Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በአዲስ አበባ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግም ተከራይ ማስወጣትም እንደማይቻል አስተዳደሩ አስታወቀ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በአዲስ አበባ በግል ከሚደረግ ስምምነት ውጪ ማንኛውም አከራይ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ እንዲሁም ተከራይ ማስወጣት እንደማይቻል አስተዳደሩ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የኑሮ ውድነቱ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማችን ነዋሪዎች ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ የቤት ኪራይ ጭማሪ እንዳይደረግ በተለያዩ ተከታታይ ጊዜያት ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል::

አሁንም በግል ከሚደረግ ስምምነት ውጪ ማንኛውም አከራይ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ እንዲሁም ተከራይ ማስወጣት የማይቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም
#አረንጓዴ_ዐሻራ‼️
ይህ የኢትዮጵያ ጉዳይ ነው‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አካሄደ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት ከአቃቂ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን ለአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አምስት ሺህ ችግኞች ተከለ።

"ነገን ዛሬ እንትከል" በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የ2015 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ጽ/ቤቱ ከ50ሺህ በላይ ችግኞችን ለክፍለከተማው ያበረከተ ሲሆን በዛሬው እለትም አምስት ሺህ ችግኞች ተተክለዋል።

በመርሀግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ደቦ ቱንካ እንደገለፁት፤ ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ከተማዋ ያላትን 15 በመቶ የደን ሽፋን ወደ 30 በመቶ ለማሳደግ የሚረዳ ነው።

ጽ/ቤቱ ከሚያከናውነው የአካባቢ ልማት የማሳደግ ተግባር በተጨማሪ ሀገራዊ በሆነው መርሀግብር በመሳተፍና ችግኞችን ከመትከል ባለፈ የመንከባከብ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በመርሀግብሩ የአዲስ አበባ የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣ የአቃቂ ክ/ከተማ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

በማህሌት ብዙነህ

ሐምሌ 4 ቀን 2015 ዓ.ም
በአዲስ አበባ እስካሁን ከአራት ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል

👉ኅብረተሰቡ በችግኝ ተከላ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል
*********************
(ኢ.ፕ.ድ)
በቅርቡ በተጀመረው የሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ በአዲስ አበባ እስካሁን ከአራት ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተካላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ አስታወቀ::

የከተማው ነዋሪ በአረጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እያሳየ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርበትም ተመልክቷል::
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=588664780123648&id=100069403920568
የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣናን በመጠቀም የሥራ ዕድልን ማስፋፋት ይገባል
*******************
(ኢ.ፕ.ድ)

ኢንተርፕራይዞች የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ገበያን በመጠቀም የሥራ ዕድል ፈጠራቸውን ማስፋፋት እንደሚኖርባቸው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች፣ አገልግሎት ሰጪዎችና ኢንዱስትሪዎች የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣናን የገበያ አማራጭን በስፋት በመጠቀም የሥራ ዕድል ፈጠራቸውን ማጠናከር አለባቸው።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=588654936791299&id=100069403920568
የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዓመታዊ ክብረ በዓል እየተካሄደ ነው
**************
(ኢ ፕ ድ)

የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዓመታዊ ክብረ በዓል እና የእውቅና ሥነሥርዓት በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በበዓሉ አከባበር ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰን ጨምሮ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮችና መኮንኖች ተገኝተዋል፡፡

"ምንጊዜም ለመዘመን እና ለድል አድራጊነት እንዘጋጅ" በሚል መሪ ሐሳብ ነው በዓሉ እየተከበረ የሚገኘው፡፡

የበዓሉ አከባበር ለሕግ የበላይነት መከበር የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የሠራዊት አባላት መዘጋጀቱ ተመላክቷል፡፡

በአከባበሩ ላይ የዕዙን ሁለንተናዊ ገጽታ የሚያንጸባርቁ የተለያዩ ሁነቶች እንደሚስተናገዱ ይጠበቃል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

ሐምሌ 4 ቀን 2015 ዓ.ም
ከ40 ቀላል ባቡሮች አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት ግማሽ ያህሉ ብቻ ናቸው
*********************
(ኢ.ፕ.ድ)
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከውጭ ካስገባቸው 40 ባቡሮች በአሁኑ ጊዜ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት ግማሽ ያህሉ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ገለጸ፡፡

የግብዓትና የሰው ኃይል እጥረት ቀላል ባቡሩ በሙሉ አቅሙ እንዳይሰራ እንቅፋት እንደፈጠሩበት ተመላክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወርቁ ደስታ ለኢፕድ እንደገለጹት፤በመጀመሪያ ወደ አገር ውስጥ ከገቡት 40 ባቡሮች መካከል በአሁኑ ጊዜ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት ግማሽ የሚሆኑት ብቻ ናቸው፡፡ ቀላል ባቡሮቹ ሥራ ማቆም ዋነኛው ምክንያትም የመለዋወጫ ግብዓት እጥረትና ጥገና የሚያካሂድ የተማረ የሰው ኃይል በሀገር ውስጥ ያለመኖሩ ነው፡፡
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=588649283458531&id=100069403920568
“የቀጣናውን የሠላም ተግዳሮት በራስ አቅም ለመፍታት የተጠባባቂ ኃይሉ አባል ሀገራት ከፍተኛ ተነሳሽነት አላቸው” -ብርጋዴር ጀነራል ጌታቸው አሊ የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል አዛዥ
********************
(ኢ.ፕ.ድ)
የምሥራቅ አፍሪካን የሠላም ተግዳሮት በራስ አቅም ለመፍታት የተጠባባቂ ኃይሉ አባል ሀገራት ከፍተኛ ተነሳሽነት እንዳላቸው የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል አዛዥ ገለጹ፡፡ የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል የተልዕኮ ድጋፍ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

የተጠባባቂ ኃይሉ አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ጌታቸው አሊ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የምስራቅ አፍሪካን የሠላም ተግዳሮት በራስ ለመፍታት የተጠባበቂ ኃይሉ አባል ሀገራት ቁርጠኝነት አዎንታዊ ሚና ያለው ነው፡፡ ይህንን ለማሳካት አባል ሀገራቱ ከፍተኛ ተነሳሽነት አላቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜም አባል ሀገራት የሚያዋጡትን ሠራዊት ለመምራትና በግዳጅ ቀጣና ላይ ተልዕኮን በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=588645860125540&id=100069403920568