አዲሱ የኢቢሲ ሚዲያ ኮምፕሌክስ ዛሬ በይፋ ይመረቃል
******************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ሸጎሌ አካባቢ የተገነባው አዲሱ የኢቢሲ ሚዲያ ኮምፕሌክስ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ በይፋ ይመረቃል። ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ተቋሙ በአፍሪካ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስችለዋል።
ሰሞኑን የምረቃው አካል የሆኑ የተለያዩ ዝግጅቶች ሲካሄዱ መቆየታቸው ይታወቃል።
በተራራ የተከበበውና በእጽዋት ያጌጠው አዲሱ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ዓለም በደረሰበት የሚዲያ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ነው።
ለሚዲያው ሠራተኞች ምቹ የሥራ ከባቢን በመፍጠር ተቋማዊ አፈፃፀም እንዲያድግ ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
ኢቢሲ "ለኢትዮጵያ ልዕልና" በሚል መሪ ቃል በአዲሱ የሚዲያ ኮምፕሌክሱ በሁሉም ሚዲየሞቹ አዳዲስ ይዘቶችን እና አቀራረቦችን አካቶ ወደ አድማጭ ተመልካች ለመድረስ ዝግጅቱን አጠናቋል።
ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ የመጀመሪያውን የትምህርት ፌስቲቫል ማካሄድ ጀመረ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ የኢፋ ቦሩ ሁለተኛ ደረጃ ልዩ አዳሪና የኦሮሚያ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያውን የትምህርት ፌስቲቫል ማካሄድ ጀመረ።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም እየተካሄደ ባለው ፌስቲቫል የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ፣ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ፣ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በዚህ ፌስቲቫል የኦሮሚያ ኢፋ ቦሩ ሁለተኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችና ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ በዛሬው እለት የተጀመረው ይህ ፌስቲቫል ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ መሆኑ ተጠቁሟል።
በቃልኪዳን አሳዬ (አዳማ)

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ‼️
ዛሬ በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ የተሰናዳውን የትምህርት ፌስቲቫል ከትህምርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ ጋር በማስጀመሬ ከፍ ያለ ደስታ ተሰምቶኛል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የትምህርት ዘርፉን ከአምስቱ የክልሉ የትኩረት አቅጣጫዎች አንዱ አድርጎ እየሰራ ይገኛል። ይህ አውደርዕይ የኢፋ ቦሩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች እና የክልላችን ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በቋንቋና ሥነ-ጥበብ ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ለማስተዋወቅ ትልቅ ድርሻ ያለው ነው።
በኦሮሚያ ልማት ማህበር፣ በኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤቶች ወይም በአጠቃላይ በክልላችን የትምህርት ልማት ስራዎች ላይ ተሳትፎ ያደረጋችሁ ግለሰቦች እንዲሁም ተቋማት በተጨማሪም ወደፊት ተሳትፎ ለማድረግ ሃሳቡ ያላችሁ ሁሉ ከዛሬ እለት አንስቶ ለተከታታይ አራት ቀናቶች ወደ አዳማ ከተማ በመምጣት የድካማችሁ ፍሬ ዉጤት የሆነውን እንድትመለከቱና ልምድ እንድትቀስሙ ከወዲሁ ጥሪዬን አቀርባለሁ።