Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በአቶ አህመድ ሽዴ የተመራ የልዑካን ቡድን በባህርዳር ከተማ ያለውን የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት የስራ እንቅስቃሴ ተመለከተ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
በአቶ አህመድ ሽዴ የተመራ የልዑካን ቡድን በባህርዳር ከተማ ያለውን የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት የስራ እንቅስቃሴ ተመለከተ።

ልዑኩ በከተማ አስተዳደሩም ሆነ በአለም ባንክ በጀት እየተገነቡ ያሉ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችንና በግለሠቦች እየተሠሩ ያሉ "የሌማት ቱሩፋት"ስራዎች የሆኑትን የበሬ ማድለብ ፣የዶሮ እርባታ እና እንቁላል ምርት ፣የወተት ልማት ፣የማርና መሰል የእንስሳት ሀብት ልማቶችን ተመልክቷል።

ልዑኩ ሌላው በጉብኝቱ በከተማው ኢንዱስትሪ መንደር ካሉ ፋብርካዎች መካከል የጌታሰው አያሌው ቶፕ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ፣የሻምበል መንገሻ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ ፣ ሙሌ የእንስሳት መኖ ማቀናበሪያ ፋብሪካን፣የቢአይካ የግራናይትና እምነ-በረድ ፋብሪካዎችን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝቷል።

በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶችንና የስራ ዕድል የተፈጠረላቸውን ሰራተኞች የማበረታታት ተግባር ማከናወኑንም ከከተማዋ ኮምንኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓም
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት !!

የከተማችንን የክረምት ስራዎች አፈፃፀም ለመመልከት እና ለመደገፍ ከፌዴራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች የሱፐርቪዢን ቡድን ጋር ውይይት ጀምረናል፡፡

ቡድኑ ለተከታታይ 10 ቀናት ወደ ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች ወርዶ የሱፐርቪዢን ስራ ያካሂዳል።

የሰራናቸው ስራዎች ብዙ፣ የሔድንበት ርቀት ረጅም ቢሆንም በከተማችን ለዓመታት የተከማቹ ችግሮችን መፍታት ከፍተኛ ጥረት እና በርካታ ትብብርን የሚጠይቅ በመሆኑ፣ የፌደራል መንግስት ክትትልና ድጋፍ ማድረጉ ተገቢ እና አስፈላጊ ነው።

እየፈጠርንና እየፈጠንን አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ፤ ለኑሮና ለስራ ምቹ ከተማ ለማድረግ በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን!
#አረንጓዴ_ዐሻራ‼️
ይህ የኢትዮጵያ ጉዳይ ነው‼️
በአፋር ክልል ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ አገልግሎት ተመለሰ
***************
(ኢ ፕ ድ)
በአፋር ክልል ሠመራ፣ ሎጊያ፣ ሚሌ፣ ኤሊውሀ፣ አዳይቱ ከተሞችና በአካባቢያቸው በተነሳ ከባድ ነፋስ ተቋርጦ የነበረው የሃይል አቅርቦት ዛሬ ወደ መደበኛ አገልግሎቱ ተመልሷል::

አገልግሎቱ ወደ መደበኛ አገልግሎቱ የተመለሰው የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተጎዱትን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች በፍጥነት በመጠገናቸው መሆኑን አገልግሎቱ አስታውቋል።

በአፋር ክልል ሠመራ፣ ሎጊያ፣ ሚሌ፣ ኤሊውሀ፣ አዳይቱ ከተሞች በተነሳ ከባድ ነፋስ በኤሌክትሪክ ምሰሶዎች እና ማሰራጫ መስመሮች ላይ ጉዳት መድረሱን መገለጹ ተጠቅሷል።

ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግም ተከራይ ማስወጣትም እንደማይቻል አስተዳደሩ አስታወቀ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በአዲስ አበባ በግል ከሚደረግ ስምምነት ውጪ ማንኛውም አከራይ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ እንዲሁም ተከራይ ማስወጣት እንደማይቻል አስተዳደሩ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የኑሮ ውድነቱ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማችን ነዋሪዎች ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ የቤት ኪራይ ጭማሪ እንዳይደረግ በተለያዩ ተከታታይ ጊዜያት ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል::

አሁንም በግል ከሚደረግ ስምምነት ውጪ ማንኛውም አከራይ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ እንዲሁም ተከራይ ማስወጣት የማይቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም
#አረንጓዴ_ዐሻራ‼️
ይህ የኢትዮጵያ ጉዳይ ነው‼️