Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሄራልድ-ለስምንት አስርተ ዓመታት የፀናው የፍትሕ ድምፅ
***************
(ኢ ፕ ድ)

አረጋዊ ነው፤ የሰማንያ ዓመታቱ ጌታ፡፡ ፈር ቀዳጅ ነው፤ ልበሙሉ ነጻነት የተቸረው። የጭቁኖች ልሳን ነው፤ መሰማት ለሻተ ሁሉ ድምፅ ሲሆን የኖረ፡፡ የፍትህ ጋሻ ጃግሬ ነው፤ የባርነት ቀንበር ለተጫናቸው እንደአንበሳ ያገሳ። ድልድይ ነው፤ ሀገሪቱን ከተቀረው የዓለም ክፍል ጋር ያገናኘ፡፡ ባለራዕይ ነው፤ ጥቁሮች ለተነጠቁት የነፃነት ጮራ የብርሃ መስኮትን ያጋራ፡፡

ዘ ኢትዮጵያን ሄራልድ መጠሪያ ስሙ ነው። የኢትዮጵያን ስም ተሸካሚው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የአብራክ ክፋይ፡፡ እንግሊዘኛ መተየቢያ ቋንቋው ነው። ጥቁሮች ስለ ነፃነት ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104096
በዲጂታል የነዳጅ ግብይት ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ልውውጥ ተደርጓል
****************
(ኢ ፕ ድ)

በአስገዳጅ ሁኔታ ተግባራዊ መደረግ በጀመረው የኤሌክትሮኒክስ ነዳጅ ክፍያ ሥርዓት ከ24 ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ልውውጥ መደረጉን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከአንድ ሺህ 317 በላይ የነዳጅ ማደያዎች በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ አማራጮች ግብይት እያከናወኑ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የታለመለት ነዳጅ ድጎማ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሰልማን ሙሐመድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የኤሌክትሮኒክስ ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104113
መልካም ዕድል‼️
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️

የ#አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እያንዳንዱን የሀገሪቱን ጥግ ለመሸፈን ያለመ ነው። ዛሬ በደቡብ ኦሞ ዞን ኝአንጋቶም ወረዳ ዐሻራችንን አሳርፈናል። በእንደዚህ ዓይነት አካባቢ የምናደርገው ጥረት የድርቅን ሥጋት ለመከላከል ያለመ ነው። እነዚህን ተግባራት በማስቀጠል ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን በመትከል ፍሬያማ ውጤት ማግኘት እንችላለን።
የፌዴራል ፖሊስ ሠላምን ለማረጋገጥ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል
-ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል
*********************************
(ኢ ፕ ድ)

የፌዴራል ፖሊስ ሠላምን ለማረጋገጥ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት ፕሬዚደንት ገለጹ፡፡

በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የምዕራብ ፈጥኖ ደራሽ በአሶሳ ከተማ ያስገነባውን ካምፕ ዛሬ አስመርቋል።

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት ፕሬዚደንት በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ እንዳሉት፤ ፌዴራል ፖሊስ በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ ግዙፍ አቅም እየፈጠረ ነው።

የፌዴራል ፖሊስ ሠላምን ለማረጋገጥ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው፤ በአሶሳ ከተማ ከተመረቀው በተጨማሪ በየክልሉ የሠራዊቱን አቅም የሚያጠናክሩ ካምፖች እየተገነቡ ነው ብለዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን በበኩላቸው፤ ክልሉ ወደ ተረጋጋ ሠላም እንዲመለስ የፌዴራል ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል ብለዋል።

በክልሉ በአሁኑ ወቅት በማዕድንና በሌሎች ዘርፎች የኢንቨስትመንት እንቅስቅሴዎች እንዳሉ ገልጸው፤ ኢንቨስትመንቱ እንዲጠናከር የፌዴራል ፖሊስ እገዛ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

የዝግጅቱ ታዳሚዎች ችግኝ በመትከልም አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።