Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ማህበረሰብ የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተከናወነ
*******************
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ማህበረሰብ የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በዛሬው እለት በለሚኩራ ክፍለ ከተማ በጨፌ ትምህርት ቤት ተከናውኗል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ጀማሉ ጀንበሩ፤ በከተማ አስተዳደር ደረጃ ባለፉት አራት አመታት 42 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል እንደተቻ አስታውሰው በተያዘው ዓመት 17 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዷል ብለዋል።

የዓለማችን ፈተና የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል ችግኝ መትከል አስፈላጊ ነው። እንዲሁም ዛሬ ላይ የሚንተክለው ችግኝ የነገው ትውልድ በተሻለና ምቹ በሆነ ምድር ላይ እንድኖር ያደርጋል ነው ያሉት።

አረንጓዴ አሻራ ከውበት ይልቅ ለትውልድ ትልቅ መሰረት የምንጥልበት እንደ መሆኑ መጠን መምህራን በተማሪዎች ላይ ከመለያየት ይልቅ ስለ አንድነት በማስተማር ሀገር ተረካቢ ትውልድ እንዲያፈሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው የዛሬው ቀን ሰኔ 30 መሆኑን አስታውሰው ቀኑ ሲታሰብ በአዕምሮአችን የሚመጣው ውጤት የምናይበትና ወደቀጣዩ ምዕራፍ የምንሻገርበት ነው ብለዋል።

ዛሬ ላይ ሆነን ነገን እንትከል ስንል ለነገው ሀገር ተረካቢው ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ ነው ሲለዚህም ነገን የሚትረከቡን እናንተ በመሆናችሁ ጠንክራችሁ ስሩ በማለት ለተማሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዛሬው እለት በተከናወነው በዚህ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ከ15 ሺ በላይ ችግኞች እንደሚተከሉ ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው እለት ተፈራርመዋል።

ሁለቱ ተቋማት በሚዲያና ኮምንኬሽን ዘርፍ በጋራ ለመስራት ስምምነቱን የፈጸሙ ሲሆን፤ ኢፕድ በዚህ መስክ ያለውን የካበተ ልምድ ለተቋሙ ለማጋራት እንደሚሰራ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

ይህንኑ ስምምነት በኢፕድ በኩል የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ሄለን እስክንድር የፈረሙ ሲሆን፤ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በኩል ደግሞ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የትራንስፎርሜሽንና ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም ከተማ ፈርመዋል።

ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም
በሞገስ ተስፋ
ከነገ ጀምሮ ሁሉም ሚንስትሮችና ሚንስትር ዴኤታዎች ለስራ ግምገማ ወደክልሎች እንደሚሄዱ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አስታወቁ
********************
(ኢ ፕ ድ)

ከነገ ጀምሮ ሁሉም ሚንስትሮችና ሚንስትር ዴኤታዎች የስራ ግምገማ ለማድረግ ወደክልሎች እንደሚጓዙ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ትናንት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ላይ እንደተናገሩት፤ ከነገ ሐምሌ አንድ ቀን 2015 ጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት ሁሉም ሚንስትሮችና ሚንስትር ዴኤታዎች በየክልሉ የስራ ግምገማ ያደርጋሉ።

ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ድኤታዎች ለስራ ግምገማው የሚሄዱባቸው ክልሎች ተመድቦ ማለቁን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እነዚሁ ሚንስትሮች በሄዱባቸው ቦታዎች እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በምን ደረጃ ላይ እንዳሉና ምን ክፍተት እንዳለ ይገመግማሉ ብለዋል።

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለጻም፤ ሚኒስትሮቹ ከመስክ ምልክታ ሲመለሱ ግምገማ ይካሄዳል።

ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓም
በሀይማኖት ከበደ
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
የኦሮሚያ ልማት ማህበር አንግቦ የተነሳውን የልማት ዓላማ ለማሳካት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥርለትን ሕንጻ በአዳማ ከተማ አስገንብቶ ለምርቃት በማብቃቱ የማኅበሩ አባላትንና ደጋፊዎቹን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡
የህዝብ አቅም ኃያል ነው፤ ችግሮቻችንን ለይተን በቅንነት፣ በታማኝነትና በትጋት እስከተጠቀምንበት ድረስ የማንሻገረው ችግር፤ የማናሳካው እቅድ እንደሌለ ይህ ስኬት ያስተምራል። ለተሰጠኝ እውቅናም አመሰግናለሁ።
ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም
መልካም ዕድል፤ ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም
በአፍሪካ ምቹ የንግድ ሥራ እንዲኖር ሀገራት የፖሊሲ ማሻሻያ ሊያደርጉ ይገባል
*****************
(ኢ ፕ ድ)

በአፍሪካ የንግድ ሥራን ምቹ ለማድረግ ሀገራት የፖሊሲ ማሻሻያ ሊያደርጉ እንደሚገባ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ኤሌክትሮኒክስ ትሬድ ግሩፕ ሊቀመንበር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ። የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

“በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ገበያ የሥራ ፈጠራ፣ የዲጂታልና የፋይናንስ አካታችነትን ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104380
በክልሉ ከ600 ሺህ በላይ ወጣቶች በዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድ መርሀ-ግብር ይሳተፋሉ
***************
(ኢ ፕ ድ)

በሲዳማ ክልል በ2015 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፍቃድ መርሀ-ግብር ከ600 ሺህ በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ እና ከዚህም ይወጣ የነበረ ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳን ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104377
የጤና አውደ ርዕይው ከ70 ሺ በላይ በሚሆኑ ሰዎች ተጎብኝቷል
*************
(ኢ ፕ ድ)
ሀገር አቀፉ የጤና አውደ ርዕይ እስካሁን ከ70 ሺ በላይ በሚሆኑ ሰዎች መጎብኘቱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የአውደ ርዕዩን የ17 ቀናት ቆይታ አስመልክቶ የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ተገኔ ረጋሣ በሰጡት መግለጫ እንዳብራሩት፤ ሰኔ 13 ቀን የተከፈተው “የመጪው ትውልድ ጤና” አውደ ርዕይ በ30 ቀናት ውስጥ ከ100 ሺ በላይ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ በእቅድ ተይዞ ነበር።

በዚህም መሠረት እስካሁን ከ70 ሺ በላይ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የምርምር ተቋማት፣ የዩኒቨርሲቲዎች፣ የክልል የጤና ቢሮ ኃላፊዎች ሠራተኞችና ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104383