Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️

የዕለት ከዕለት ጥረት በተገቢው መንገድ ካልተደረገ ዘላቂ ሰላምን ማስፈን አይቻልም። እንደ አረንጓዴ ዐሻራችን ካሉ የልማት ሥራዎች ጎን ለጎን የጋራ ሰላማችንን ለማጎልበት የበለጠ ተባብረን መሥራት ይኖርብናል።
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ባንክ ስራን በይፋ አሰጀመሩ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ባንክ ስራን በይፋ በዛሬው ዕለት አሰጀምረዋል።
በመረሐግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ፣ የክልሉ አፈጉባኤ ፣የባንኩ ስራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ሀጢያ ፣ የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብርሀም ማርሻሎ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ባንክ በይፈ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አብስረው፤ ባንኩ ክልሉ እየሄደበት ያለውን ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚያጠናክር ነው ብለዋል።

የክልሉ አስተዳደር ከባንኩ ጋር በጋራ በመስራት ለስራ ፈጣሪዎች የብድር አገልግሎት በመስጠት ብሎም ተደራሽነትን የማረጋገጥ ስራ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደሰታ እንደተናገሩት የሲዳማ ባንክ በአጭር ጊዜ ለስኬት የበቃ ባንክ ነው። ሀገሪቱ የጀመረችውን ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲሁም ዘመናዊ የባንክ ተጀራሽነትን በስፋት ለማቅረብ ትልቅ ሚና ይኖረዋል። የብሄራዊ ባንክ ድጋፍ እንደማይለይም አስታውቀዋል ።

የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ሀጢያ በበኩላቸው ባንኩ ብሄራዊ ባንክ ያስቀመጠውን መስፈርት በአጭር ጊዜ ውስጥ በማሟላት የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል።

ባንኩ ከነበረበት ከሲዳማ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን በተፈረመና ከአንድ ቢሊዮን በላይ ካፒታል የተቋቋመ መሆኑን ገልፀዋል።

ባንኩ ከ500 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የብድር አገልግሎት በመስጠት ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑን ገልፀው፤ በቀጣይ ተደራሽና ዘመናዊ አገልግሎቶችን በማስፈት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ባንኩ እሴት በሚጨምሩና ሀገራዊ ኢኮኖሚ ፋይዳ ባላቸው ወጪ ምርቶችና አገልግሎቶች ላይ ትኩረትአድርጎ እንደሚሰራ ተናግርዋል።
በማህሌት ብዙነህ(ሀዋሳ )