Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ‼️

ኢትዮጵያ ለብዙ ሺህዎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል ያስገኙ 13 የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ገንብታ ወደ ስራ አስገብታለች። የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮችንም ገንብተን በስራ ላይ እንገኛለን።

ከአለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃይ ባንጋ ጋር በመሆን ዛሬ ጠዋት በአንደኛው የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በምርት ስራ ላይ ካሉ ኢንዱስትሪዎቻችን ሁለቱን አብረን ጎብኝተናል። ኢትዮጵያ ትልቅ አቅም ያላት ሀገር ብቻ ሳትሆን በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች መዋእለ ነዋይ ለማፍሰስ ለሚሹ ሁሉ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረች ነው።
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና አጀማመርን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተመለከቱ
********************
(ኢ ፕ ድ)

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመገኘት የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ የፈተና አሠጣጥ ሂደቱን ተመልክተዋል።

የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሠር ብርሃኑ ነጋ ከሚንስቴር ደኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ጋር በመሆን አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ሲቪል ሠርቪስ ዩኒቨርሲቲና የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ኢንስቲቲዩት ምልከታ አድርገዋል።

በምልከታቸውም ሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሣይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና በጥሩ ሁኔታ እየተሠጠ መሆኑን ለመገንዘብ መቻሉን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ዛሬ የተጀመረው የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና እስከ ሀምሌ 28/2015 ዓ.ም ለተከታታይ አራት ቀናት ይሰጣል። መጀመሪያው ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ሚስጥራዊነቱና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ መጠናቀቁ ይታወሳል።

ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️

እንደ ሀገር ከ28 ዓመታት በኋላ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ የተሰጠው የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት 73 ሺህ 667 ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን ከነዚህም 80.2% ያህሉ 50 ፐርሰንትና ከዚያ በላይ በማምጣት ወደ ቀጣይ ክፍል ሲያልፉ ፤ 67 ሺህ 939 ከሚሆኑ የቀን ተማሪዎች መካከል 56 ሺህ 842 የሚሆኑት 83.6% የማለፊያ ውጤቱን በማስመዝገብ ወደ ቀጣዩ የትምህርት እርከን ተዘዋውረዋል።

የትምህርት ግብዓት ለማሟላት እያደረግን ያለው ጥረት እና መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ተማሪዎችን ብቁ የማድረግ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣት የሰሩት ስራ ተማሪዎቹ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ በማስቻሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡

ሃገሩን የሚወድ ጠንካራ ትውልድ ለመገንባት እና የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የጀመርናቸውን ስራዎች አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል::
“የኢንዱስትሪ ፓርኮች መገንባት ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል ፈጥሯል”- የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ
************************
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች መገንባታቸው ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር ማስቻሉን ተመልክቻለሁ ሲሉ የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ ተናገሩ።

ፕሬዚዳንቱን በዛሬው እለት በዓለም ባንክ ድጋፍ የተገነባውን የቦሌ ለሚ 2 ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝተዋል።

ፕሬዚዳንቱ በጉብኝቱ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች መገንባታቸው ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል ፈጥሯል። ስለዚህ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ማስፋፋት በጣም አስፈላጊና ወሳኝ ነው ብለዋል።

ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል ከመፍጠር ባለፈ በርካታ ፋብሪካዎች እንዲገነቡ አድርጓል።

በተለይ በፓርኮቹ ለወጣት ሴቶች የሥራ እድል እየተፈጠረ በመሆኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲኖር ያደርጋል ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ በዚህም ወጣቶችና ሴቶች ራሳቸውን ከመቻል አልፈው ለሌሎች መትረፍ እንደቻሉ ተረድቻለሁ ብለዋል።

ስለዚህ ይህንን ማጠናከር ከተቻለ ወደፊት የተሻለ ስኬትና እድገት እንደሀገር ማስመዝገብ ይቻላል ብለዋል።

የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ ከጠቅላይ ሚኒስት ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር ) ጋር በመሆኑን የቦሌ ለሚ 2 ኢንዱስትሪ ፓርክን መጎብኘታቸው ይታወሳል።

በሳሙኤል ወንደሰን

ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም
ስሙን በማጠልሸት ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላትን እንደማይታገስ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ
************
(ኢ.ፕ.ድ)

ከውጭና ከውስጥ ያሉ የጥፋት ሀይሎች በመቀናጀት ስሙን በማጥፋት ተግባር የተሰማሩ አካላትን እንደማይታገስ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አስታወቀ።

የመከላከያ ሠራዊትብየህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ እነዚህ የጥፋት ሀይሎች የመከላከያ ሰራዊትን ስም የማጥፋት ዘመቻ እያደረጉ ነው።

መከላከያ ሰራዊት አገርን የታደገና አይነተ ብዙ ችግሮችን ተጋፍጦ ድል ያደረገ ሠራዊት ነው ያሉት ኮሎኔል ጌትነት፤
ከዚህ በኋላ የሠራዊቱን ስም የማጥፍት ድርጊት አይታገስም ሲሉ ገልጸዋል።

በጌትነት ምህረቴ
ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም