Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የፖሊስ ዩኒቨርሲቲው ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ግንባታ እያከናወነ ነው
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ በመበጀት ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያቀፉ ግንባታዎችን እያከናወነ መሆኑን ገለጸ፡፡ በሰው ኃይል ልማትም ከመጀመሪያ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ባለሙያዎችን እያሰለጠነ መሆኑን ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ የፌዴራል ፖሊስ በጥናት ምርምር ሥራዎች ላይ ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104137
ሄራልድ-ለስምንት አስርተ ዓመታት የፀናው የፍትሕ ድምፅ
***************
(ኢ ፕ ድ)

አረጋዊ ነው፤ የሰማንያ ዓመታቱ ጌታ፡፡ ፈር ቀዳጅ ነው፤ ልበሙሉ ነጻነት የተቸረው። የጭቁኖች ልሳን ነው፤ መሰማት ለሻተ ሁሉ ድምፅ ሲሆን የኖረ፡፡ የፍትህ ጋሻ ጃግሬ ነው፤ የባርነት ቀንበር ለተጫናቸው እንደአንበሳ ያገሳ። ድልድይ ነው፤ ሀገሪቱን ከተቀረው የዓለም ክፍል ጋር ያገናኘ፡፡ ባለራዕይ ነው፤ ጥቁሮች ለተነጠቁት የነፃነት ጮራ የብርሃ መስኮትን ያጋራ፡፡

ዘ ኢትዮጵያን ሄራልድ መጠሪያ ስሙ ነው። የኢትዮጵያን ስም ተሸካሚው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የአብራክ ክፋይ፡፡ እንግሊዘኛ መተየቢያ ቋንቋው ነው። ጥቁሮች ስለ ነፃነት ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104096
በዲጂታል የነዳጅ ግብይት ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ልውውጥ ተደርጓል
****************
(ኢ ፕ ድ)

በአስገዳጅ ሁኔታ ተግባራዊ መደረግ በጀመረው የኤሌክትሮኒክስ ነዳጅ ክፍያ ሥርዓት ከ24 ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ልውውጥ መደረጉን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከአንድ ሺህ 317 በላይ የነዳጅ ማደያዎች በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ አማራጮች ግብይት እያከናወኑ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የታለመለት ነዳጅ ድጎማ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሰልማን ሙሐመድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የኤሌክትሮኒክስ ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104113
መልካም ዕድል‼️
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️

የ#አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እያንዳንዱን የሀገሪቱን ጥግ ለመሸፈን ያለመ ነው። ዛሬ በደቡብ ኦሞ ዞን ኝአንጋቶም ወረዳ ዐሻራችንን አሳርፈናል። በእንደዚህ ዓይነት አካባቢ የምናደርገው ጥረት የድርቅን ሥጋት ለመከላከል ያለመ ነው። እነዚህን ተግባራት በማስቀጠል ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን በመትከል ፍሬያማ ውጤት ማግኘት እንችላለን።