አዲሱ የኢቢሲ ሚዲያ ኮምፕሌክስ ዛሬ በይፋ ይመረቃል
******************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ሸጎሌ አካባቢ የተገነባው አዲሱ የኢቢሲ ሚዲያ ኮምፕሌክስ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ በይፋ ይመረቃል። ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ተቋሙ በአፍሪካ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስችለዋል።
ሰሞኑን የምረቃው አካል የሆኑ የተለያዩ ዝግጅቶች ሲካሄዱ መቆየታቸው ይታወቃል።
በተራራ የተከበበውና በእጽዋት ያጌጠው አዲሱ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ዓለም በደረሰበት የሚዲያ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ነው።
ለሚዲያው ሠራተኞች ምቹ የሥራ ከባቢን በመፍጠር ተቋማዊ አፈፃፀም እንዲያድግ ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
ኢቢሲ "ለኢትዮጵያ ልዕልና" በሚል መሪ ቃል በአዲሱ የሚዲያ ኮምፕሌክሱ በሁሉም ሚዲየሞቹ አዳዲስ ይዘቶችን እና አቀራረቦችን አካቶ ወደ አድማጭ ተመልካች ለመድረስ ዝግጅቱን አጠናቋል።
ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ የመጀመሪያውን የትምህርት ፌስቲቫል ማካሄድ ጀመረ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ የኢፋ ቦሩ ሁለተኛ ደረጃ ልዩ አዳሪና የኦሮሚያ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያውን የትምህርት ፌስቲቫል ማካሄድ ጀመረ።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም እየተካሄደ ባለው ፌስቲቫል የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ፣ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ፣ የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በዚህ ፌስቲቫል የኦሮሚያ ኢፋ ቦሩ ሁለተኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችና ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ በዛሬው እለት የተጀመረው ይህ ፌስቲቫል ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ መሆኑ ተጠቁሟል።
በቃልኪዳን አሳዬ (አዳማ)

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ‼️
ዛሬ በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ የተሰናዳውን የትምህርት ፌስቲቫል ከትህምርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ ጋር በማስጀመሬ ከፍ ያለ ደስታ ተሰምቶኛል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የትምህርት ዘርፉን ከአምስቱ የክልሉ የትኩረት አቅጣጫዎች አንዱ አድርጎ እየሰራ ይገኛል። ይህ አውደርዕይ የኢፋ ቦሩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች እና የክልላችን ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በቋንቋና ሥነ-ጥበብ ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ለማስተዋወቅ ትልቅ ድርሻ ያለው ነው።
በኦሮሚያ ልማት ማህበር፣ በኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤቶች ወይም በአጠቃላይ በክልላችን የትምህርት ልማት ስራዎች ላይ ተሳትፎ ያደረጋችሁ ግለሰቦች እንዲሁም ተቋማት በተጨማሪም ወደፊት ተሳትፎ ለማድረግ ሃሳቡ ያላችሁ ሁሉ ከዛሬ እለት አንስቶ ለተከታታይ አራት ቀናቶች ወደ አዳማ ከተማ በመምጣት የድካማችሁ ፍሬ ዉጤት የሆነውን እንድትመለከቱና ልምድ እንድትቀስሙ ከወዲሁ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን የሰባት ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን የ7 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ።
የድጋፍ ስምምነቱ የተደረገው የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው በተገኙበት የኢትዮጵያ የብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) እና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ ተፈራርመዋል።
ህብረቱ ድጋፉን ያደረገው ኮሚሽኑ እያከናወነ ያለው ብሔራዊ ምክክር በውጤት እንዲጠናቀቅ በማለም ነው።
እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ ስምምነቱ የተፈረመው የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራትና የዓለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች በተገኙበት ነው።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አዲሱ ክልል እንዲደራጅ ውሳኔ አሳለፈ
********
(ኢ ፕ ድ)
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ባካሄደበት በዛሬው ቀጣይ ዉሎው የስድስት ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የተካተቱበት «የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል» በሚል ስያሜ አዲስ 12ኛ ክልል ሆኖ እንዲደራጅ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ቀድሞ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይኖሩ የነበሩ የስድስት ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባካሄዱት ሕዝበ ውሳኔ በአንድ ክልል የመደራጀት ፍላጎታቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የብሔሮችን፣ ብሔረሰቦችንና ሕዝቦችን ውሳኔ መሰረት በማድረግ በአንድ ክልል እንዲደራጁ በዛሬው እለት ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ወስኗል፡፡
«የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል» በሚል በአዲስ የተደራጁት በወላይታ፣ በጋሞ፣ በጎፋ፣ በጌዲዮ፣ በደቡብ ኦሞ፣ በኮንሶ ዞኖችና በደራሼ፣ በቡርጂ፣ በአማሮ፣ በኧሌና በባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች የሚገኙ ሕዝቦች ናቸው፡፡
ቀድሞ የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል ውስጥ የነበሩ የሀድያ፣ የሀላባ፣ የከምባታ ጠምበሮ፣ የስልጤ፣ የጉራጌ ዞኖችና የየም ልዩ ወረዳ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በነባሩ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የሚቀጥሉ ይሆናል።
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በ6ኛው የፓርላማ ዘመን፣ በ1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜው ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ውስጥ በስድስት ዘኖችና በአምስት ልዩ ወረዳዎች የሚገኙ የጌዴኦ ፣ የወላይታ ፣ የጋሞ ፣ የጎፋ ፣ የኮንሶ እና የደቡብ ኦሞ ዘኖች እንዲሁም የቡርጂ፣ የአማሮ፣ የደራሼ፣ የባስኬቶ እና የኧሌ ልዩ ወረዳዎች ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በጋራ ክልል ለመመስረት ያቀረቡትን ጥያቄ በመቀበል በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 47/3/(ለ)መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕዝበ ውሳኔ እንዲያደራጂ እና በጋራ ክልል የመመሥረት ጥያቄው የሕዝቡን ይሁንታ ስለማግኘቱ የሕዝበ ውሳኔውን ውጤት ሪፖርት ለምክር ቤቱ እንዲያቀርብ ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ መምራቱ ይታወሳል።
አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር የውሳኔ ሀሳቡ እንዲጸድቅ አቅርበው በሙሉ ድምጽ ደግፎ ማፅደቁን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ በነገው ዕለት ማብራሪያ ይሰጣሉ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ጉባዔውን ነገ ያካሂዳል።
ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሂደው 28ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፌዴራል መንግሥት የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች የሚሰጡትን ምላሽ እና ማብራሪያ ያዳምጣል።
ምክር ቤቱ በውሎው የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2016 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን አስመልክቶ የሚያቀርበውን ሪፖርት እና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ የበጀት አዋጁን እንደሚያጸድቅም የሚጠበቅ መሆኑን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።