የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አካሄደ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት ከአቃቂ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን ለአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አምስት ሺህ ችግኞች ተከለ።
"ነገን ዛሬ እንትከል" በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የ2015 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ጽ/ቤቱ ከ50ሺህ በላይ ችግኞችን ለክፍለከተማው ያበረከተ ሲሆን በዛሬው እለትም አምስት ሺህ ችግኞች ተተክለዋል።
በመርሀግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ደቦ ቱንካ እንደገለፁት፤ ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ከተማዋ ያላትን 15 በመቶ የደን ሽፋን ወደ 30 በመቶ ለማሳደግ የሚረዳ ነው።
ጽ/ቤቱ ከሚያከናውነው የአካባቢ ልማት የማሳደግ ተግባር በተጨማሪ ሀገራዊ በሆነው መርሀግብር በመሳተፍና ችግኞችን ከመትከል ባለፈ የመንከባከብ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በመርሀግብሩ የአዲስ አበባ የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣ የአቃቂ ክ/ከተማ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
በማህሌት ብዙነህ
ሐምሌ 4 ቀን 2015 ዓ.ም

በአዲስ አበባ እስካሁን ከአራት ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል
👉ኅብረተሰቡ በችግኝ ተከላ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል
*********************
(ኢ.ፕ.ድ)
በቅርቡ በተጀመረው የሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ በአዲስ አበባ እስካሁን ከአራት ነጥብ አምስት ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተካላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ አስታወቀ::
የከተማው ነዋሪ በአረጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እያሳየ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርበትም ተመልክቷል::
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=588664780123648&id=100069403920568

የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣናን በመጠቀም የሥራ ዕድልን ማስፋፋት ይገባል
*******************
(ኢ.ፕ.ድ)
ኢንተርፕራይዞች የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ገበያን በመጠቀም የሥራ ዕድል ፈጠራቸውን ማስፋፋት እንደሚኖርባቸው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች፣ አገልግሎት ሰጪዎችና ኢንዱስትሪዎች የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣናን የገበያ አማራጭን በስፋት በመጠቀም የሥራ ዕድል ፈጠራቸውን ማጠናከር አለባቸው።
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=588654936791299&id=100069403920568

የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዓመታዊ ክብረ በዓል እየተካሄደ ነው
**************
(ኢ ፕ ድ)
የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዓመታዊ ክብረ በዓል እና የእውቅና ሥነሥርዓት በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በበዓሉ አከባበር ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰን ጨምሮ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮችና መኮንኖች ተገኝተዋል፡፡
"ምንጊዜም ለመዘመን እና ለድል አድራጊነት እንዘጋጅ" በሚል መሪ ሐሳብ ነው በዓሉ እየተከበረ የሚገኘው፡፡
የበዓሉ አከባበር ለሕግ የበላይነት መከበር የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የሠራዊት አባላት መዘጋጀቱ ተመላክቷል፡፡
በአከባበሩ ላይ የዕዙን ሁለንተናዊ ገጽታ የሚያንጸባርቁ የተለያዩ ሁነቶች እንደሚስተናገዱ ይጠበቃል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

ከ40 ቀላል ባቡሮች አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት ግማሽ ያህሉ ብቻ ናቸው
*********************
(ኢ.ፕ.ድ)
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከውጭ ካስገባቸው 40 ባቡሮች በአሁኑ ጊዜ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት ግማሽ ያህሉ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ገለጸ፡፡
የግብዓትና የሰው ኃይል እጥረት ቀላል ባቡሩ በሙሉ አቅሙ እንዳይሰራ እንቅፋት እንደፈጠሩበት ተመላክቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወርቁ ደስታ ለኢፕድ እንደገለጹት፤በመጀመሪያ ወደ አገር ውስጥ ከገቡት 40 ባቡሮች መካከል በአሁኑ ጊዜ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት ግማሽ የሚሆኑት ብቻ ናቸው፡፡ ቀላል ባቡሮቹ ሥራ ማቆም ዋነኛው ምክንያትም የመለዋወጫ ግብዓት እጥረትና ጥገና የሚያካሂድ የተማረ የሰው ኃይል በሀገር ውስጥ ያለመኖሩ ነው፡፡
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=588649283458531&id=100069403920568

“የቀጣናውን የሠላም ተግዳሮት በራስ አቅም ለመፍታት የተጠባባቂ ኃይሉ አባል ሀገራት ከፍተኛ ተነሳሽነት አላቸው” -ብርጋዴር ጀነራል ጌታቸው አሊ የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል አዛዥ
********************
(ኢ.ፕ.ድ)
የምሥራቅ አፍሪካን የሠላም ተግዳሮት በራስ አቅም ለመፍታት የተጠባባቂ ኃይሉ አባል ሀገራት ከፍተኛ ተነሳሽነት እንዳላቸው የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል አዛዥ ገለጹ፡፡ የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል የተልዕኮ ድጋፍ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡
የተጠባባቂ ኃይሉ አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ጌታቸው አሊ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የምስራቅ አፍሪካን የሠላም ተግዳሮት በራስ ለመፍታት የተጠባበቂ ኃይሉ አባል ሀገራት ቁርጠኝነት አዎንታዊ ሚና ያለው ነው፡፡ ይህንን ለማሳካት አባል ሀገራቱ ከፍተኛ ተነሳሽነት አላቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜም አባል ሀገራት የሚያዋጡትን ሠራዊት ለመምራትና በግዳጅ ቀጣና ላይ ተልዕኮን በአግባቡ ለመወጣት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=588645860125540&id=100069403920568

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በ2016 በጀት ዓመት ከ140 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዷል
*****
(ኢ.ፕ.ድ)
- ቢሮው በ2015 በጀት ዓመት ከ107 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰብስቧል
የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ የ2015 በጀት ዓመት የገቢ ዕቅድ ማጠቃለያ እና የ2016 በጀት ዓመት የግብር ማሳወቂያ የንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በዛሬው እለት አካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ በመርሃ ግብሩ እንደተናገሩት፤ ቢሮው በ2015 በጀት ዓመት ከገቢዎች ቢሮ ፣ ከማዕከል ገቢ ሰብሳቢ ሴክተሮች፣ ከክፍለ ከተሞች እና ከሌሎች ገቢዎች ጨምሮ በጥቅሉ ከ107 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል።
የተሰበሰበው ገቢ ከ2014 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ53 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
ይህም በገንዘብ 37 ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር መሆኑን የገለፁት ኃላፊው፤ የተሰበሰበው ብር ለከተማዋ ዘላቂ የልማት ዘርፎች ማለትም ለትምህርት ቤት፣ ለተማሪዎች ምገባ እና ለትውልድ መተላለፍ ለሚችሉ ኘሮጀክቶች የሚውል ነው። ስለዚህ ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በሚቀጥለው በጀት ዓመት አጠናክረው ሊከፍሉ ይገባል ብለዋል።
በ2016 በጀት ዓመት ደግሞ ከ140 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዷል ያሉት አቶ አደም፤ ይህንን ገቢ እውን ለማድረግ አመራሩ በትኩረት የሚሰራ ሲሆን አሰራሩም በቴክኖሎጂ የሚደገፍ ይሆናል ብለዋል።
በ2015 በጀት ዓመት የነበሩ ተግዳሮቶች ማለትም ሀሰተኛ ደረሰኝ የሚጠቀሙ እና ከዋጋ በታች ደረሰኝ በሚቆርጡ ነጋዴዎች ላይ ከፍተኛ ትኩረት ይደረጋል። ህብረተሰቡም ግብር መክፈል ለሀገር ክብር መሆኑን ሊገነዘብ ይገባል ብለዋል።
በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት፤ በከተማዋ የግብር አሰባሰብ ሂደቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ቢመጣም በሚገባው እና መሰብሰብ ባለበት ልክ እየተሰበሰበ አይደለም።
መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እና የከተማዋን ገቢ በማሳደግ ውብ እና ሁለተናዊ እድገት ለማምጣት መተባበር ያስፈልጋል ብለዋል።
ከንቲባዋ በመርሃ ግብሩ በ2015 በጀት አመት ጠንካራ አፈፃፀም ለነበራቸው ሥራ አስፈፃሚዎች እውቅናና ሽልማት የሰጡ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ለ2016 በጀት አመት ጠንካራ ሥራ እንዲሰሩ የአደራ ሰርተፍኬት ሰጥተዋል።
ሐምሌ 4 ቀን 2015ዓ.ም
በሳሙኤል ወንደሰን