Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የሁለቱ አገራትን የአረንጓዴ አሻራ ዲፕሎማሲ እውን ያደረገ ነው"
- አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
****************************
(ኢ ፕ ድ)

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንን "ነገን ዛሬ እንትከል" በሚል በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ከጅቡቲ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ጋር በመሆን በአይሲቲ ፓርክ ችግኝ ተከሉ።

አቶ ደመቀ መኮንን ከጅቡቲ የፐብሊክ ዲጵሎማሲ ልኡካን ጋር ችግኝ በተከሉበት ወቅት እንደገለጹት፣ የሁለቱ አገራት ህዝቦች ታሪካዊና ከጎረቤትነት የዘለለ ትስስርና ትብብር አላቸው።

ዛሬ የተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በአይሲቲ ፓርክ የጅቡቲ የተከናወነው መርሃግብር የሁለቱ አገራት የትብብር ማቀፍ እውን ያደረገ ታሪካዊ ሁነት ነው ብለዋል።

የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ግንኙነት በቀጣይም በሁለንተናዊ ማዕቀፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ይህ አረንጓዴ አሻራ ዲፕሎማሲ በጅቡቲና በኢትዮጵያ እውን የሆነበት ነውም ብለዋል።
በሞገስ ተስፋ
ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ አዲሱን የኢቢሲ ሚዲያ ኮምፕሌክስ መረቁ
******************
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ ሸጎሌ አካባቢ የተገነባው አዲሱን የኢቢሲ ሚዲያ ኮምፕሌክስን
መርቀው ከፍተዋል።

ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ተቋሙ በአፍሪካ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስችለዋል ተብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ለምክር ቤት የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባሉ
****************
(ኢ ፕ ድ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የመንግስትን የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀርባሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምክር ቤቱ ዛሬ በሚያካሂደው 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ስብሰባው የፌደራል መንግስት የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለምክር ቤቱ የመንግስትን የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ የሚያቀርቡትን ሪፖርትና ማብራሪያ በሁሉም የማህበራዊ ገጾቻችን ይከታተላሉ።

ለሲዳሙ አፎ https://www.facebook.com/Epasidaamu/

ለአፋን ኦሮሞ https://www.facebook.com/Epabariisaa/

ለትግርኛ https://www.facebook.com/Epatigrigna/ 

ለእንግሊዘኛ https://www.facebook.com/epaEnglish/ 

ለአፋርኛ ቋንቋ https://www.facebook.com/profile.php?id=100092595632078

ለሶማልኛ ቋንቋ https://www.facebook.com/profile.php id=100092677890373

ለአረብኛ https://www.facebook.com/Epaalalam/