Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
መልካም ዕድል‼️
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️

የ#አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እያንዳንዱን የሀገሪቱን ጥግ ለመሸፈን ያለመ ነው። ዛሬ በደቡብ ኦሞ ዞን ኝአንጋቶም ወረዳ ዐሻራችንን አሳርፈናል። በእንደዚህ ዓይነት አካባቢ የምናደርገው ጥረት የድርቅን ሥጋት ለመከላከል ያለመ ነው። እነዚህን ተግባራት በማስቀጠል ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን በመትከል ፍሬያማ ውጤት ማግኘት እንችላለን።
የፌዴራል ፖሊስ ሠላምን ለማረጋገጥ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል
-ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል
*********************************
(ኢ ፕ ድ)

የፌዴራል ፖሊስ ሠላምን ለማረጋገጥ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት ፕሬዚደንት ገለጹ፡፡

በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የምዕራብ ፈጥኖ ደራሽ በአሶሳ ከተማ ያስገነባውን ካምፕ ዛሬ አስመርቋል።

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት ፕሬዚደንት በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ እንዳሉት፤ ፌዴራል ፖሊስ በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ ግዙፍ አቅም እየፈጠረ ነው።

የፌዴራል ፖሊስ ሠላምን ለማረጋገጥ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፤ በአሶሳ ከተማ ከተመረቀው በተጨማሪ በየክልሉ የሠራዊቱን አቅም የሚያጠናክሩ ካምፖች እየተገነቡ ነው ብለዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን በበኩላቸው፤ ክልሉ ወደ ተረጋጋ ሠላም እንዲመለስ የፌዴራል ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል ብለዋል።

በክልሉ በአሁኑ ወቅት በማዕድንና በሌሎች ዘርፎች የኢንቨስትመንት እንቅስቅሴዎች እንዳሉ ገልጸው፤ ኢንቨስትመንቱ እንዲጠናከር የፌዴራል ፖሊስ እገዛ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

የዝግጅቱ ታዳሚዎች ችግኝ በመትከልም አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
የኢትዮጵያን የምርጫ ስርአት ለማጠናከር የሚውል ከ30 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ተፈረመ
*********************
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ ዘላቂ ዲሞክራሲን ለማስፈን የሚያስችላትን የምርጫ ስርአት እንድታጠናክር ለማግዝ የሚውል የ30 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር የፋናንስ ድጋፍ ስምምነት ፕሮጀክት በገንዘብ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድና በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ድርጅት መካካል ተፈርሟል፡፡

ፕሮጀክቱ ሶስት ግቦች ያሉት ሲሆን አንድኛው የምርጫ ቦርድ ተቋማዊ መዋቅርን በማጠናከር ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ አሳታፊ ፣ተአማኒና ደረጃውን የጠበቀ ምርጫና ህዝበ ውሳኔ እንዲያካሂድ ተቋሙን ማጠናከር፣ ሁለተኛው ከሲቪክ ተቋማት ጋር በጋር በመሆን በምርጫ ሂደት የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎን ማሳደግ ሶስተኛው ደግሞ ነፃ ፍትሀዊ እና ተአማኒ ምርጫ እንዲያከሂድ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ናቸው፡፡

ፕሮጀክቱ በሚቀጥሉት አራት አመታት ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን የሀገሪቱን የምርጫ ስርአት በማጠናከር ዘላቂ ዴሞክራሲን ለማስፈን አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት ‼️

በእርከን ሥራ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በውኃ ማቆር እና በጥንታዊ የእጅ መሣሪያዎች በታወቀው የኮንሶ ሕዝብ መካከል በመገኘቴ እጅግ ደስ ብሎኛል።