Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ ረፋድ ላይ በካይሮ በተካሄደው ‘የሱዳን ጎረቤት ሀገሮች ጉባዔ’ ላይ ተሳትፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በግብፅ የተካሄደውን የመሪዎች ጉባኤን ጨምሮ ሱዳን ለተፈጠረው ቀውስ እፎይታ ለማምጣት የተጀመሩ የተለያዩ ጥረቶችን እውቅና ሰተው በሱዳን ያለውን ግጭት ለመፍታት በኢጋድ መሪነት እና ከአፍሪካ ህብረት ድጋፍ ሰጪነት የተጀመረውን ነባር ውይይቶች ጋር ማጣጣም እንደሚያስፈልግ መግለፃቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት  ቤት አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው የግብፅ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።

ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ. ም
የኢትዮጵያ እና የግብጽ ግንኙነት ላይ በጋራ የተሰጠ መግለጫ‼️

ዛሬ ሐምሌ 6 ቀን 2015 ዓ.ም የአረብ ሪፐብሊክ ግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ተቀብለው አነጋግረዋል።

መሪዎቹ ባደረጉት ምክክር የሁለቱን ሃገራት ህዝቦች የጋራ ጥቅም ባስጠበቀና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የባህልና የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሻሻል ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

የመሪዎቹ ቁርጠኝነት በቀጠናው ሰላምና ደህንነትን ለማስፈንና መረጋጋትን ለማስጠበቅ ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ ባሻገር ሃገራቱ የሚያጋጥሟቸውን የጋራ ፈተናዎች ለመሻገርም ያስችላል።

ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ምክክር የታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድርን በተመለከተ በተከታዮቹ ሁለት ነጥቦች ላይ ተስማምተዋል፤

👉 የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትንና የአሰራር ደንቦችን በተመለከተ በግብፅ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል የሚካሄደውን ንግግር በፍጥነት ለማስጀመር እንዲሁም ንግግሩን በአራት ወራት ውስጥ አጠናቆ ከመግባባት ላይ ለመድረስ አስፈላጊውን ሁሉ ጥረት እንደሚያደርጉ ተስማምተዋል።

👉 ንግግሩ በሚካሄድበት ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ በ2015-2016 ዓ.ም የግድቡ የውሃ ሙሌት ወቅት ግብፅና ሱዳን ከወንዙ በሚያገኙት የውሃ አቅርቦት ላይ የጎላ ችግር እንዳያጋጥም ለማድረግ ኢትዮጵያ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጣለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ግብጽ በነበሩበት ወቅት አዲሱን ካይሮ ጎብኝተዋል‼️