Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
“የእንስሳት ሀብት ጥቅም በትክክል እየተመዘነ አይደለም"
- ፕሮፌሰር ብርሃኑ በላይ ዓለም አቀፍ የእንስሳት እርባታ ተመራማሪ
**********************
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ ትልቅ ቁጥር ያለው የእንስሳት ሀብት ያላት ቢሆንም ሀብቱ በትክክል እየተመዘነ አለመሆኑንና ለሀብቱ ተገቢው ትኩረት አለመሰጠቱን ዓለም አቀፍ የእንስሳት እርባታ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ብርሃኑ በላይ ገለጹ።

ዓለም አቀፍ የእንስሳት እርባታ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በሁሉም ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=104402
የቤቶች ግንባታ በአዲስ አበባ - ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት!!

👉 የነባር 139 ሺህ 008 20/80 እና 40/60 ቤቶች ፕሮግራም የተመረጡ ወደ ቤት ለመግባት የሚያስችሉ ስራዎችን በማጠናቀቅ አፈጻጸሙን 13ዐ ሺህ ዐዐዐ (98.65 በመቶ) በማድረስ ባለእድለኞች ወደ ቤታቸው እንዲገቡ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፣

👉 በከተማው በጀት ከሚገነቡት 1ዐ ሺህ የኪራይ ቤቶች ውስጥ 4 ሺህ 4ዐዐ በሚቀጥለው መስከረም ወር ይጠናቀቃል፤

👉 5 ሺህ 6ዐዐ ተገጣጣሚ ቤቶች ደግሞ ግንባታ በአማካይ 29 ነጥብ 25 በመቶ ማድረስ ተችሏል፣

👉 በጋራ መኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር 4,940 ነዋሪዎች በ60 ማህበራት እንዲደራጁ ተደርጓል፣

👉 ከዚህ ውስጥ የ54 ማህበራት ቦታ ተረክበው የመጀመሪያ ኘሮግራም ተካሄዷል፣

👉 በመንግስትና በግል አጋርነት የቤት ልማት ፕሮግራም የ60ሺህ ቤቶች ግንባታ ለማስጀመር ቅድመ ሁኔታን ተጠናቋል፣

👉 የ90 ቀናት ልዩ ዕቅድ በጎ ፈቃደኞች ባለሃብቶችን በማስተባበር እና በከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ከ6 ሺህ 415 ቤቶችን በማስገንባት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የከተማችን ነዋሪዎች በኪራይ ለማስተላለፍ ተችሏል፣

👉 በአጠቃላይ ለባለእድለኞች የተላለፉት 130 ሺህ ቤቶችን ለኪራይ ከተገነቡት 4 ሺህ 400 እና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉት ነዋሪዎች የተገነቡትን 6 ሺህ 415፣ በድምሩ 140,815 ቤቶችን ለነዋሪዎች ማቅረብ ተችሏል።

ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም
የሀረሪ ክልል የወረዳ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች የዓባይ ግድብን ጎበኙ
***
****
(ኢ ፕ ድ)

የሀረሪ ክልል የወረዳ ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች በጉባ እየተገነባ የሚገኘውን የዓባይ ግድብ ሂደትና አሁናዊ ገጽታን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው የኢትዮጵያዊያን አሻራ ያረፈበትን ግድብ የመጎብኘት እድል በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

በጉብኝቱ ላይ የሀረሪ ክልል ምከር ቤት የህዝብ ግኑኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ዋቁማ እንዳሉት የዓባይ ግድብ በኢትዮጵያዊያን ትብብር እና አንድነት በመገንባት ላይ ያለ የጋራ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።

የግድቡን ገጽታና ስራ በቦታው ተገኝተው በመጎብኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ለሀገር ብልጽግና፣ አንድነትና ልማት መሰረት የሆነው የግድቡ ግንባታ በስኬት እንዲጠናቀቅ የሁሉም ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

ሐምሌ 1ቀን2015ዓ.ም
500 ሚልዮን ችግኞች በአንድ ጀንበር‼️
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች‼️

👉 ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በአንድ ጀንበር 500 ሚልዮን ችግኝ እንተክላለን፤ ዳግም ታሪክ እንስራ፣

👉 ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ/ም በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ታሪክ እንድንሰራ ጥሪ አቀርባለሁ፣

👉 ሐምሌ 10 ቀን ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ሪከርድ እንሰብራለን፤

👉 ከዚህ በፊት ከ350 ሚልዮን በላይ ዛፎች በአንድ ጀንበር ተክለን ዓለምን ጉድ አስብለናል፣

👉 ዘንድሮ 500 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር በመትከል የራሳችንን ሪከርድ እናሻሽላለን፣

👉 ዘንድሮም 6 ነጥብ 5 ቢልዮን ችግኝ ለመትከል በየክልሉ፣ በየዞኑና በየወረዳው ክረምቱን ከምንሠራቸው ሥራዎች አንዱ አረንጓዴ ዐሻራችንን ማኖር ብለን እየሰራን ነው፣

👉 ባለፉት አምስት ዓመታት 25 ቢልዮን ችግኞችን ተክለናል፣

👉 ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ/ም ጀንበር ወጥታ እስክትገባ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ቤቱ አይውልም፤ በዕቅፍ ካለ ሕጻን፣ በድካም ካለ አረጋዊ፣ በአልጋ ከሚገኝ ታማሚ በስተቀር ቤቱ ማንም አይውልም፣

👉 ምክንያቱም ይህ የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም፤ የፓርቲ ፕሮግራምም አይደለም፤ የመንግሥት ጉዳይም አይደለም፤ ይህ የኢትዮጵያ ጉዳይ ነው፣

👉 አረንጓዴ ዐሻራ አሁን ያለው ትውልድ የትናንት ዕዳውን ይከፍልበታል፤

👉 በደን ተሸፍና የኖረች ሀገር ዛሬ ራቁቷን እንድትሆን ያደረግናት እኛ ነን፣ ከተከልነው የቆረጥነው በልጧል፣ የትናንቱ ደን በታሪክ መዛግብት ላይ ብቻ የሚገኝ ሆኗል፡፡ ዐረንጓዴ ዐሻራ ይሄንን የቀደምቶቻችን ዕዳ እንድንከፍል ያደርጋል፣

👉 አረንጓዴ ዐሻራ ለነገ ትውልድ ወረት ነው፡፡ የምናስረክባት ሀገር በሁለንተናዋ ሉዓላዊነቷ የተጠበቀ መሆን አለበት፣

👉 የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የዲፕሎማሲ፣ የማኅበራዊ ኑሮ፣ የተፈጥሮ ሉዓላዊነቶቿ ተሟልተው መከበር አለባቸው፣

👉 ስድስት በር ያለው ቤት አንዱን ከፍቶ እስከዋለ ድረስ የሌሎቹ በሮች መዘጋት ደኅንነቱን አያስጠብቅለትም፤ የሀገር ሉዓላዊነትም በሁለንተናዊ መስኮች እስካልተጠበቀ ድረስ በተከፈተው በር የሚገባው ብዙ ነው፣

👉 ታዳሽ ኃይልን የኢነርጂ ዋና ምንጭ ለማድረግ ቆርጠን ለተነሣን ሕዝቦች፤ አረንጓዴ ዐሻራ እንደ ዐድዋ ዘመቻ የሉዓላዊነታችን ማስጠበቂያችን ነው፣

👉 የእምነትና የባህል፣ የፖለቲካ ፓርቲና አስተሳሰብ፣ እድሜና ጾታ፣ የትምህርትና የኑሮ ደረጃ ሳይለየን ሐምሌ 10 ቀን ከጀንበር ቀድመን እንውጣ፤ ከጀንበር በኋላ እንመለሳን፤ ኢትዮጵያን አረንጓዴ እናለብሳለን፡፡

👉 በኢትዮጵያ የምትኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች፣ ኤምባሲዎች፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሠራተኞች፣ በኢትዮጵያ በኩል የምታልፉ መንገደኞች፣ ለተለያየ ጉዳይ በአጋጣሚ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችሁ የውጭ ሀገር ሰዎች ሐምሌ 10 ቀን አረንጓዴ ዐሻራችሁን አኑሩ፣

👉 ዓለምን በኢትዮጵያ በኩል አልብሱ፤ኢትዮጵያ ታሪክ ስትሰራ የታሪኩ አካል ሁኑ፣

👉 ኢትዮጵያ ዓመቱን ሙሉ አረንጓዴ እስክትለብስ ድረስ መትከላችንን እንቀጥላለን፣