Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️

ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በ100,414 ካሬ ሜትር መሬት ላይ የገነባናቸውን 158 የመስሪያ ሼዶች አስመርቀን በትጋት ለሚሰሩ እጆች ዝግጁ አድርገናል፡፡

በሰኔ ወር የተላለፉ 2,389 ሼዶችን ጨምሮ በጥቅሉ ባዘጋጀናቸው ከ2500 በላይ ሼዶች 17 ሺህ የከተማችን ወጣቶችና ሴቶች እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው::

ወጣቶችና ሴቶች የለውጡ ዋና ሞተር በመሆናቸው በከተማው ባሉ መጠነ ሰፊ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ በመሳተፍ እራሳቸውን እና ሃገራቸውን መለወጥ እንዲችሉ የከተማ አስተዳደሩ 24/7 በመስራት ላይ ይገኛል ።በዚህም ዓመት ከወጣቶችና ሴቶች ጋር በነበረን ውይይት ለተጠየቅነው የመስሪያ ቦታ ጥያቄ በተጨባጭ ፈጣን ምላሽ የሰጠንበት ወቅት ነው::

የህዝባችንን የኑሮ ሸክም የሚያቀልሉ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለሁሉም የምትመች "ውብ አዲስ አበባን" ዕውን ለማድረግ በትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም የስራ ማስታወቂያ‼️
በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ -ግብር 6 ነጥብ 25 ቢሊዮን የቡና ችግኞች ተተክለዋል
*****************************
(ኢ ፕ ድ)
በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ስድስት ነጥብ 25 ቢሊዮን የቡና ችግኞች መተከላቸውን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

በባለሥልጣኑ የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ደፈረስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በመጀመሪያው ምዕራፍ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር አምስት ቢሊዮን በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ አንድ ነጥብ 25 ቢሊዮን የቡና ችግኞች ተተክለዋል፡፡

የቡና ችግኞችን በማስፋፋት ቀጣይነት ባለው መልኩ ይሠራበታል ያሉት አቶ ፍቃዱ፤ በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በአጠቃላይ ከአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን በላይ የቡና ችግኞች እንደሚተከሉ ይጠበቃል ብለዋል።

በመስኖ አጠቃቀም ሥርዓት የሚለሙ የቡና ችግኞች በደቡብ፣ በምዕራብና በምሥራቅ እንዲሁም ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106086
መሬት በሊዝ ወስደው ያላለሙ 68 ባለሃብቶች ውል ተቋረጠ
*************************
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 90 ሄክታር መሬት በሊዝ ወስደው ያላለሙ 68 አልሚዎችን ውል ማቋረጡን እና 1 ሺ 283 አልሚዎች ግንባታ እንዲጀምሩ መወሰኑን አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም አስመልክቶ በተካሄደው ግምገማ ላይ እንደተናገሩት፤ አንዳንድ አልሚዎች መሬት ከተቀበሉ በኋለ በወቅቱ ግንባታ ሳይጀምሩ ለረጅም ዓመታት አጥረው ያስቀምጣሉ።

ነገር ግን የሊዝ ሕጉ አንድ መሬት ለልማት ከተወሰደ በኋላ መቼ እንደሚጀመር፤ መቼ ሀምሳ በመቶ መድረስና መቼ ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106081
ክረምትን ለበጎ ፈቃድ ያዋሉ ወጣቶች
*************
(ኢ ፕ ድ)

የበጎ ፈቃድ ሥራና ሰብዓዊነት ግለሰቦችን ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ መንገድ ሌሎች ሰዎችን እንዲረዱ የሚያደርጋቸው ምግባር ነው:: በጎ ፈቃድን ለሚያከናውኑት በጎ ምግባር በምላሹ ምንም ሳይጠይቁ ለሰው ልጅ የሚሰጥ በመሆኑ የተመረጡት ብቻ የሚከውኑት ተግባር ነው።

በጎ አድራጊነት ከማኅበረሰቡ ጎን በመሆን የሚያውቁትን የሚያስተምሩበት የአቅማቸውን ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106085
‹‹ኢትዮጵያ ዋነኛ የጀርመን የልማት አጋር ነች›› በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አውር
*******************
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከሚገኙ ሀገራት ዋነኛዋ የጀርመን አጋር ናት ሲሉ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አውር ተናገሩ፡፡

በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አውር ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ ጀርመን በተለያዩ ዘርፎች አጋርነት ከፈጠረችባቸው 12 የአፍሪካ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ዋነኛዋ ናት።

ኢትዮጵያና ጀርመን በሁለትዮሽ ብቻ ሳይሆን በባለብዙ ወገን ግንኙነትም ላይ በንቃት ተሳትፏቸውን እያሳደጉ ይገኛል። እንደ አምባሳደር ስቴፈን ገለጻ፤ ኢትዮጵያና ጀርመን በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በመልካም አስተዳደር ማስፈን፣ እንዲሁም በአሳታፊና ሰላማዊ ማኅበረሰብ ላይም ግንኙነታቸውን አሳድገዋል።

በዘላቂ የልማት ዘርፎች፣ በኢኮኖሚ፣ በሥነ-ምሕዳርና በማኅበረሰብ ልማት ውስጥ የሚያደርጉትን ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106083
በክልሎች የአንበጣ መንጋ ምልክት በመታየቱ የቅድመ መከላከል ሥራ እየተሠራ ነው
*****************
(ኢ ፕ ድ)

በአፋርና በትግራይ ክልል የተበታተነ የአንበጣ መንጋ ምልክት በመታየቱ ተራብቶ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የቅድመ መከላከል ሥራ እየተሠራ ነው ሲል የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ::

በግብርና ሚኒስቴር የእፅዋት ጥበቃ መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ በላይነህ ንጉሤ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ2015/16 ዓ.ም የመኸር ወቅት በአፋርና በትግራይ ክልል በተደረገ የአንበጣ መንጋ የዳሰሳና የትንበያ ጥናት ሥራ የተበታተነ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ ምልክት አሳይቷል:: የታየው የተበታተነ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ ተራብቶ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የክትትልና ቁጥጥር ሥራ እየተሠራ ነው::

በአፋርና በትግራይ ክልል የታየው የተበታተነ የአንበጣ መንጋ በሳርና በሰብል ላይ ጉዳት ማድረስ የሚችል አይደለም ያሉት ሥራ አስፈፃሚው፤ የታየውን ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106107
በትግራይ ክልል የአሸንዳ በዓል በልዩ ድምቀት ይከበራል-ቢሮው
******************
(ኢ ፕ ድ)
በትግራይ ክልል የአሸንዳ በዓል በልዩ ድምቀት እንደሚከበር የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሃላፊ ዶክተር አፅበሃ ገብረእግዚአብሄር ለኢዜአ እንደገለጹት በአሉ የተገኘውን ሰላም ማጽናት በሚያስችል መልኩ ይከበራል።

በአሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የመከባበርና የመደጋገፍ እሴቶች የሚጎለብቱበት በመሆኑ በልዩ ድምቀት በባህላዊ ኩነቶች እንደሚከበር አመላክተዋል።

በአሉ ከተለያዩ አካባቢዎች ልጃገረዶችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የፌዴራልና የክልል የስራ ሀላፊዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።

ከነሀሴ 16 - 18 ቀን 2015 ዓ.ም ለሶሰት ቀናት በሚከበረው በዓል የጎዳና ላይ ትርኢትን ጨምሮ የልጃገረዶች ባህላዊ አልባሳትና ባህላዊ ጨዋታዎች እንደሚቀርቡበትም አመላክተዋል።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለበአሉ ዝግጅት ድጋፍ ማድረጉን የገለጹት ሀላፊው በአሉ ቱሪዝሙን የሚያነቃቃ መሆኑን አስታውቀዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሴቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ አለማት አማረ በበኩላቸው አሸንዳ በየዓመቱ በሴቶች የሚከበር በዓል ነው ብለዋል።

ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም
ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ከአሜሪካ ግምጃ ቤት ምክትል ረዳት ፀሐፊ ጋር ተወያዩ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ከአሜሪካ ግምጃ ቤት ምክትል ረዳት ፀሐፊ ኤሪክ ሜየር ጋር በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር ላይ ተወያዩ ።

በውይይቱም ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ የአሜሪካ ግምጃ ቤት በኢትዮጵያ እድገትን ለማፋጠንና የኢኮኖሚ መረጋጋት እንዲመጣ እየተወጣ ላለው ገንቢ ሚና ምስጋና ማቅረባቸውን ባንኩ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም