Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን በዘላቂነት ለማቋቋም የተገነባው የተቀናጀ የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል ተመረቀ
***********************
(ኢ ፕ ድ)

በአቃቂ ቃሊቲ ኮዬ ፈጬ ወረዳ 10 የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን በዘላቂነት ለማቋቋም የተገነባው የተቀናጀ የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመርቋል።

በምረቃ መርሐግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይና የከተማ አስተዳደሩ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አብዱልቃድር ጨምሮ የተለያዩ የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ማዕከሉ የዶሮና እንቁላል ማርቢያ የእንስሳት ማድለቢያንና የምርት ማሳያና መሸጫዎችን ጨምሮ አርሶ አደሩን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚረዱ የልማት ሥራዎች ይገኙበታል፡፡

በማርቆስ በላይ

ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም
በመዲናዋ ምዘና ከተደረገላቸው ትምህርት ቤቶች 240ዎቹ ከደረጃ በታች ናቸው

👉የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ከተማ አቀፍ ንቅናቄ ነገ ይጀመራል
***************************
(ኢ ፕ ድ)

ምዘና ከተደረገላቸው 526 የመንግሥት ትምህርት ቤቶች መካከል 240 ትምህርት ቤቶች ከደረጃ በታች መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። በመዲናዋ የትምህርት ቤቶችን የመጨረሻው የጥራት ደረጃ አራትን ያሟላ አንድም ትምህርት ቤት አለመኖሩ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዑመር ቢሮው ያከናወነውን ጥናት ....
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0yfXz1KQsihT2aUf2HC52q6LF82o2ZbV3hL2xghZjXehUgYETiyRc5mokxdgqa5AUl&id=100069403920568&mibextid=Nif5oz
እስራኤል ኤምባሲ አካባቢ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት ምክንያት መገናኛ አካባቢ መንገድ ስለተዘጋ በዚህ አካባቢ የምትጓዙ ሰዎች አማራጭ መንገድ እንድትጠቀሙ ሲል የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አሳስቧል‼️
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
******************
(ኢ ፕ ድ)

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከ43ኛው የአፍሪካ ኀብረት የስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ጎን ለጎን ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብሽር ኦማር ጃማ ጋር በሁለትዮሽና አከባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ዛሬ በተጀመረው 43ኛው የአፍሪካ ኀብረት የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሁለቱ አገሮች ወቅታዊ ወዳጅነትን በተመለከተ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በሁሉም መስኮች የተሳሰሩ በመሆናቸው በጋራ ጉዳዬች ተባብረው ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑክ ቡድን በ43ኛው የአፍሪካ ኀብረት የስራ አስፈፃሚ ምክርቤት ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐረር ከተማ ያስገነቡት የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ ሥራ ጀመረ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐረር ከተማ ያስገነቡትን 7ኛውን የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ ከሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሚስራ አብደላ ጋር በመሆን ስራ አስጀምረዋል።

ፋብሪካው በቀን 300 ሺ ዳቦና 420 ኩንታል ዱቄት ያመርታል።

በሶስት ፈረቃ ከ150 በላይ ሰዎች የስራ እድል የሚፈጥር መሆኑንም የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በቀጣይም በአምስት ከተሞች እየተገነቡ ያሉትን ፋብሪካወች ተጠናቀው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ግንባታቸው እየተፋጠነ ይገኛልም ብሏል፤ ጽህፈት ቤቱ።

ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም
#ኢፕድ_ድንቃድንቅ‼️
ታምረኛው ቤተሰብ ‼️

ከወደ ፓኪስታን “ተዓምር ነው” የተባለ ዜና ተሰምቷል፡፡ ዜናው ፓኪስታናዊያንን ብቻ አስገርሞ አልቀረም።

ይልቁንም ጉዳዩ እንግዳ ነገር በመሆኑም ጭምር በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይም “አጃኢብ” ተበሎ ሰፍሯል።

ነገሩ እንዲህ ነው። ጥንዶቹ በፓኪስታን ላርካና ነዋሪ ናቸው፡፡ ባልና ሚስቱ አሚር አሊና ከዲጃ ይባላሉ፡፡ የሁለቱም የልደት ቀን ተመሳሳይ ነው፤ እአአ ኦገስት አንድ፡፡

ጥንዶቹ ይህን ልዩ ቀን ታሪካዊ ለማድረግ አሰቡ፡፡ መላም ዘየዱ፡፡

አደረጉትም። በልደት ቀናቸው በአንድ ጣሪያ ስር ለመኖር ወስነው በጎርጎሮሳዊያኑ የጊዜ ቀመር ኦገስት 1 ቀን 1991 በልደት ቀናቸው ተጋቡ።

በተጋቡ ልክ በአንድ አመታቸው ቤታቸው በልጅ ተባረከ። በባልና ሚስቱ የልደት ቀንና የጋብቻ ቀን መመሳሰል የተጀመረው ግጥምጥሞሽ ወደ በኩር ልጃቸውም ተሻገረ።

ጥንዶቹ የመጀመሪያ ልጃቸውን በልደት ቀናቸው ወለዱ። ስሟንም ሲንዶ አሏት።
የጥንዶቹ ተዓምር የሚመስል ህይወት በዚህ አላበቃም፡፡

የአምላክ ድንቅ ስራ በዚህ ቤተሰብ ቀጥሎ፤ ጥንዶቹ ሁለት መንታ ሴት ልጆችን አሁንም በተመሳሳይ የልደት ቀናቸውን በሚያከብሩበት ኦገስት 1 ወለዱ። ተገረሙ፤ ብዙዎችንም አስደመሙ።

የቤተሰቡ ታምራት እንደቀጠለ ነው።
ባልና ሚስቱ ሌለ መንታ ወንድ ልጆችን አቅፈው ሳሙ። እነዚህ መንታ ወንድማማቾችም ይህችን ምድር የተቀላቀሉት እህቶቻቸው በተወለዱበት ወላጆቻቸው ደግሞ በተወለዱበትና በተጋቡበት ቀን መሆኑ ግርምቱን ከፍ አደረገው።

ጥንዶቹ በአምላክ ስራ እየተገረሙም እየተደነቁም የራሳቸውንና የአምስቱን ልጆቻቸውን ልደት በተመሳሳይ ቀን እያከበሩ ኑሯቸውን መግፋት ቀጠሉ።

የቤተሰቡ ታምር በዚህ እንዲቋጭ አልተፈለገምና ጥንዶቹ ዳግም ሁለት ሴት ልጆችን አከታትለው ወለዱ።

የሚገርመው ታዲያ ሁለቱም በተለያየ አመት ይወለዱ እንጂ የተወለዱበት ቀን ግን እንደ ቤተሰቡ ሁሉ ተመሳሳይ ነበር፤ ኦገስት 1።
ስለዚህ ጉዳይ ሲጠየቅ አባት አሚር አሊ ስለመደነቁና መደሰቱ ይናገራል፡፡

ባለቤቱ ከዲጃም ሁልጊዜ ድንቅና ስኬታማ ስለሆነው የወሊድ ታሪክ እንደምትደነቅ ተናግራለች። ባልና ሚስቱ ይሄን ጉዳይ ከፈጣሪ የተሰጠ ድንቅ ስጦታ አድርገው ተቀብለውታል፡፡

የአለም ድንቃድንቅ መዝገብም ገዳዩን ሰምቶ ብቻ ማለፍአልፈለገም። በዚህ ጉዳይ ላይ ከዚህ ቀደም የተመዘገበ ነገር እንዳለ መለስ ብሎ አጣራ።

ከእነዚህ ቤተሰቦች ቀድሞ አሜሪካውያን የአምስት ቤተሰብ አባላት ተመሳሳይ የልደት ቀን ኖሯቸው መዝገቡ ላይ ሰፍረው ተገኙ። ሆኖም ፓኪስታናዊያኑ ዘጠኝ በመሆናቸው በድንቃድንቅ መዝገቡ ላይ ከመስፈር ያገዳቸው አልነበረም።

አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ

https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓም
በዳግማዊት ግርማ