Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በሐዋሳከተማአንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ኢንቨስተሮች ፍቃድ ተሰጠ
************************
(ኢ ፕ ድ)

በሐዋሳ ከተማ አንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 40 ኢንቨስተሮች አዲስ የኢንቨስትመንትና የማስፋፊያ ፍቃድ መሰጠቱን የከተማዋ ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የሐዋሳ ከተማ ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ፍቅሬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በተጠናቀቀው 2015 በጀት ዓመት በሐዋሳ ከተማ 40 ኢንቨስተሮች አዳዲስ ፈቃድና ማስፋፊያ ፈቃድ ተሰጥቷል። በዚህም አንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ብር ካፒታል ኢንቨስትመንት በከተማዋ ኢንቨስት ተደርጓል።

በአሁኑ ወቅት በከተማው በአጠቃላይ 817 ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ተሰማርተው ይገኛሉ ያሉት ኃላፊው፤ ከዚህ ውስጥ 159 ያህሉ በኢንዱስትሪ፤ ከ280 በላይ የሚሆኑት በአገልግሎት ዘርፎች፤ 311 በኮንስትራክሽን እና ከ50 በላይ የሚሆኑት በከተማ ግብርና ዘርፎች የተሠማሩ ናቸው። በዚህም አራት ሺህ 100 ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል።

አምራች ኢንዱስትሪዎች አሁንም ወደሥራ እየገቡ በመሆናቸው የሚፈጥሩት የሥራ ዕድል እየሰፋ ....
https://press.et/?p=106034
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር 27 ፕሮጀክቶችን እያከናወነ ነው
*******************
(ኢ ፕ ድ)

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በሁለት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር 27 የተለያዩ ፕሮጀክቶች ማከናወኑን አስታወቀ። በ195 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡት ሰባት ፕሮጀክቶች በ2015 በጀት ዓመት ተጠናቀዋል።

የዩኒቨርሲቲው የግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋሁን ገብሩ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው ከሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች መካከል የባለሰባት ወለል የአስተዳደር ሕንጻ ይገኝበታል።

ለሕንጻ ግንባታው ከ803 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተመደበ ሲሆን፤ ግንባታው ሲጠናቀቅ የተለያዩ ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106033
የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ተደርሷል
****************************
(ኢ ፕ ድ)

የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደተደረሰ ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የብሔራዊ ፓርኮች አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አዳነ ፀጋዬ ለኢፕድ እንደተናገሩት፤ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን በዓለም አቀፍ ቅርስነት ለማስመዝገብ የሚረዱ አስፈላጊ ሰነዶች ለዩኔስኮ ቀርበዋል።

ዩኔስኮ የላካቸው ባለሙያዎች ወደባሌ ብሔራዊ ፓርክ በመሄድ ለተቋማቸው የተላከውን ሰነድ ከፓርኩ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማነጻጸር መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106044
ኮሚሽኑ ከ14 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ለያዙ የታክስ ጉዳዮች ውሳኔ ሰጥቷል
******************
(ኢ ፕ ድ)
ከ14 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ የያዙ የታክስ ጉዳዮች ተመልክቶ የዳኝነት ውሳኔ መስጠቱን የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ገለጸ።

የኮሚሽኑ የ2015 የዕቅድ አፈጻጸም፣ የተገልጋዮች እርካታ ዳሰሳ ጥናትና የ2016 ዓ.ም መሪ ዕቅድ የግምገማ መድረክ ትናንት ተካሂዷል።

የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አያሌው በመድረኩ ተገኝተው እንደገለጹት፤ የውሳኔ የተሰጠባቸው ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106055
የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጉብኝት እያደረጉ ነው
********************
(ኢ ፕ ድ)
👉 ፕሬዝዳንቱ በፓርኩ ውስጥ ችግኝ ተክለዋል

የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ ከጠቅላይ ሚኒስት ዐቢይ አሕመድ ጋር በመሆኑን የቦሌ ለሚ 2 ኢንዱስትሪ ፓርክን እየጎበኙ ነው።

ፕሬዝዳንቱ በፓርኩ ውስጥ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በመሆንም ችግኝ ተክለዋል።

የባንኩ ፕሬዚዳንት ትናንት ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም ፕሬዝዳንቱን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም ፕሬዚዳንቱን በዛሬው እለት በዓለም ባንክ ድጋፍ የተገነባውን የቦሌ ለሚ 2 ኢንዱስትሪ ፓርክ አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴና እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን እያስጎበኟቸው ነው።

የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የትብብር አድማስ በማስፋት ለኢኮኖሚ እድገታችን በኮንሴሽናል ፋይናንስ፣ በአለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በኩል ጠንካራ የኢንቨስትመንት ፋይናንስ አቅርቦት እና የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳችንን የሚደግፍ የዘለቀ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ጠቅላይ ሚኒስትረ ዐቢይ አሕመድ በትናንትናው እለት ማስታወቃቸው ይታወሳል።

በሳሙኤል ወንደሰን
ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓም
(ፎቶ ፋይል)
የከተማ አቀፍ የስድስኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

👉 104 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን አሳልፈዋል
*******************
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የከተማ አቀፍ የስድስኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤትን በዛሬ ዕለት ይፋ አድርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፣ በከተማ አስተዳደሩ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት አድርጎ የስድስተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከ28 አመት በዋላ ዘንድሮ ለመጀመሪያጊዜ ተሰቷል፡፡

እንደ ዶክተር ዘላለም ገለጻ፡-በከተማ አስተዳደሩ 73 ሺ 667 የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል፡፡ ፈተናው ከወሰዱት ተማሪዎች መካከል 3 ተማሪዎች 99 ከመቶ አምጥተዋል፡፡ 477 ተማሪዎች 95ና ከዛ በላይ ማምጣታቸውን ገልጸው 2 ሺህ 787 ተማሪዎች 90ና ከዛ በላይ ያመጡ ሲሆን 59 ሺህ 105 ተማሪዎች 50ና ከዛ በላይ ማምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡

የአጠቃላይ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች 80 ነጥብ 2 በመቶ የሚሆኑት 50ና ከዛ በላይ ማምጣታቸውን ገልፀዋል፡፡

ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች በመደበኛ ከተፈተኑት 67 ሺህ 939 ተማሪዎች 56 ሺህ 842 50ና ከዛ በላይ አምጥተዋል፡፡በዚህም 83 ነጥብ 6 በመቶ የሚሆኑት ማለፋቸውን ተናግረዋል፡፡

የማለፊያ ነጥብን በተመለከተ ለመደበኛ ተማሪዎች 50ና ከዛ በላይ ያመጡ ተማሪዎች የሚያልፉ ሲሆን ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች 45ና ከዛ በላይ ያመጡ ወደ ቀጣዩ ክፍል የሚሸጋገሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

104 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎችን ማሳለፋቸውን ገልጸው ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ ጀምሮ መመልከት የሚችሉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በማርቆስ በላይ
ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ‼️

ኢትዮጵያ ለብዙ ሺህዎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል ያስገኙ 13 የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ገንብታ ወደ ስራ አስገብታለች። የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮችንም ገንብተን በስራ ላይ እንገኛለን።

ከአለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋ ጋር በመሆን ዛሬ ጠዋት በአንደኛው የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በምርት ስራ ላይ ካሉ ኢንዱስትሪዎቻችን ሁለቱን አብረን ጎብኝተናል። ኢትዮጵያ ትልቅ አቅም ያላት ሀገር ብቻ ሳትሆን በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች መዋእለ ነዋይ ለማፍሰስ ለሚሹ ሁሉ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረች ነው።
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና አጀማመርን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተመለከቱ
********************
(ኢ ፕ ድ)

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመገኘት የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ የፈተና አሠጣጥ ሂደቱን ተመልክተዋል።

የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሠር ብርሃኑ ነጋ ከሚንስቴር ደኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ጋር በመሆን አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ሲቪል ሠርቪስ ዩኒቨርሲቲና የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ኢንስቲቲዩት ምልከታ አድርገዋል።

በምልከታቸውም ሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሣይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና በጥሩ ሁኔታ እየተሠጠ መሆኑን ለመገንዘብ መቻሉን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ዛሬ የተጀመረው የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና እስከ ሀምሌ 28/2015 ዓ.ም ለተከታታይ አራት ቀናት ይሰጣል። መጀመሪያው ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ሚስጥራዊነቱና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ መጠናቀቁ ይታወሳል።

ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️

እንደ ሀገር ከ28 ዓመታት በኋላ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ የተሰጠው የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት 73 ሺህ 667 ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን ከነዚህም 80.2% ያህሉ 50 ፐርሰንትና ከዚያ በላይ በማምጣት ወደ ቀጣይ ክፍል ሲያልፉ ፤ 67 ሺህ 939 ከሚሆኑ የቀን ተማሪዎች መካከል 56 ሺህ 842 የሚሆኑት 83.6% የማለፊያ ውጤቱን በማስመዝገብ ወደ ቀጣዩ የትምህርት እርከን ተዘዋውረዋል።

የትምህርት ግብዓት ለማሟላት እያደረግን ያለው ጥረት እና መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ተማሪዎችን ብቁ የማድረግ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣት የሰሩት ስራ ተማሪዎቹ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ በማስቻሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡

ሃገሩን የሚወድ ጠንካራ ትውልድ ለመገንባት እና የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የጀመርናቸውን ስራዎች አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል::