ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በኢትዮጵያና በደቡብ አፍሪካ መካከል በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።
ስምምነቱን የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስቴር ተፈራረመዋል።
ስምምነቱ በአገራቱ በወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦች ተላልፈው እንዲሰጡ ማድረግ የሚያስችል ማእቀፍ መፍጠር የሚያስችል መሆኑን በፍትህ ሚኒስቴር የህግ ጉዳዮች አለም አቀፍ ትብብር ማእቀፍ ዳይሬክተር አቶ የሱፍ ጀማዎ ተናግረዋል።
በስምምነቱ የተቀመጡ በርካታ ቅድመ ሁኔታዎች አሉ ያሉት ዳይሬክተሩ፣ ቅድመ ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ተፈላጊዎቹ ተላልፈው ይሰጣሉ።
ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ከቱርክ፣ ከአረብ ኤምረቶች፣ ቻይና፣ ሩዋንዳ፣ ዩጋንዳና ከሱዳን ጋር ተመሳሳይ ምምነት አላት ብለዋል።
በሞገስ ጸጋዬ
ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ክልሉ ከጎብኚዎች አንድ ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ብር አግኝቷል
**********
(ኢ.ፕ.ድ)
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ክልሉን ከጎበኙ ቱሪስቶች አንድ ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር መገኘቱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ገለጸ።
የክልሉ የባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ2015 በጀት ዓመት ከጎብኚዎች በተለያየ መልኩ ሁለት ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ይሰበሰባል ተብሎ የታቀደ ሲሆን፤ አንድ ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሏል። ይህም የእቅዱን 70 በመቶ ያሳካ ነው።
በበጀት ዓመቱ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች ክልሉን መጎብኘታቸውን የሚናገሩት ኃላፊው፤ ቢሮዉ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን በማበረታታት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ አንድ ነጥብ 3 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ክልሉን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=105966

‹‹የመማሪያ መጻሕፍትን ወስደው ለተማሪዎቻቸው በማይሰጡ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ ርምጃ እንወስዳለን››
-ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ
********************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲሱ የትምህርት ዘመን ታትሞ የመጣን የመማሪያ መጽሐፍ ወስደው ለተማሪዎቻቸው በማይሰጡ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ርምጃ እንወስዳለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ አስታወቁ።
ዶክተር ዘላለም በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ ቢሮው ከመጽሐፍ ጋር በተያያዘ ከሌሎች ክልሎች በተሻለ ሁኔታ ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት መጻሕፍትን አትሞ ማቅረብ ከዶላር እጥረት የተነሳ ከባድ ነው። ብዙዎቹ ግብዓቶች የሚገቡት ከውጭ ሀገር ነው።
ነገር ግን እሱ የፈጠረው ጫና ቢኖርም ፈተናው ታልፎ ብዙ ጥረቶች በመደረጋቸው በርካታ የታተሙ መጻሕፍት አሉ። እነዚህን መጻሕፍት ወስደው ለተማሪዎቻቸው ለመስጠት መነሳሳቱ በሌላቸው የግል ትምህርት ቤቶች ላይ ርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን።
በመስኩ ያጋጠሙ ፈተናዎችን አልፈን ያሳተምናቸው መጻሕፍትን ተቀብለው ለተማሪዎቻቸው ከማድረስ አኳያ በግል ትምህርት ቤቶች አካባቢ አንዳንድ ችግሮች ይስተዋላሉ ያሉት ኃላፊው፤ እነዚህ ትምህርት ቤቶች ታትሞ የመጣን መጽሐፍት ወስደው ለተማሪዎች………
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=105943

በአፋር ክልል ከ120 በላይ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እየተሠራ ነው
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
በአፋር ክልል በትምህርት ቤቶች ደረጃ ማሻሻል ንቅናቄ 123 ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን ለማሻሻል እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለፀ፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱ ሐሰን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በክልሉ አንድ ሺህ 241 ትምህርት ቤቶች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል በኅብረተሰቡና በባለሀብቶች እገዛ የ123 ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እየተሠራ ነው፡፡
ንቅናቄው እንደ ሀገር የአምስት ዓመት ዕቅድ የተያዘለት መሆኑን የጠቀሱት አቶ አብዱ፤ በክልሉ ከሚገኙት 41 ወረዳዎች ከእያንዳንዳቸው ሦስት ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ የተቀመጠ ሲሆን፤ አጠቃላይ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=105970

አፍሪካ ዘላቂ ሰላም ማስፈን የሚችል ጠንካራ ወታደራዊ ኮማንድ ያስፈልጋታል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
አፍሪካ የ2063 አጀንዳን ለማሳካት ቅድሚያ አህጉራዊ ሰላሟን ማስጠበቅ የሚችል ጠንካራ የሆነ ወታደራዊ ኮማንድ እንደሚያስፈልጋት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ አቶ ሰለሞን ተፈራ ገለጹ።
አቶ ሰለሞን ተፈራ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አፍሪካ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መስተጋብሮችን አስተሳስሮ በመጠቀም ዕድገት ለማስመዝገብ ቅድሚያ ሰላምን ማስፈን ያስፈልጋታል።
ድህነት በመቅረፍ ብልጽግናን ለማምጣት ከውጭ ጣልቃ ገብነት ነጻ አህጉር መፍጠር ይገባል።
እንደ መምህሩ ገለጻ፤ የአፍሪካ ህብረት የተቋቋመበት ዋና አላማ አንዱ ሰላም የሰፈነባትና ድህነት የተቀረፈባት አህጉር....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=105957

የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር 3ነጥብ4 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘ
**************
(ኢ ፕ ድ)
በ2015 በጀት ዓመት የ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን የቢሾፍቱ የከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ በቀጣይ የከተማዋን ገቢ ለማሳደግ የቱሪስቶችን ቀልብ የሚስቡ ኢንቨስትመንቶች ላይ ከፍተኛ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁሟል፡፡
የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ የከተማ አስተዳደሩ የሚቀጥሉትን 10 ዓመታት ማዕከል ያደረገ ፍኖተ ካርታ ነድፎ እየሰራ ነው፡፡
ይህም በተለይ በገቢ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ ዕድገት እንዲያሳይ የተተለመ ነው፡ ፡ በዚህም በ2015 በጀት ዓመት አስተዳደሩ የ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ አግኝቷል፡፡
ከ10 ዓመቱ እቅድ ደግሞ የአምስት ዓመት ብሎም የበጀት ዓመቱ እቅድ ተነድፎ ሲሰራ የቆየ ሲሆን፤ ስኬታማ ተግባራትን ማከናወን ተችሏል ያሉት አቶ አለማየሁ፤ በ2015 በጀት ዓመት የከተማ አስተዳደሩ፤ 3ነጥብ4 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱ ስኬታማ አድርጎታል…………
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=105975

የሀይድሮጅን ፐርኦክሳይድ አቅርቦትን በሀገር ውስጥ ምርት ማሟላት ተችሏል
**************
(ኢ ፕ ድ)
በ2015 በጀት ዓመት ከ722 ቶን በላይ የሀይድሮጅን ፐርኦክሳይድ በማምረት የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ሙሉ ለሙሉ መሸፈን መቻሉን የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ አስታወቀ።
የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አህመድ ሞቱማ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ሀይድሮጅን ፐርኦክሳይድ ጨርቃ ጨርቅ ለማቅለም ፣ለግብርና ለአበባ እርሻ፣ ለሳኒታይዘር ምትርትና ለሌሎች ፋብሪካዎች ግብአትነት ያገለግላል።
በበጀት ዓመቱ ከ722 ቶን በላይ የሀይድሮጅን ፐርኦክሳይድ በማምረት የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ሙሉ ለሙሉ መሸፈን ተችሏል።
እስከ ቅርብ ጊዜ የዚህ ምርት የሀገር ውስጥ የፍላጎት መጠን 650 ቶን እንደነበር አውስተው፤ በተያዘው በጀት ዓመት ከ722 ቶን በላይ ማምረት በመቻሉ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ሙሉ ለሙሉ መሸፈኑን ተናግረዋል።
ፋብሪካው በአሁኑ ወቅት ያለው የማምረት አቅም በአንድ ኮምፕረሰር አንድ ሺ 500 ቶን እንደሆነ የተናገሩት ሥራ አስኪያጁ፤ ፋብሪካው ባሉት ሦስት ኮምፐረሰሮች ማምረት ሲጀምር አምስት ሺ 500 ቶን እንደሚደርስ ገልጸዋል።
ይህም በቀጣይ እየጨመረ የሚመጣውን የሀገር ውስጥ ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል ይሆናል ያሉት አቶ አህመድ፤ እስካሁን በሙሉ …..
ሙሉውን ለማንበበ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=105947

የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ከሶስት ነጥብ ሁለት ቢሊየን ብር በላይ የዳኝነት ዉሳኔዎችን ማስተላለፉን ገለጸ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በተጠናቀቀው በጀት አመት ከሶስት ነጥብ ሁለት ቢሊየን ብር በላይ የዳኝነት ዉሳኔዎችን ማስተላለፉን ገለጸ።
በ2015ዓ.ም ሂደቶችን አልፈዉ ከቀረቡ 991 መዝገቦች ዉስጥ ሶስት ነጥብ ሁለት ቢሊየን ብር ለያዙ 674 መዝገቦች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓም ድረስ ዉሳኔ መስጠት መቻሉን የኮሚሽኑ ፕሬዚደንት አቶ ሙሉጌታ አያሌዉ አስታውቀዋል።
የኮመሽኑ አመታዊ አፈጻጸሙም 99 ነጥብ ሰባት በመቶ መሆኑን ገልጸዋል። የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ከ2011ዓ.ም ጀምሮ ቅሬታዎችን እየተቀበለ ከ14.4 ቢሊየን ብር በላይ የዳኝነት ዉሳኔዎችን አስተላልፏል።
እንደ አቶ ሙሉጌታ ገለጻ፤ በዉሳኔ ሀሳቡ መሰረትም ለመንግስት የሚጸናዉ እንዳለ ሆኖ ለባለጉዳዩ የሚመለሰዉ ደግሞ ተመላሽ ይሆናል።
የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በገቢዎች እና ጉምሩክ ቅሬታ ያላቸዉ ሰዎች መጀመሪያ ቅሬታቸዉን በተቋሙ አቅርበዉ ተቋሙ ምላሽ ካልሰጣቸዉ በይግባኝ ቅሬታቸዉን ተቀብሎ ዉሳኔ እንዲሰጥ በ2010ዓ.ም መጨረሻ ተቋቁሞ በ2011ዓ.ም ስራ የጀመረ ተቋም እንደሆነ ይታወሳል።
በመዓዛ ማሞ
ሐምሌ24 ቀን 2015 ዓም

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በስሙ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተጠቀሙ ግለሰቦችን ይፋ አደረገ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ ተቋማት በቀረበለት የተማሪዎች የትምህርት ማስረጃ ይጣራልን ጥያቄ መሰረት የደረሰበትንና ሀሰተኛ ናቸው ያላቸውን ሰነዶችና ግለሰቦች ስም ይፋ አድርጓል።
የዩኒቨርሲቲው እንዳስታወቀው፤ በ2015 ዓ/ም የቀረቡ የትምህርት ማስረጃ ማጣራት ጥያቄዎችን ተከትሎ በተደረገ የማጣራት ሂደት ከአንዳንድ ተቋማት የቀረቡ የዩኒቨርሲቲው ምሩቃን የትምህርት ማስረጃዎች በዩኒቨርሲቲው በተሰጣቸው የተማሪ ውጤት ኮፒ ላይ የአጠቃላይ ነጥብ ለውጥ የተደረገባቸው እንዲሁም ፈጽሞ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ያልተማሩባቸው ሐሰተኛ ዲግሪ ማስረጃዎች ሆነው የተገኙ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
መሰል ኃላፊነት የጎደላቸው ተግባራት እንዳይበረታቱ ብሎም ሕዝብና መንግሥት ሙያዊ ብቃት በሌላቸውና ኃላፊነት በጎደላቸው ዜጎች ለጉዳት እንዳይጋለጥ በማሰብ በዩኒቨርሲቲው የትምህርት ማስረጃ ላይ የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ በማስመሰልና በመቀየር እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ስምና ሎጎ ያልተማሩበትን ዲግሪ ይዘው የማጭበርበር ተግባር ላይ የተሠማሩ ግለሰቦች መኖራቸወን አረጋግጫለሁም ብሏል።
ወደ ፊትም በዚህ ተግባር የሚሠማሩ ቢኖሩ ለሕዝብ የማጋለጥ ሥራ በተከታታይነት እንዲሠራ ዩኒቨርሲቲው መወሰኑንመ ገልጿል።
ከታች በቀረበው ዝርዝር መሰረት የሐሰተኛ ማስረጃ ማጣራት ሪፖርት ላይ ስማቸው የተጠቀሱ ግለሰቦች በእነዚህ የትምህርት ማስረጃዎች በየትኛውም ተቋም ቢቀጠሩ ማስረጃዎቻቸው ሕጋዊነት የሌላቸው መሆኑንም ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።
ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓም

"በሁለተኛው የሩስያ-አፍሪካ ጉባዔ ኢትዮጵያ በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ስኬታማ ሥራዎችን አከናውናለች"
- ሰላማዊት ካሣ የመንግሥት ኮሙኒኬሸን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በሁለተኛው የሩስያ-አፍሪካ ጉባዔ ኢትዮጵያ በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ስኬታማ ሥራዎችን ማከናወኗን የመንግሥት ኮሙኒኬሸን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሣ ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሀገራቱን የፖለቲካና የባህል ዲፕሎማሲ በኢኮኖሚው መስክ ማጠናከር እንደሚገባ የጋራ አቋም አንጸባርቀዋልም ብለዋል።
የመንግሥት ኮሙኒኬሸን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሣ፤ በማብራሪያቸው የሩስያ-አፍሪካ የኢኮኖሚና የሰብዓዊነት ጉባዔ ኢትዮጵያ በልማት ሥራዎች ያስመዘገበቻቸውን ተጨባጭ ውጤቶች ያስተዋወቀችበት መሆኑንም አንስተዋል።
አፍሪካውያን በምግብ ራሳቸውን ለመቻል የሚያደርጉትን ጥረት ሩስያ በቴክኖሎጂ ግብዓት እንድታግዝ ጥሪ ያቀረበችበትና የዘርፉ ተቋማት የሁለትዮሽ ስምምነቶችን የተፈራረሙበት ነው ብለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ በሩስያ ቆይታው ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ስኬታማ ውይይት ማድረጉንና ወደ ተግባር የሚቀየሩ ስምምነቶችን መፈራረሙንም ጠቅሰዋል።
በሁለቱ መሪዎች ውይይት ኢትዮጵያ በተለይም በምግብ ራሷን ለመቻል በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ተምሳሌታዊ ተግባር እያከናወነች መሆኑም ተነስቷል ብለዋል።
ለ125 ዓመታት የዘለቀውን የሁለቱን አገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት በኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መስኮች ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችሉ ጉዳዮችም የውይይቱ አካል ነበሩ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ።
ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በልማት መስክ በተለይም በግብርናው ዘርፍ ላደረገችው ስኬታማ እንቅስቃሴ የሩስያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አድንቀዋል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት ሩስያ በቴክኖሎጂ፣ በኢንቨስትመንትና በግብዓት የመደገፍ ፍላጎት ያላት መሆኑን አረጋግጣለች።
በጉባዔው የኢትዮጵያን የተለያዩ ተቋማት የወከሉ አመራሮች ከሩስያ አቻዎቻቸው ጋር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር የሚያስችሉ ውይይቶች ማድረጋቸውንም ተናግረዋል።
ለአብነትም የሰላምና ፀጥታ፣ የቴክኖሎጂ፣ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ትብብርን ማጠናከር ስለሚቻልባቸው ጉዳዮች መምከራቸውን በመጠቆም።
የሁለቱን አገራት ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት በኢኮኖሚውም ከፍ ወዳለ ደረጃ ማሸጋገር የሚችሉ ስምምነቶች መፈረማቸውን ነው ሚኒስትር ዴኤታዋ ያነሱት።
የንግድ ትስስራቸውን ለማጠናከር እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን መፍታት የሚያስችል የጉምሩክ አገልግሎት ትብብር፣ በኢትዮጵያ የባዮሎጂካል ሳይንስ ምርምር ማዕከል ለማቋቋም፣ የአየር ትራንስፖርት ትብብርና የኒዩክሌር ኃይልን ለሰላማዊ አገልግሎት ማዋል የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ስምምነት መደረጉንም ጠቅሰዋል።
በአፍሪካ የኢንዱስትሪ ሂደቶችን ለማጠናከር ሩስያ እንድታግዝ ኢትዮጵያ ጥሪ ማቅረቧን አስታውሰው በአፍሪካና ሩስያ መካከል ያለውን የንግድ ትስስር እንቅፋቶችን ለመፍታት በጋራ መስራት እንደሚገባ በጉባኤው ተመላክቷል ነው ያሉት።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም የነዳጅ ዋጋ መናርንና የግብርና ግብዓት ችግሮችን ለመፍታት ሩስያ ከአፍሪካ ጋር አበክራ እንድትሰራ ጥሪ መቅረቡን አንስተዋል።
አፍሪካ የተፈጥሮ ኃብቷን እሴት ጨምራ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የምታደርገውን ጥረት የሩስያ እገዛ ወሳኝ መሆኑ መነሳቱን በማስታወስ ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የሩስያ አፍሪካ ጉባዔ ለማስተናገድ ጥያቄ ማቅረቧንም ሚኒስትር ዴኤታዋ ጠቁመዋል።
ሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ የኢኮኖሚና የሰብዓዊነት ጉባኤ ባሳለፍነው ሳምንት ሐምሌ 20 እና 21 ቀን 2015 ዓ.ም በሩስያ ቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ መካሄዱ ይታወቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ሐምሌ24 ቀን2015 ዓም

ከደባርቅ_ጃናሞራ በመጓዝ ላይ የነበረ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የስምንት ሰዎች ህይወት አለፈ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከደባርቅ_ጃናሞራ ሰዉና የአፈር ማዳበሪያ ጭኖ በመጓዝ ላይ የነበረ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የስምንት ሰዎች ህይወት አለፈ።
225 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያና ከ16 ሰው በላይ ጭኖ ጉዞውን ከደባርቅ ጃናሞራ አድርጎ ሲጓዝ የነበረው የጭነት መኪና መካነ-ብርሃን ከተማ ከመድረሱ በፊት ደበላ አካባቢ መንገዱን ስቶ መገልበጡን የሰሜን ጎንደር ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።
የስምንቱ ሰዎች ህይዎት ወዲያውኑ ሲያልፍ ከአራት ሰዎች በላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በጃናሞራ እና ደባርቅ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ ናቸው።
አደጋው የተከሰተው ከረፋዱ 4:00 ሰአት አካባቢ ሲሆን ሰወቹ አብዛኛው የተሳፈሩት ቧሂት መገንጠያ ሲሆን የሴፍትኔት የእርዳታ ብር ለማውጣት የመጡ አርሶ አደሮች እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።