Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
“የኢንዱስትሪ ፓርኮች መገንባት ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል ፈጥሯል”- የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ
************************
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች መገንባታቸው ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር ማስቻሉን ተመልክቻለሁ ሲሉ የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ ተናገሩ።

ፕሬዚዳንቱን በዛሬው እለት በዓለም ባንክ ድጋፍ የተገነባውን የቦሌ ለሚ 2 ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝተዋል።

ፕሬዚዳንቱ በጉብኝቱ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች መገንባታቸው ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል ፈጥሯል። ስለዚህ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ማስፋፋት በጣም አስፈላጊና ወሳኝ ነው ብለዋል።

ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል ከመፍጠር ባለፈ በርካታ ፋብሪካዎች እንዲገነቡ አድርጓል።

በተለይ በፓርኮቹ ለወጣት ሴቶች የሥራ እድል እየተፈጠረ በመሆኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲኖር ያደርጋል ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ በዚህም ወጣቶችና ሴቶች ራሳቸውን ከመቻል አልፈው ለሌሎች መትረፍ እንደቻሉ ተረድቻለሁ ብለዋል።

ስለዚህ ይህንን ማጠናከር ከተቻለ ወደፊት የተሻለ ስኬትና እድገት እንደሀገር ማስመዝገብ ይቻላል ብለዋል።

የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ ከጠቅላይ ሚኒስት ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር ) ጋር በመሆኑን የቦሌ ለሚ 2 ኢንዱስትሪ ፓርክን መጎብኘታቸው ይታወሳል።

በሳሙኤል ወንደሰን

ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም
ስሙን በማጠልሸት ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላትን እንደማይታገስ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ
************
(ኢ.ፕ.ድ)

ከውጭና ከውስጥ ያሉ የጥፋት ሀይሎች በመቀናጀት ስሙን በማጥፋት ተግባር የተሰማሩ አካላትን እንደማይታገስ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አስታወቀ።

የመከላከያ ሠራዊትብየህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ እነዚህ የጥፋት ሀይሎች የመከላከያ ሰራዊትን ስም የማጥፋት ዘመቻ እያደረጉ ነው።

መከላከያ ሰራዊት አገርን የታደገና አይነተ ብዙ ችግሮችን ተጋፍጦ ድል ያደረገ ሠራዊት ነው ያሉት ኮሎኔል ጌትነት፤
ከዚህ በኋላ የሠራዊቱን ስም የማጥፍት ድርጊት አይታገስም ሲሉ ገልጸዋል።

በጌትነት ምህረቴ
ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም
የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ከዓለም ባንክ ፕሬዝደንት አጃይ ባንጋ ጋር ተወያዩ
*******
(ኢ ፕ ድ)

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ከሚገኙት የዓለም ባንክ ፕሬዝደንት አጃይ ባንጋን ጋር በቢሯቸው ውይይት አድርገዋል፡፡

ውይይቱ በኢትዮጵያና በተቋሙ መካከል ባሉ የጋራ ጉዳዮች፣ በኢትዮጵያና በዓለምን ባንክ መካከል መልካም ግንኙነት ይበልጥ መጠናከር በሚችልበት ሁኔታ እንዲሁም የኢትዮጵያ ቅድሚያ በምትሰጣቸው የልማት  መስኮች ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

በአለም ባንክ የሚደገፉ ፕሮጀክቶች በኢትጵያ ለዋንኞቹ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ጠቅሰው በኢትዮጵያና በአለም ባንክ መካከል ያለው የልማት ትብብር ዘላቂና አካታች እድገት ለማስመዝብ እንደሚያግዝ ሚኒስትሩ አመልተዋል፡፡

በተሻሻለ ምርታማነትና በተወዳዳሪነት መንፈስ ኢኮኖሚያዊ ሽግግርን ለማፋጠን የታቀደውን ሁለተኛውን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ተገባራዊ በማድረግ ሂደት ሊያጋጥሙ ስለሚችሉት  መልካም እድሎችና ፈተናዎች  ክቡር ሚኒስትሩ አብራርተው ከሀገሪቱ የልማት ፍላጎትን  ከማክሮ ኢኮኖሚ ተግዳሮቶች አንጻር ሀገሪቱ ይህን ግዙፍ ማሻሻያ አጀንዳ ውጤታማ በሆነ መልኩ ተግባራዊ እንድታደርግ የአለም ባንክ ድጋፉን እንዲሰጥ የባንኩን ፕሬዚዳንት ጠይቀዋል፡፡

ክቡር አቶ አህመድ ጨምረውም ድህነት እያስከተለ ያለውን ልዩ ተግዳሮት ታሳቢ ያደረገ ምላሽ ከባንኩ የማሻሻያ ሂደት እንደሚጠብቁና በተለይም የባንኩ ድጋፍ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት አንገብጋቢ ፍላጎት ጋር መጣጣሙን በተመለከተ ለውጥ እንሚጠብቁም ተናግረዋል፡፡

አዲሱ የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ባንኩ ባካሄደው የለውጥ ሂደት  በአጭር ጊዜ ውስጥ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እንዲሁም  የባንኩን የፋይናንስ አቅም ለማሳደግ በቅርቡ የተወሰዱትን ውጤታማ እርምጃዎች  ለፕሬዝደነት አጃይ ባንጋ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️

ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በ100,414 ካሬ ሜትር መሬት ላይ የገነባናቸውን 158 የመስሪያ ሼዶች አስመርቀን በትጋት ለሚሰሩ እጆች ዝግጁ አድርገናል፡፡

በሰኔ ወር የተላለፉ 2,389 ሼዶችን ጨምሮ በጥቅሉ ባዘጋጀናቸው ከ2500 በላይ ሼዶች 17 ሺህ የከተማችን ወጣቶችና ሴቶች እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው::

ወጣቶችና ሴቶች የለውጡ ዋና ሞተር በመሆናቸው በከተማው ባሉ መጠነ ሰፊ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ በመሳተፍ እራሳቸውን እና ሃገራቸውን መለወጥ እንዲችሉ የከተማ አስተዳደሩ 24/7 በመስራት ላይ ይገኛል ።በዚህም ዓመት ከወጣቶችና ሴቶች ጋር በነበረን ውይይት ለተጠየቅነው የመስሪያ ቦታ ጥያቄ በተጨባጭ ፈጣን ምላሽ የሰጠንበት ወቅት ነው::

የህዝባችንን የኑሮ ሸክም የሚያቀልሉ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለሁሉም የምትመች "ውብ አዲስ አበባን" ዕውን ለማድረግ በትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ‼️
በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ -ግብር 6 ነጥብ 25 ቢሊዮን የቡና ችግኞች ተተክለዋል
*****************************
(ኢ ፕ ድ)
በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ስድስት ነጥብ 25 ቢሊዮን የቡና ችግኞች መተከላቸውን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

በባለሥልጣኑ የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ደፈረስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በመጀመሪያው ምዕራፍ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር አምስት ቢሊዮን በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ አንድ ነጥብ 25 ቢሊዮን የቡና ችግኞች ተተክለዋል፡፡

የቡና ችግኞችን በማስፋፋት ቀጣይነት ባለው መልኩ ይሠራበታል ያሉት አቶ ፍቃዱ፤ በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በአጠቃላይ ከአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን በላይ የቡና ችግኞች እንደሚተከሉ ይጠበቃል ብለዋል።

በመስኖ አጠቃቀም ሥርዓት የሚለሙ የቡና ችግኞች በደቡብ፣ በምዕራብና በምሥራቅ እንዲሁም ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106086