የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)መልዕክት ‼️
የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀያሺ ዮሺማሳን ተቀብዬ አነጋግሪያለው። ኢትዮጵያ ከጃፓን ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች:: በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ላይ ለመተባበር ቁርጠኛ አቋምም አላት።

በአማራ ክልል ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ በመደበኛ የህግ ማስከበር ስርአት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ እንዲተገብር የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠየቀ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
በአማራ ክልል ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ በመደበኛ የህግ ማስከበር ስርአት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ እንዲተገብር የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠየቀ።
በአማራ ክልል የተከሰተው የሰላም መደፍረስ በክልሉ ከፍተኛ ሰብአዊ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እያደረሰ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።
የተከሰተውን የፀጥታ ችግር በቁጥጥር ስር ለማዋል እስካሁን በክልሉና በፌደራል የፀጥታ ሃይሎች በኩል በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል።
ሆኖም በክልሉ ያለው የፀጥታ መደፍረስና ጥቃት በንፁሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት በአስቸኳይ ለማስቆም የፌደራል መንግስት ከመደበኛው የህግ ማስከበር ስርአት ባሻገር በኢፌዴሪ ህገ መንግስት መሰረት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ በአፋጣኝ እንዲተገበር ነው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የጠየቀው።
ክልሉ ወደ ቀደመ መረጋጋቱ እንዲመለስ ዜጎች ሰላማቸው ተመልሶ አርሶአደሩ ወደ እርሻው ክልሉም ወደ ልማት ስራዎች ፊቱን እንዲያዞር ለማድረግ መንግስት ያለበትን ሃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ ይገባልም በሚል የፌደራል መንግስትን ጠይቋል።

የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል። ጉባኤው ለሶስት ቀናት ቆይታ የሚኖረው ሲሆን የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደርጋል።
አጀንዳዎቹም የባለፈውን ጉባኤ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማፅደቅ፣ የምክር ቤቱን የ2015 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም መገምገም፣ የክልሉን አስፈፃሚ መስሪያቤቶች የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም መገምገም፣ የክልሉን ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የዕቅድ አፈፃፀምን መርምሮ ማፅደቅ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የዕቅድ አፈፃፀምን መርምሮ ማፅደቅ፣ ለአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የስልጣን ርክክብ ማካሄድ መሆናቸው ታውቋል።
ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓም

የኦሮሚያ ክልል ከንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት 166 ሚልዮን ብር ማግኘቱን ገለጸ
****************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል ከንግድ ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ አገልግሎት በ2015 በጀት ዓመት ከ166 ሚልዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን የክልሉ ንግድ ቢሮ ገለፀ።
የቢሮው የእቅድና በጀት ዳይክተር አቶ ክፍሌ ታደለ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ክልሉ ከንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ከ166 ሚልዮን ብር በላይ ገቢ አግኝቷል።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ ክልሉ በበጀት ዓመቱ ከግማሽ ሚልዮን በላይ ለሚሆኑ ተገልጋዮች በሰጠው አገልግሎት ነው ገቢውን ማስገባት የቻለው።
በዳግማዊት ግርማ (ከሚዛን አማን)

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
ዛሬ ማለዳ በቀን 67 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ መስጠት የሚችሉ፣ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የአዲስአበባ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 1.8 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው የንጹህ መጠጥ ውሀ፣ የፍሳሽ ማጣሪያ እና የውሀ ላብራቶሪ ፕሮጀክቶችን መርቀን አገልግሎት አስጀምረናል፡፡
በቀን 67 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ መስጠት የሚችሉ 25 የውሀ ጉድጓዶች ቁፋሮ እና የውሀ መሰረተ ልማት ግንባታን በማጠናቀቅ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች አሟልተን ስራ ያስጀመርናቸው ፕሮጀክቶች የከተማዋን ዕለታዊ ውሃ የማምረት አቅም ወደ 792 ሺህ ሜትር ኪዩብ ከፍ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
ለሕብረተሰቡ የሚሰራጨውን ውሀ ደህንነት የሚያረጋግጥ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ዘመናዊ የውሃ እና ፍሳሽ ላብራቶሪ ተቋቁሞ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን አሟልተን ስራ ያስጀመርናቸው ሲሆን፣ በሌላ በኩል የፍሳሽ ማጣሪያ እና 40 ኪሎ ሜትር የተለያዩ መጠን ያላቸው የውሀ ማስተላለፊያ መስመሮች ዝርጋታ ስራ እንዲጀምር አድርገናል፡፡
እነዚህ ፕሮጀክቶች በ2015 በጀት ዓመት ተጀምረው የተጠናቀቁ ናችው። ከተማችን ፕሮጀክት ጀምራ በተያዘለት ጊዜና በጀት የማጠናቀቅ ባሕሏን ጠብቃ የነዋሪውን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥና የከተማችንን ገጽታ በመገንባት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን ከፍ ለማድረግ በትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን።
የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን!

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ አመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር፣ ሁለተኛ ዓመት፣ አራተኛ መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል።
ምክር ቤቱ እያካሄደ በሚገኘው ጉባኤም የ2015 አመት የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት አፈፃፀም ሪፖርት እና 2016 እቅድ ላይ ከተወያየ በኋላ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት የ2015 የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ የሚወያይ ሲሆን ምክር ቤቱ ለቋሚ ኮሚቴ የመራው የ2013 እና 2014 የኦዲት ግኝት ግብረ መልስ ለምክር ቤቱ ይቀርባል።
ከዚህ በተጨማሪም ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚኖረው ቆይታ የክልሉ መስተዳድር የ2016 ዓ.ም የሥራ ዘመን ማስፈጸሚያ በጀት ላይ በመምከርም ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የክልሉ የመንግሥት ኮምንኬሽን ቢሮ ዘግቧል።
ሐምሌ 28,ቀን 2015 ዓ.ም

ከ48 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የኤሌክትሪክ ቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ሥርዓት ሊዘረጋ ነው
**************
(ኢ ፕ ድ)
-ፕሮጀክቱ አምስት ሚሊዮን ደንበኞችን ማስተናገድ ያስችላል
ከ48 ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የኃይል ብክነትን ለመቀነስና የገንዘብ አሰባሰብን ለማዘመን የሚረዳ የኤሌክትሪክ ቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ሥርዓት ሊዘረጋ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ አምስት ሚሊዮን ደንበኞችን ማስተናገድ እንደሚያስችል ተገልጿል።
በአገልግሎቱ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ48 ሚሊዮን 875 ሺህ 545 ዶላር በሆነ ወጪ የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ሥርዓት ለመዘርጋት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ ዘመናዊ የቅድመ ክፍያ መተግበሪያና የአይሲቲ መሰረተ-ልማት፣ የ500 ሺህ ባለነጠላና ባለሶስት ፌዝ የስማርት ቆጣሪና ተያያዥ ግብዓቶች አቅርቦትን እንዲሁም የቴክኒክና የሲስተም አጠቃቀም ስልጠናና ሌሎች ስራዎችን ያካትታል፡፡
ቴክኖሎጂው ደንበኞች ወደ ማዕከላት መምጣት ሳይጠበቅባቸው ካሉበት ቦታ ሆነው ለኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦቱ ቅድመ ክፍያ.........
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=106270