት የተሻለ ገቢ ለመሰበሰብ ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ያለደረሰኝ የሚከናወኑ ክፍያዎችንና በዘርፉ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ለማስወገድ ባለስጣን መ/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።
የግብር አሰባሰብ ሂደቱን ዘመናዊ ለማድረግ ቴሌብርን እና ሌሎች የዲጅታል አገልግሎቶችን ለማስፋፋት እንሰራለን ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ማስታወቃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ከእነተሽከርካሪዎቹ መያዛቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለፀ።
የተለያዩ አልባሳት ቦንዳ፣ ሺሻ ማስጨሻ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ዓይነት ሲጋራዎች እና ህገ-ወጥ መድሀኒቶችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች መነሻቸውን ከጂቡቲ አድርገው አዲስ አበባ ከተማ ሊገቡ ሲሉ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከኅብረተሰቡ የደረሳቸውን ጥቆማ መሠረት በማድረግ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በጋራ ባደረጉት ጠንካራ ፍተሻ የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ ከነ-ተሽከርካሪዎቹ መያዛቸው ታውቋል።
በወንጀሉ የተሳተፋ ሁለት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሆነ ተገልጿል።
የተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን በደረሰኝ ገቢ መደረጋቸው ተጠቅሷል።
የፀጥታ ተቋማቱ በኮንትሮባንድ ላይ እያደረጉ ያሉትን የተቀናጀ ኦፕሬሽንና ክትትል አጠናክረው መቀጠላቸውን እየገለጹ ኅብረተሰቡ እስከአሁን ላደረገው ትብብር ምስጋና አቅርበው የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመግታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ የበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️
ሀገር አቀፍ የጤና ዐውደ ርእይ" ዛሬ በሳይንስ ሙዚየም አስጀምረናል። በዐውደ ርእዩ የመንግሥት እና የግል ተቋማት ፣ በጤና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሠማሩ ድርጅቶች እንዲሁም የምርምር ተቋማት ይሳተፋሉ።

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከ ዩኒዶ ተወካይ ጋር ተወያዩ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በዛሬው ዕለት ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት(ዩኒዶ) ተወካይ ኦሬሊያ ካላብሮን ጋር ተወያይተዋል፡፡
የሁለቱ ወገኖች ውይይት በኢትዮጵያ እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) መካከል ያለውን አጋርነት ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መሆኑ ታውቋል።
አምባሳደር ምስጋኑ በዚህ ወቅት ፥ ኢትዮጵያ ከዩኒዶ ጋር በአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪዎች፣ በጨርቃ ጨርቅ፣ በቆዳና ቆዳ ውጤቶችና በፋርማሲዩቲካል ምርቶች ላይ አጋርነቷን ለማሳደግ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
ተወካይ ኃላፊዋ ኦሬሊያ ካላብሮን በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ ያለውን የማሻሻያ እርምጃዎች አድንቀዋል፡፡
በተጨማሪም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ ለማከናወን ስላቀዳቸው ተግባራት ተወያይተዋል።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሀገር አቀፍ የጤና ዐውደ ርእይ መክፈቻ ላይ ያደረጉት ንግግር።
በዘንድሮው ክረምት ሁለት ሚሊዮን በጎ ፍቃደኞች ይሳተፋሉ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ ለአምስት ወራት በሚቆየው በዘንድሮው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር ሁለት ሚሊዮን በጎ ፍቃደኞች እንደሚሳተፉና በዚህም ከመንግሥት ወጪ ይደረግ የነበረ ሶስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር እንደሚድን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ አደራጎት ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ አደራጎት ማስተባበሪያ ኮሚሽን የበጎ ፍቃድ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=103055

"በመንገዱ መጓተት ምክንያት ለእንግልት ተዳርገናል”
የጎንደር አዘዞ ነዋሪዎች
"ግንባታው የዘገየው በኮንትራክተሩ የአፈጻጸም ማነስ ነው”
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
በጎንደር አዘዞ መንገድ ሥራ መጓተት ምክንያት ተጉላልተናል ሲሉ የአዘዞ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ፅህፈት ቤት በበኩሉ መንገዱን የሚሰራው ኮንትራክተር የአፈፃፀም ማነስ ነው ብሏል።
የጎንደር አዘዞ ነዋሪው ሙሉቀን አካልነህ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ መንገዱ ለዓመታት ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=103048
(ፎቶ ፋይል)