Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የሀረሪ ክልል የወረዳ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች የዓባይ ግድብን ጎበኙ
***
****
(ኢ ፕ ድ)

የሀረሪ ክልል የወረዳ ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች በጉባ እየተገነባ የሚገኘውን የዓባይ ግድብ ሂደትና አሁናዊ ገጽታን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው የኢትዮጵያዊያን አሻራ ያረፈበትን ግድብ የመጎብኘት እድል በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

በጉብኝቱ ላይ የሀረሪ ክልል ምከር ቤት የህዝብ ግኑኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ዋቁማ እንዳሉት የዓባይ ግድብ በኢትዮጵያዊያን ትብብር እና አንድነት በመገንባት ላይ ያለ የጋራ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።

የግድቡን ገጽታና ስራ በቦታው ተገኝተው በመጎብኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ለሀገር ብልጽግና፣ አንድነትና ልማት መሰረት የሆነው የግድቡ ግንባታ በስኬት እንዲጠናቀቅ የሁሉም ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

ሐምሌ 1ቀን2015ዓ.ም
500 ሚልዮን ችግኞች በአንድ ጀንበር‼️
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች‼️

👉 ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በአንድ ጀንበር 500 ሚልዮን ችግኝ እንተክላለን፤ ዳግም ታሪክ እንስራ፣

👉 ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ/ም በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ታሪክ እንድንሰራ ጥሪ አቀርባለሁ፣

👉 ሐምሌ 10 ቀን ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ሪከርድ እንሰብራለን፤

👉 ከዚህ በፊት ከ350 ሚልዮን በላይ ዛፎች በአንድ ጀንበር ተክለን ዓለምን ጉድ አስብለናል፣

👉 ዘንድሮ 500 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር በመትከል የራሳችንን ሪከርድ እናሻሽላለን፣

👉 ዘንድሮም 6 ነጥብ 5 ቢልዮን ችግኝ ለመትከል በየክልሉ፣ በየዞኑና በየወረዳው ክረምቱን ከምንሠራቸው ሥራዎች አንዱ አረንጓዴ ዐሻራችንን ማኖር ብለን እየሰራን ነው፣

👉 ባለፉት አምስት ዓመታት 25 ቢልዮን ችግኞችን ተክለናል፣

👉 ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ/ም ጀንበር ወጥታ እስክትገባ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ቤቱ አይውልም፤ በዕቅፍ ካለ ሕጻን፣ በድካም ካለ አረጋዊ፣ በአልጋ ከሚገኝ ታማሚ በስተቀር ቤቱ ማንም አይውልም፣

👉 ምክንያቱም ይህ የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም፤ የፓርቲ ፕሮግራምም አይደለም፤ የመንግሥት ጉዳይም አይደለም፤ ይህ የኢትዮጵያ ጉዳይ ነው፣

👉 አረንጓዴ ዐሻራ አሁን ያለው ትውልድ የትናንት ዕዳውን ይከፍልበታል፤

👉 በደን ተሸፍና የኖረች ሀገር ዛሬ ራቁቷን እንድትሆን ያደረግናት እኛ ነን፣ ከተከልነው የቆረጥነው በልጧል፣ የትናንቱ ደን በታሪክ መዛግብት ላይ ብቻ የሚገኝ ሆኗል፡፡ ዐረንጓዴ ዐሻራ ይሄንን የቀደምቶቻችን ዕዳ እንድንከፍል ያደርጋል፣

👉 አረንጓዴ ዐሻራ ለነገ ትውልድ ወረት ነው፡፡ የምናስረክባት ሀገር በሁለንተናዋ ሉዓላዊነቷ የተጠበቀ መሆን አለበት፣

👉 የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የዲፕሎማሲ፣ የማኅበራዊ ኑሮ፣ የተፈጥሮ ሉዓላዊነቶቿ ተሟልተው መከበር አለባቸው፣

👉 ስድስት በር ያለው ቤት አንዱን ከፍቶ እስከዋለ ድረስ የሌሎቹ በሮች መዘጋት ደኅንነቱን አያስጠብቅለትም፤ የሀገር ሉዓላዊነትም በሁለንተናዊ መስኮች እስካልተጠበቀ ድረስ በተከፈተው በር የሚገባው ብዙ ነው፣

👉 ታዳሽ ኃይልን የኢነርጂ ዋና ምንጭ ለማድረግ ቆርጠን ለተነሣን ሕዝቦች፤ አረንጓዴ ዐሻራ እንደ ዐድዋ ዘመቻ የሉዓላዊነታችን ማስጠበቂያችን ነው፣

👉 የእምነትና የባህል፣ የፖለቲካ ፓርቲና አስተሳሰብ፣ እድሜና ጾታ፣ የትምህርትና የኑሮ ደረጃ ሳይለየን ሐምሌ 10 ቀን ከጀንበር ቀድመን እንውጣ፤ ከጀንበር በኋላ እንመለሳን፤ ኢትዮጵያን አረንጓዴ እናለብሳለን፡፡

👉 በኢትዮጵያ የምትኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች፣ ኤምባሲዎች፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሠራተኞች፣ በኢትዮጵያ በኩል የምታልፉ መንገደኞች፣ ለተለያየ ጉዳይ በአጋጣሚ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችሁ የውጭ ሀገር ሰዎች ሐምሌ 10 ቀን አረንጓዴ ዐሻራችሁን አኑሩ፣

👉 ዓለምን በኢትዮጵያ በኩል አልብሱ፤ኢትዮጵያ ታሪክ ስትሰራ የታሪኩ አካል ሁኑ፣

👉 ኢትዮጵያ ዓመቱን ሙሉ አረንጓዴ እስክትለብስ ድረስ መትከላችንን እንቀጥላለን፣
500 ሚልዮን ችግኞች በአንድ ጀንበር እንተክላለን አረንጓዴ ዐሻራችንን እናሳርፋለን‼️
መልካም ዕድል፤ ሐምሌ 2 ቀን 2015 ዓ.ም‼️