የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️
የዕለት ከዕለት ጥረት በተገቢው መንገድ ካልተደረገ ዘላቂ ሰላምን ማስፈን አይቻልም። እንደ አረንጓዴ ዐሻራችን ካሉ የልማት ሥራዎች ጎን ለጎን የጋራ ሰላማችንን ለማጎልበት የበለጠ ተባብረን መሥራት ይኖርብናል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ባንክ ስራን በይፋ አሰጀመሩ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ባንክ ስራን በይፋ በዛሬው ዕለት አሰጀምረዋል።
በመረሐግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ፣ የክልሉ አፈጉባኤ ፣የባንኩ ስራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ሀጢያ ፣ የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብርሀም ማርሻሎ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ባንክ በይፈ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አብስረው፤ ባንኩ ክልሉ እየሄደበት ያለውን ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚያጠናክር ነው ብለዋል።
የክልሉ አስተዳደር ከባንኩ ጋር በጋራ በመስራት ለስራ ፈጣሪዎች የብድር አገልግሎት በመስጠት ብሎም ተደራሽነትን የማረጋገጥ ስራ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደሰታ እንደተናገሩት የሲዳማ ባንክ በአጭር ጊዜ ለስኬት የበቃ ባንክ ነው። ሀገሪቱ የጀመረችውን ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲሁም ዘመናዊ የባንክ ተጀራሽነትን በስፋት ለማቅረብ ትልቅ ሚና ይኖረዋል። የብሄራዊ ባንክ ድጋፍ እንደማይለይም አስታውቀዋል ።
የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ሀጢያ በበኩላቸው ባንኩ ብሄራዊ ባንክ ያስቀመጠውን መስፈርት በአጭር ጊዜ ውስጥ በማሟላት የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል።
ባንኩ ከነበረበት ከሲዳማ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን በተፈረመና ከአንድ ቢሊዮን በላይ ካፒታል የተቋቋመ መሆኑን ገልፀዋል።
ባንኩ ከ500 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የብድር አገልግሎት በመስጠት ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑን ገልፀው፤ በቀጣይ ተደራሽና ዘመናዊ አገልግሎቶችን በማስፈት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ባንኩ እሴት በሚጨምሩና ሀገራዊ ኢኮኖሚ ፋይዳ ባላቸው ወጪ ምርቶችና አገልግሎቶች ላይ ትኩረትአድርጎ እንደሚሰራ ተናግርዋል።
በማህሌት ብዙነህ(ሀዋሳ )

ከ90 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የሐዋሳ ከተማ መግቢያ በር በነገው ዕለት ይመረቃል
************
(ኢ ፕ ድ)
ከ90 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የሐዋሳ ከተማ መግቢያ ሚሊኒየም ፓርክ በነገው ዕለት እንደሚመረቅ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ አስታወቀ፡፡
በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ታሪኩ ታመነ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በከተማው በ2014 ዓ.ም የተጀመሩትን አብዛኛዎቹን ፕሮጀክቶች በዚህ ዓመት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ታቅዶ እየተሠራ ነው፡፡
በከተማ በተለይም በUNDP የሚደገፉ 29 ፕሮጀክቶች መኖራቸው ጠቁመው፣ ከአስፋልት መንገድ ግንባታ ውጪ ያሉት ሌሎች ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቁ ገልጸዋል፡፡
ከሁሉም ለየት የሚለውና ጥቁር ውሃ መግቢያ በር ላይ እየተገነባ የሚገኘው ሚሊኒየም ፓርክ ሪስቶሬሽን ፕሮጀክት ለከተማውና ለክልሉ እንዲሁም እንደ ሀገርም ትልቅ ትርጉም ያለው ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡፡
ሰኔ 2014 ዓ.ም የአንድ ዓመት የግንባታ ውል የተገባለት ፕሮጀክት ከ90 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል። ግንባታው በተያዘለት ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡
የፕሮጀክቱ ግንባታ የሲዳማን ባህላዊ ዕሴቶችን ማሳየት የሚችልና በአሁኑ ወቅት ዓለም የደረሰበትን ሙሉ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የተገነባ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡
ወደ ሐዋሳ ከተማ መግቢያ በር የሆነው ፕሮጀክት በሀገሪቱ ካሉት መሰል ፕሮጀክቶች የመጀመሪያው ይሆናል።
በተጨማሪም የትምህርት፡ የጤናና ሌሎችም አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ግንባታቸው ተጠናቅቆ ለሕብረተሰቡ ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋልም ብለዋል አቶ ታሪኩ፡፡
በጥቁር ዉሃ ዳቶ ሐዋሳ መግብያ በር ሙሉ በሙሉ ዲጂታል ተክኖሎጂ የተገጠመለት በመሆኑ ወጪና ገቢ የትራፊክ ፍሰት ከመቆጣጠሩም በላይ የከተማዉን ብሎም የህብረተሰቡን ደህንነት ለተጠበቀ ያግዛል በለዋል። ከፍትኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል።
በከተማው ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ ከሚገኙት ፕሮጀክቶች መካከል 15 ሎት ጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ፤ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ የሚሠሩ ሼዶች፤ 8 የታክሲ ተርሚናሎች፤ የሕዝብ መዝናኛ ሥፍራዎች፣ 3 ቦታ የሚተከሉ የትራፊክ እንዲሁም ሌሎች የመንገድ ዳር መብራቶች፡ ዘመናዊና ውብ የሆኑ የእግረኛ መንገዶች እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡
በአምሳሉ ፈለቀ

የቢላሎ - ቀርሳ - አርሲ ነገሌ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ አፈጻጸም 93 በመቶ ላይ ደርሷል
********************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን እየተገነባ ያለው የቢላሎ - ቀርሳ - አርሲ ነገሌ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ አፈጻጸም 93 በመቶ ላይ የደረሰ ሲሆን ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ፡፡
የመንገዱን ግንባታ ለማከናወን አንድ ቢሊዮን ሰባት መቶ አራት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰድሳ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ስምንት ብር ወጪው በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው ፡፡
ግንባታውን እያካሄደ የሚገኘው የስራ ተቋራጭ ቻይና ኮሚዩኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ (CCCC) ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ሽላዲያ አሶሴት ከኢንሲራድ ሲቪል ኢንጂነሪንግ ሲስተም እና ሂትከን ኢንጅነሪንግ ጋር በጣምራ እያከናወኑት ይገኛሉ ፡፡
መንገዱ በዋናነት ቢላሎ ከተማን፣ ኤጎ ከተማን፣ ቀርሳ ከተማን እና ጎልጆታ ከተማን የሚያገናኝ ሲሆን ይኸውም የአሰላና ሻሸመኔ ከተማን ለማገናኘት ቀላል ያደርገዋል፡፡
ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የሚያልፍባቸው ዞን እና ወረዳዎች በስንዴ፣ ገብስ እና ድንች አምራችነት ከሚታወቁ ቦታዎች ውስጥ ስለሆኑ እነዚህን የግብርና ምርቶች ወደ መሃል ሃገር ገበያ ለማምጣት ጉልህ ሚና አለው፡፡