ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት የደቡብ ሱዳን ተልዕኮ ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል ገለጸች
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት የደቡብ ሱዳን ተልዕኮ (UNMISS) ድጋፍ ማድረጓን አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች።
በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ከዩኤንሚስ(UNMISS) ምክትል ኃላፊና ከተመድ የደቡብ ሱዳን ምክትል ልዩ ተወካይ ጉዋንግ ኮንግ ጋር ተወያይተዋል።
ሁለቱ ባለስልጣናት በቀጣናው ባለው የሰላም እና ደህንነት ሁኔታ ላይ መወያየታቸው ተገልጿል።
ጉዋንግ ኮንግ ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን እየተወጣች ያለው ወሳኝ ሚና እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች ለዩኤንሚስ እያደረጉት ያለውን ትልቅ አበርክቶ አድንቀዋል።
በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በቀጣናው መረጋጋት እንዲሰፍን አበክራ እየሰራች ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ዩኤንሚስ ለሚያከናውናቸው ስራዎች በቀጣይ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥልም ገልጸዋል።
በተባበሩት መንግስታት የደቡብ ሱዳን ተልዕኮ(ዩኤንሚስ) በተመድ የጸጥታ ምክር ቤት ውሳኔ የተቋቋመው እ.አ.አ በ2011 ነው።
እንደ ኢዜአ ዘገባ የተልዕኮው አላማ በደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት አማካኝነት አገሪቷ ዳግም ወደ እርስ በእርስ ጦርነት እንዳትመለስ መከላከል፣ ጠንካራ ሰላም መገንባት እንዲሁም ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ እና ነጻ ምርጫ እንዲካሄድ ድጋፍ ማድረግ ናቸው።
ኢትዮጵያ ለዩኤንሚስ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰላም አስከባሪ ኃይል ካበረከቱ አገራት መካከል በዋናነት ትጠቀሳለች።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️
‘ገበታ ለሸገር’ እና ‘ገበታ ለሀገር’ የቱሪዝም ሴክተር ልማት ሥራዎች በአብዛኛው ተጠናቅቀዋል። ይሄን ተከትሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ 8 የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማልማት የ‘ገበታ ለትውልድ’ ሐሳባችንን ገፍተንበታል። የዐርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርትን በ120 ሄክታር መሬት ላይ፣ የአባያ ሐይቅን እያየ በሚያማምር ቦታ ላይ እንዲገነባ ዛሬ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠናል።
በዓመት ከመንፈቅ ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቀው ይህ ፕሮጄክት 1.3 ትሪሊዮን ዶላር የሚሸፍነውን ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ዘርፍ ገቢን ተቋዳሽ እንድንሆን ያደርገናል። ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ ሀብታችንን በመጠቀም ሀብት የማፍራት ጅምሮችን በማስፋፋት፣ የብልጽግና ጉዟችንን ለማሳካት እንተጋለን።

ከንቲባ አዳነች በዛሬው እለት ከ17 ሺህ በላይ የሰላምና ፀጥታ አካላት ጋር ችግኝ ተከሉ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከ17 ሺህ በላይ የሰላምና ፀጥታ አካላት ጋር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ችግኝ ተከሉ።
በዛሬው እለት 100 ሺህ ችግኞች የሚተከሉ ሲሆን የሰላምና ፀጥታ አካላቱ አንድ ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል እቅድ እንደያዙም ተገልጿል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በከተማዋ በሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ 17 ሚሊዮን ሀገር በቀል ዛፎች፣ ለምግብነት የሚውሉ እና ለውበት የሚሆኑ ችግኞችን በከተማችን የተለያዩ አካባቢዎች የሚተከሉ ይሆናል።
አዲስ አበባን አረንጓዴ በማልበስ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ውብ ከተማ ለማድረግ ሁላችንም ችግኝ መትከል አለብን ያሉ ሲሆን ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክበን እንዲጸድቁ እና ፍሬ እንዲያፈሩ ማድረግ የሁላችንም ሃላፊነት ነው ብለዋል።
በሳሙኤል ወንደሰን

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሲዲሲ ድጋፍ ማድረጓን ትቀጥላለች
-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
***********************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ በሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ) የምታደርገውን ድጋፍ እንደምታጠናክር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።
አቶ ደመቀ ከአፍሪካ ሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጂን ካሴያ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
በውይይቱም በአዲስ አበባ የተገነባው አዲሱ የአፍሪካ ሲዲሲ የዋና መቀመጫ ሕንጻ በአፍሪካ የጤና አጀንዳ ለማራመድ የሚያስችል ዐብይ ፕሮጀክት መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ማዕከሉ እያከናወናቸው ላሉ ስራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመው የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጂን ኬሲያ የኢትዮጵያ መንግሥት ለማዕከሉ እያደረገ ለሚገኘው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
አፍሪካ ሲዲሲ ለአባል አገራት አስፈላጊውን የቴክኒክ ድጋፍ መስጠቱን እንደሚቀጥል መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል የአፍሪካ ሕብረት ገለልተኛ የጤና ተቋም ሆኖ እ.አ.አ 2016 መቋቋሙ ይታወሳል። ማዕከሉ የሕብረቱ አባል አገራት በሽታን አስቀድሞ ማወቅ፣መከላከል እና መቆጣጠር የሚያስችላቸውን አቅም እንዲገነቡ እና የማህበረሰብ ጤና መርሐ-ግብሮች ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፍ ያደርጋል።

ኢትዮጵያ የናይል ኮሚሽንን ለማቋቋም ዲፕሎማሲያዊ ጥረቷን አጠናክራ ቀጥላለች
********************
(ኢ ፕ ድ)
የተፋሰሱን ሀገራት ትስስር ለማጠናከርና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ የናይል ኮሚሽንን ለማቋቋም ዲፕሎማሲያዊ ጥረቷን አጠናክራ እንደቀጠለች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር ፍስሐ ሻወል አስታወቁ፡፡
በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ፍስሐ ሻወል ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ከግብፅ በስተቀር ሁሉም የተፋሰሱ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104083

የሐዋሳ ከተማ መግቢያ ሚሊኒየም ፓርክ ግንባታ ተጠናቅቆ በዛሬው ዕለት ተመርቋል
**********************
(ኢ ፕ ድ)
በሐዋሳ ከተማ ከ90 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የሐዋሳ ከተማ መግቢያ ሚሊኒየም ፓርክ ግንባታ ተጠናቅቆ
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተመርቋል።
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ተገንብተው የተጠናቀቁ የተለያዩ ፕሮጀክቶችም ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።
በዛሬው ዕለት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በተገኙበት የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።
በይፋ የተመረቀው የሐዋሳ ከተማ መግቢያ ሚሊኒየም ፓርክ በግራና ቀኝ የሲዳማን ባህላዊ የቤት አሰራርን፣ አናቱ ላይ ደግሞ የሻፌታን ቅርጽ የያዘ ሲሆን የ "እንኳን ደህና መጣችሁ" ን መልዕክትንም ያዘለ ነው።
የሐዋሳ ከተማ መግቢያ ሚሊኒየም ፓርክ ከ90 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደወጣበት ለማወቅ ተችሏል።
በተመረቁ ፕሮጀክቶች መሐል ለሀዋሳ ከተማ አዲስ ገፅታ የሆነው የከተማ መግቢያ በር፣ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተገነቡ ት/ቤቶች ታቦር አንደኛ ደረጃ G+3 የመማሪያ ህንፃና ሌሎች ፕሮጀክቶች ምረቃ እየተካሄደ ይገኛል።
በአስቴር ኤልያስ (ሐዋሳ)