Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
አፍሪካ ዘላቂ ሰላም ማስፈን የሚችል ጠንካራ ወታደራዊ ኮማንድ ያስፈልጋታል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
አፍሪካ የ2063 አጀንዳን ለማሳካት ቅድሚያ አህጉራዊ ሰላሟን ማስጠበቅ የሚችል ጠንካራ የሆነ ወታደራዊ ኮማንድ እንደሚያስፈልጋት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ አቶ ሰለሞን ተፈራ ገለጹ።

አቶ ሰለሞን ተፈራ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አፍሪካ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መስተጋብሮችን አስተሳስሮ በመጠቀም ዕድገት ለማስመዝገብ ቅድሚያ ሰላምን ማስፈን ያስፈልጋታል።

ድህነት በመቅረፍ ብልጽግናን ለማምጣት ከውጭ ጣልቃ ገብነት ነጻ አህጉር መፍጠር ይገባል።

እንደ መምህሩ ገለጻ፤ የአፍሪካ ህብረት የተቋቋመበት ዋና አላማ አንዱ ሰላም የሰፈነባትና ድህነት የተቀረፈባት አህጉር....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=105957
የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር 3ነጥብ4 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘ
**************
(ኢ ፕ ድ)
በ2015 በጀት ዓመት የ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን የቢሾፍቱ የከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ በቀጣይ የከተማዋን ገቢ ለማሳደግ የቱሪስቶችን ቀልብ የሚስቡ ኢንቨስትመንቶች ላይ ከፍተኛ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ የከተማ አስተዳደሩ የሚቀጥሉትን 10 ዓመታት ማዕከል ያደረገ ፍኖተ ካርታ ነድፎ እየሰራ ነው፡፡

ይህም በተለይ በገቢ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ ዕድገት እንዲያሳይ የተተለመ ነው፡ ፡ በዚህም በ2015 በጀት ዓመት አስተዳደሩ የ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ አግኝቷል፡፡

ከ10 ዓመቱ እቅድ ደግሞ የአምስት ዓመት ብሎም የበጀት ዓመቱ እቅድ ተነድፎ ሲሰራ የቆየ ሲሆን፤ ስኬታማ ተግባራትን ማከናወን ተችሏል ያሉት አቶ አለማየሁ፤ በ2015 በጀት ዓመት የከተማ አስተዳደሩ፤ 3ነጥብ4 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱ ስኬታማ አድርጎታል…………

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=105975
የሀይድሮጅን ፐርኦክሳይድ አቅርቦትን በሀገር ውስጥ ምርት ማሟላት ተችሏል
**************
(ኢ ፕ ድ)
በ2015 በጀት ዓመት ከ722 ቶን በላይ የሀይድሮጅን ፐርኦክሳይድ በማምረት የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ሙሉ ለሙሉ መሸፈን መቻሉን የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ አስታወቀ።

የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አህመድ ሞቱማ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ሀይድሮጅን ፐርኦክሳይድ ጨርቃ ጨርቅ ለማቅለም ፣ለግብርና ለአበባ እርሻ፣ ለሳኒታይዘር ምትርትና ለሌሎች ፋብሪካዎች ግብአትነት ያገለግላል።

በበጀት ዓመቱ ከ722 ቶን በላይ የሀይድሮጅን ፐርኦክሳይድ በማምረት የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ሙሉ ለሙሉ መሸፈን ተችሏል።

እስከ ቅርብ ጊዜ የዚህ ምርት የሀገር ውስጥ የፍላጎት መጠን 650 ቶን እንደነበር አውስተው፤ በተያዘው በጀት ዓመት ከ722 ቶን በላይ ማምረት በመቻሉ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ሙሉ ለሙሉ መሸፈኑን ተናግረዋል።

ፋብሪካው በአሁኑ ወቅት ያለው የማምረት አቅም በአንድ ኮምፕረሰር አንድ ሺ 500 ቶን እንደሆነ የተናገሩት ሥራ አስኪያጁ፤ ፋብሪካው ባሉት ሦስት ኮምፐረሰሮች ማምረት ሲጀምር አምስት ሺ 500 ቶን እንደሚደርስ ገልጸዋል።

ይህም በቀጣይ እየጨመረ የሚመጣውን የሀገር ውስጥ ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል ይሆናል ያሉት አቶ አህመድ፤ እስካሁን በሙሉ …..

ሙሉውን ለማንበበ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=105947
የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ከሶስት ነጥብ ሁለት ቢሊየን ብር በላይ የዳኝነት ዉሳኔዎችን ማስተላለፉን ገለጸ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በተጠናቀቀው በጀት አመት ከሶስት ነጥብ ሁለት ቢሊየን ብር በላይ የዳኝነት ዉሳኔዎችን ማስተላለፉን ገለጸ።

በ2015ዓ.ም ሂደቶችን አልፈዉ ከቀረቡ 991 መዝገቦች ዉስጥ ሶስት ነጥብ ሁለት ቢሊየን ብር ለያዙ 674 መዝገቦች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓም ድረስ ዉሳኔ መስጠት መቻሉን የኮሚሽኑ ፕሬዚደንት አቶ ሙሉጌታ አያሌዉ አስታውቀዋል።

የኮመሽኑ አመታዊ አፈጻጸሙም 99 ነጥብ ሰባት በመቶ መሆኑን ገልጸዋል። የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ከ2011ዓ.ም ጀምሮ ቅሬታዎችን እየተቀበለ ከ14.4 ቢሊየን ብር በላይ የዳኝነት ዉሳኔዎችን አስተላልፏል።

እንደ አቶ ሙሉጌታ ገለጻ፤ በዉሳኔ ሀሳቡ መሰረትም ለመንግስት የሚጸናዉ እንዳለ ሆኖ ለባለጉዳዩ የሚመለሰዉ ደግሞ ተመላሽ ይሆናል።

የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በገቢዎች እና ጉምሩክ ቅሬታ ያላቸዉ ሰዎች መጀመሪያ ቅሬታቸዉን በተቋሙ አቅርበዉ ተቋሙ ምላሽ ካልሰጣቸዉ በይግባኝ ቅሬታቸዉን ተቀብሎ ዉሳኔ እንዲሰጥ በ2010ዓ.ም መጨረሻ ተቋቁሞ በ2011ዓ.ም ስራ የጀመረ ተቋም እንደሆነ ይታወሳል።

በመዓዛ ማሞ
ሐምሌ24 ቀን 2015 ዓም
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በስሙ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተጠቀሙ ግለሰቦችን ይፋ አደረገ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ ተቋማት በቀረበለት የተማሪዎች የትምህርት ማስረጃ ይጣራልን ጥያቄ መሰረት የደረሰበትንና ሀሰተኛ ናቸው ያላቸውን ሰነዶችና ግለሰቦች ስም ይፋ አድርጓል።

የዩኒቨርሲቲው እንዳስታወቀው፤ በ2015 ዓ/ም የቀረቡ የትምህርት ማስረጃ ማጣራት ጥያቄዎችን ተከትሎ በተደረገ የማጣራት ሂደት ከአንዳንድ ተቋማት የቀረቡ የዩኒቨርሲቲው ምሩቃን የትምህርት ማስረጃዎች በዩኒቨርሲቲው በተሰጣቸው የተማሪ ውጤት ኮፒ ላይ የአጠቃላይ ነጥብ ለውጥ የተደረገባቸው እንዲሁም ፈጽሞ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ያልተማሩባቸው ሐሰተኛ ዲግሪ ማስረጃዎች ሆነው የተገኙ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

መሰል ኃላፊነት የጎደላቸው ተግባራት እንዳይበረታቱ ብሎም ሕዝብና መንግሥት ሙያዊ ብቃት በሌላቸውና ኃላፊነት በጎደላቸው ዜጎች ለጉዳት እንዳይጋለጥ በማሰብ በዩኒቨርሲቲው የትምህርት ማስረጃ ላይ የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ በማስመሰልና በመቀየር እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ስምና ሎጎ ያልተማሩበትን ዲግሪ ይዘው የማጭበርበር ተግባር ላይ የተሠማሩ ግለሰቦች መኖራቸወን አረጋግጫለሁም ብሏል።

ወደ ፊትም በዚህ ተግባር የሚሠማሩ ቢኖሩ ለሕዝብ የማጋለጥ ሥራ በተከታታይነት እንዲሠራ ዩኒቨርሲቲው መወሰኑንመ ገልጿል።

ከታች በቀረበው ዝርዝር መሰረት የሐሰተኛ ማስረጃ ማጣራት ሪፖርት ላይ ስማቸው የተጠቀሱ ግለሰቦች በእነዚህ የትምህርት ማስረጃዎች በየትኛውም ተቋም ቢቀጠሩ ማስረጃዎቻቸው ሕጋዊነት የሌላቸው መሆኑንም ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።

ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓም
"በሁለተኛው የሩስያ-አፍሪካ ጉባዔ ኢትዮጵያ በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ስኬታማ ሥራዎችን አከናውናለች"
- ሰላማዊት ካሣ የመንግሥት ኮሙኒኬሸን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በሁለተኛው የሩስያ-አፍሪካ ጉባዔ ኢትዮጵያ በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ስኬታማ ሥራዎችን ማከናወኗን የመንግሥት ኮሙኒኬሸን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሣ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሀገራቱን የፖለቲካና የባህል ዲፕሎማሲ በኢኮኖሚው መስክ ማጠናከር እንደሚገባ የጋራ አቋም አንጸባርቀዋልም ብለዋል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሸን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሣ፤ በማብራሪያቸው የሩስያ-አፍሪካ የኢኮኖሚና የሰብዓዊነት ጉባዔ ኢትዮጵያ በልማት ሥራዎች ያስመዘገበቻቸውን ተጨባጭ ውጤቶች ያስተዋወቀችበት መሆኑንም አንስተዋል።

አፍሪካውያን በምግብ ራሳቸውን ለመቻል የሚያደርጉትን ጥረት ሩስያ በቴክኖሎጂ ግብዓት እንድታግዝ ጥሪ ያቀረበችበትና የዘርፉ ተቋማት የሁለትዮሽ ስምምነቶችን የተፈራረሙበት ነው ብለዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ በሩስያ ቆይታው ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ስኬታማ ውይይት ማድረጉንና ወደ ተግባር የሚቀየሩ ስምምነቶችን መፈራረሙንም ጠቅሰዋል።

በሁለቱ መሪዎች ውይይት ኢትዮጵያ በተለይም በምግብ ራሷን ለመቻል በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ተምሳሌታዊ ተግባር እያከናወነች መሆኑም ተነስቷል ብለዋል።

ለ125 ዓመታት የዘለቀውን የሁለቱን አገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት በኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መስኮች ይበልጥ ማጠናከር የሚያስችሉ ጉዳዮችም የውይይቱ አካል ነበሩ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ።
ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በልማት መስክ በተለይም በግብርናው ዘርፍ ላደረገችው ስኬታማ እንቅስቃሴ የሩስያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አድንቀዋል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት ሩስያ በቴክኖሎጂ፣ በኢንቨስትመንትና በግብዓት የመደገፍ ፍላጎት ያላት መሆኑን አረጋግጣለች።

በጉባዔው የኢትዮጵያን የተለያዩ ተቋማት የወከሉ አመራሮች ከሩስያ አቻዎቻቸው ጋር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር የሚያስችሉ ውይይቶች ማድረጋቸውንም ተናግረዋል።

ለአብነትም የሰላምና ፀጥታ፣ የቴክኖሎጂ፣ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ትብብርን ማጠናከር ስለሚቻልባቸው ጉዳዮች መምከራቸውን በመጠቆም።

የሁለቱን አገራት ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት በኢኮኖሚውም ከፍ ወዳለ ደረጃ ማሸጋገር የሚችሉ ስምምነቶች መፈረማቸውን ነው ሚኒስትር ዴኤታዋ ያነሱት።
የንግድ ትስስራቸውን ለማጠናከር እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን መፍታት የሚያስችል የጉምሩክ አገልግሎት ትብብር፣ በኢትዮጵያ የባዮሎጂካል ሳይንስ ምርምር ማዕከል ለማቋቋም፣ የአየር ትራንስፖርት ትብብርና የኒዩክሌር ኃይልን ለሰላማዊ አገልግሎት ማዋል የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ስምምነት መደረጉንም ጠቅሰዋል።

በአፍሪካ የኢንዱስትሪ ሂደቶችን ለማጠናከር ሩስያ እንድታግዝ ኢትዮጵያ ጥሪ ማቅረቧን አስታውሰው በአፍሪካና ሩስያ መካከል ያለውን የንግድ ትስስር እንቅፋቶችን ለመፍታት በጋራ መስራት እንደሚገባ በጉባኤው ተመላክቷል ነው ያሉት።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም የነዳጅ ዋጋ መናርንና የግብርና ግብዓት ችግሮችን ለመፍታት ሩስያ ከአፍሪካ ጋር አበክራ እንድትሰራ ጥሪ መቅረቡን አንስተዋል።

አፍሪካ የተፈጥሮ ኃብቷን እሴት ጨምራ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የምታደርገውን ጥረት የሩስያ እገዛ ወሳኝ መሆኑ መነሳቱን በማስታወስ ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የሩስያ አፍሪካ ጉባዔ ለማስተናገድ ጥያቄ ማቅረቧንም ሚኒስትር ዴኤታዋ ጠቁመዋል።

ሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ የኢኮኖሚና የሰብዓዊነት ጉባኤ ባሳለፍነው ሳምንት ሐምሌ 20 እና 21 ቀን 2015 ዓ.ም በሩስያ ቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ መካሄዱ ይታወቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ሐምሌ24 ቀን2015 ዓም
ከደባርቅ_ጃናሞራ በመጓዝ ላይ የነበረ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የስምንት ሰዎች ህይወት አለፈ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከደባርቅ_ጃናሞራ ሰዉና የአፈር ማዳበሪያ ጭኖ በመጓዝ ላይ የነበረ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የስምንት ሰዎች ህይወት አለፈ።

225 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያና ከ16 ሰው በላይ ጭኖ ጉዞውን ከደባርቅ ጃናሞራ አድርጎ ሲጓዝ የነበረው የጭነት መኪና መካነ-ብርሃን ከተማ ከመድረሱ በፊት ደበላ አካባቢ መንገዱን ስቶ መገልበጡን የሰሜን ጎንደር ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።

የስምንቱ ሰዎች ህይዎት ወዲያውኑ ሲያልፍ ከአራት ሰዎች በላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በጃናሞራ እና ደባርቅ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ ናቸው።

አደጋው የተከሰተው ከረፋዱ 4:00 ሰአት አካባቢ ሲሆን ሰወቹ አብዛኛው የተሳፈሩት ቧሂት መገንጠያ ሲሆን የሴፍትኔት የእርዳታ ብር ለማውጣት የመጡ አርሶ አደሮች እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።

ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም
አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከቼሪ ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ ዋና ስራ ጋር መወያየታቸውን በቻይና የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታወቀ።
*****
(ኢ.ፕ.ድ)
በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው የቼሪ ኮሜርሻል ተሽከርካሪዎች ኢንተርናሽናል ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ጄን ኩይ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን ኢንባሲው አስታውቋል።

በውይይታቸውም አምባሳደሩ ፤ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የመኪና አምራቾች ዋነኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻ አድርገው እንዲመርጡ ያደረጓቸውን ዋና ዋና ምክንያቶች አብራርተዋል።

አምባሳደሩ በኢኮኖሚው ፈጣን እድገት ምክንያት እየጨመረ የመጣውን የንግድ ተሽከርካሪዎች ፍላጎት በመጥቀስ፣ በሀገሪቱ ውስጥ የመኪና መገጣጠሚያ ፍብሪካዎች ለሚያቋቁሙ አለም አቀፍ ኩባንያዎች መንግስት ያዘጋጀውን ማራኪ ማበረታቻ ጠቅሰዋል።

የኩባንያ ስራ አስፈጻሚ ጄን ኩይ በበኩላቸው የኢትዮጵያን ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት በማንሳት፥ ኢኮኖሚያዊ እድገቱ ለፍላጎቱ ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

በኤሌክትሪክ ለሚሰሩ ተሽከርካሪዎች የተደረገው የታክስ ማሻሻያም ኢትዮጵያ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያመላክት መሆኑን ጠቅሰው፥ ኩባንያቸው የዚህ ማሻሻያ አካል እንደሚሆንና በኢትዮጵያ ቢሮ የመክፈት ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል።

የቼሪ ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያው ላለፉት 19 አመታት በቻይና የአውቶሞቢል ገበያ ቀዳሚ ተጠቃሽ መሆኑን መረጃው ያመለክታልል።

ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም
ከሆርቲካልቸር ምርት ኤክስፖርት 660 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ
********
(ኢ ፕ ድ)

በ2015 በጀት ዓመት ከሆርቲካልቸር ምርት ኤክስፖርት 660 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። በቀጣዩ የ2015/16 ምርት ዘመን ከሆርቲካልቸር ዘርፉ ከ731 ሚሊዮን የአሜሪካን በላይ ዶላር ለማግኘት እየተሠራ ነው።

በግብርና ሚኒስቴር የሆርቲካልቸር ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ አብደላ ነጋሽ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ከ567 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ዶላር ከአበባ፣ 22 ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ዶላር ከፍራፍሬ፣ ከአትክልት፣ እፀ-ጣዕምና ስራስር ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106010
በክልሉ የመኸር እርሻ ከ29 ሚሊዮን 182 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል
********************
(ኢ ፕ ድ)

በክልሉ የመኸር እርሻ ከ29 ሚሊዮን 182 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ሐሊፋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በዘንድሮው የመኸር እርሻ 937 ሺህ 722 ሄክታር መሬት በሰብል ለመሸፈን ታቅዶ እየተሠራ ነው፤ ከክልሉ የመኸር እርሻ ከ29 ሚሊዮን 182 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል።

በሰብል ለመሸፈን ከታቀደው ሄክታር መሬት ውስጥ እስካሁን ከ800 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ታርሷል ያሉት አቶ ባበክር፤ ከ700 ሺህ ሄክታር በላዩ መሬት ደግሞ ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106025
በሐዋሳከተማአንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ኢንቨስተሮች ፍቃድ ተሰጠ
************************
(ኢ ፕ ድ)

በሐዋሳ ከተማ አንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 40 ኢንቨስተሮች አዲስ የኢንቨስትመንትና የማስፋፊያ ፍቃድ መሰጠቱን የከተማዋ ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የሐዋሳ ከተማ ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ፍቅሬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በተጠናቀቀው 2015 በጀት ዓመት በሐዋሳ ከተማ 40 ኢንቨስተሮች አዳዲስ ፈቃድና ማስፋፊያ ፈቃድ ተሰጥቷል። በዚህም አንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር ካፒታል ኢንቨስትመንት በከተማዋ ኢንቨስት ተደርጓል።

በአሁኑ ወቅት በከተማው በአጠቃላይ 817 ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ተሰማርተው ይገኛሉ ያሉት ኃላፊው፤ ከዚህ ውስጥ 159 ያህሉ በኢንዱስትሪ፤ ከ280 በላይ የሚሆኑት በአገልግሎት ዘርፎች፤ 311 በኮንስትራክሽን እና ከ50 በላይ የሚሆኑት በከተማ ግብርና ዘርፎች የተሠማሩ ናቸው። በዚህም አራት ሺህ 100 ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል።

አምራች ኢንዱስትሪዎች አሁንም ወደሥራ እየገቡ በመሆናቸው የሚፈጥሩት የሥራ ዕድል እየሰፋ ....
https://press.et/?p=106034
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር 27 ፕሮጀክቶችን እያከናወነ ነው
*******************
(ኢ ፕ ድ)

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በሁለት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር 27 የተለያዩ ፕሮጀክቶች ማከናወኑን አስታወቀ። በ195 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡት ሰባት ፕሮጀክቶች በ2015 በጀት ዓመት ተጠናቀዋል።

የዩኒቨርሲቲው የግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋሁን ገብሩ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው ከሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች መካከል የባለሰባት ወለል የአስተዳደር ሕንጻ ይገኝበታል።

ለሕንጻ ግንባታው ከ803 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተመደበ ሲሆን፤ ግንባታው ሲጠናቀቅ የተለያዩ ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106033