የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል። ጉባኤው ለሶስት ቀናት ቆይታ የሚኖረው ሲሆን የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደርጋል።
አጀንዳዎቹም የባለፈውን ጉባኤ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማፅደቅ፣ የምክር ቤቱን የ2015 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም መገምገም፣ የክልሉን አስፈፃሚ መስሪያቤቶች የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም መገምገም፣ የክልሉን ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የዕቅድ አፈፃፀምን መርምሮ ማፅደቅ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የዕቅድ አፈፃፀምን መርምሮ ማፅደቅ፣ ለአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የስልጣን ርክክብ ማካሄድ መሆናቸው ታውቋል።
ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓም

የኦሮሚያ ክልል ከንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት 166 ሚልዮን ብር ማግኘቱን ገለጸ
****************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል ከንግድ ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ አገልግሎት በ2015 በጀት ዓመት ከ166 ሚልዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን የክልሉ ንግድ ቢሮ ገለፀ።
የቢሮው የእቅድና በጀት ዳይክተር አቶ ክፍሌ ታደለ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ክልሉ ከንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ከ166 ሚልዮን ብር በላይ ገቢ አግኝቷል።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ ክልሉ በበጀት ዓመቱ ከግማሽ ሚልዮን በላይ ለሚሆኑ ተገልጋዮች በሰጠው አገልግሎት ነው ገቢውን ማስገባት የቻለው።
በዳግማዊት ግርማ (ከሚዛን አማን)

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
ዛሬ ማለዳ በቀን 67 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ መስጠት የሚችሉ፣ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የአዲስአበባ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 1.8 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው የንጹህ መጠጥ ውሀ፣ የፍሳሽ ማጣሪያ እና የውሀ ላብራቶሪ ፕሮጀክቶችን መርቀን አገልግሎት አስጀምረናል፡፡
በቀን 67 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ መስጠት የሚችሉ 25 የውሀ ጉድጓዶች ቁፋሮ እና የውሀ መሰረተ ልማት ግንባታን በማጠናቀቅ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች አሟልተን ስራ ያስጀመርናቸው ፕሮጀክቶች የከተማዋን ዕለታዊ ውሃ የማምረት አቅም ወደ 792 ሺህ ሜትር ኪዩብ ከፍ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
ለሕብረተሰቡ የሚሰራጨውን ውሀ ደህንነት የሚያረጋግጥ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ዘመናዊ የውሃ እና ፍሳሽ ላብራቶሪ ተቋቁሞ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን አሟልተን ስራ ያስጀመርናቸው ሲሆን፣ በሌላ በኩል የፍሳሽ ማጣሪያ እና 40 ኪሎ ሜትር የተለያዩ መጠን ያላቸው የውሀ ማስተላለፊያ መስመሮች ዝርጋታ ስራ እንዲጀምር አድርገናል፡፡
እነዚህ ፕሮጀክቶች በ2015 በጀት ዓመት ተጀምረው የተጠናቀቁ ናችው። ከተማችን ፕሮጀክት ጀምራ በተያዘለት ጊዜና በጀት የማጠናቀቅ ባሕሏን ጠብቃ የነዋሪውን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥና የከተማችንን ገጽታ በመገንባት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን ከፍ ለማድረግ በትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን።
የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን!

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ አመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር፣ ሁለተኛ ዓመት፣ አራተኛ መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል።
ምክር ቤቱ እያካሄደ በሚገኘው ጉባኤም የ2015 አመት የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት አፈፃፀም ሪፖርት እና 2016 እቅድ ላይ ከተወያየ በኋላ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት የ2015 የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ የሚወያይ ሲሆን ምክር ቤቱ ለቋሚ ኮሚቴ የመራው የ2013 እና 2014 የኦዲት ግኝት ግብረ መልስ ለምክር ቤቱ ይቀርባል።
ከዚህ በተጨማሪም ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚኖረው ቆይታ የክልሉ መስተዳድር የ2016 ዓ.ም የሥራ ዘመን ማስፈጸሚያ በጀት ላይ በመምከርም ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የክልሉ የመንግሥት ኮምንኬሽን ቢሮ ዘግቧል።
ሐምሌ 28,ቀን 2015 ዓ.ም

ከ48 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የኤሌክትሪክ ቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ሥርዓት ሊዘረጋ ነው
**************
(ኢ ፕ ድ)
-ፕሮጀክቱ አምስት ሚሊዮን ደንበኞችን ማስተናገድ ያስችላል
ከ48 ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የኃይል ብክነትን ለመቀነስና የገንዘብ አሰባሰብን ለማዘመን የሚረዳ የኤሌክትሪክ ቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ሥርዓት ሊዘረጋ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ አምስት ሚሊዮን ደንበኞችን ማስተናገድ እንደሚያስችል ተገልጿል።
በአገልግሎቱ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ48 ሚሊዮን 875 ሺህ 545 ዶላር በሆነ ወጪ የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ሥርዓት ለመዘርጋት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ ዘመናዊ የቅድመ ክፍያ መተግበሪያና የአይሲቲ መሰረተ-ልማት፣ የ500 ሺህ ባለነጠላና ባለሶስት ፌዝ የስማርት ቆጣሪና ተያያዥ ግብዓቶች አቅርቦትን እንዲሁም የቴክኒክና የሲስተም አጠቃቀም ስልጠናና ሌሎች ስራዎችን ያካትታል፡፡
ቴክኖሎጂው ደንበኞች ወደ ማዕከላት መምጣት ሳይጠበቅባቸው ካሉበት ቦታ ሆነው ለኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦቱ ቅድመ ክፍያ.........
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=106270

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ ወሰነ
**************
(ኢ ፕ ድ)
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባ በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ ወሰነ።
ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የሕዝብን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በቀረበው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6 /2015 ላይ ነው፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚታየውን በትጥቅ የተደገፈ ህገወጥ እንቅስቃሴ በመደበኛ የህግ ማስክበር ስርዓት ለመቆጣጠር ወደ ማይቻልበት ደረጃ የተሸጋገረ በመሆኑ፤ ይህ እንቅስቃሴ የክልሉን ነዋሪ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ያወከ እና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ፤ የሕዝብን ሠላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንዲሁም ህግ እና ስርዓት ለማስከበር የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ እንቅስቃሴው በሃገር ደህንነት እና በህዝብ ሰላም ላይ የደቀነው አደጋ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መጥቷል፡፡ መንግስት ትጥቅ አንስተው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ሁሉ የሰላም እና ህጋዊ መንገድን እንዲከተሉ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
የታጠቁ ፅንፈኛ ቡድኖች እየፈፀሙ ባለዉ ጥቃት ምክንያት የክልሉ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል፡፡
የክልሉ መንግስትም በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ያጋጠመው የፀጥታ መደፍረስ በክልሉ ከፍተኛ ሰብዓዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እያስከተለ የሚገኝ መሆኑን በመግለጽ፣ ሁኔታውን በመደበኛው የህግ ማስከበር ሥርዓት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ፣ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ በኢፌድሪ ህገ መንግስት መሰረት እንዲደነግግ እና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ጥያቄ አቅርቧል።
በመደበኛ የህግ ስርዓትን መሰረት አድርጎ ይህን ፈር የለቀቀ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር አዳጋች ሁኔታ በመፈጠሩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ህገመንግስቱ እና ህገመንግስታዊ ስርዓት ላይ የተቃጣ አደጋን በመደበኛ የህግ ስርዓት ለመቆጣጠር ባልተቻለ ጊዜ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ ህገመንግስታዊ ስርዓትን ከአደጋ የመከላከል ስልጣን እንዳለው በኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀፅ 93 (1) ተደንግጓል፡፡
በመሆኑም የሚኒስትሮች ምክር ቤት በህገመንግስቱ የተጣለበትን ሃላፊነት ለመወጣት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ስላለበት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ ወስኖል ፡፡
ሐምሌ 28 ቀን2015 ዓም

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለ2016 በጀት ዓመት ከ56 ነጥብ አንድ ቢሊየን በላይ ብር በጀት አጸደቀ
*************
የደቡብ ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በሀዋሳ እየተካሔደ ነው።
ምክር ቤቱ ለ2016 በጀት ዓመት 56 ቢሊየን 135 ሚሊየን 342 ሺ 085 ብር በጀት አጽድቋል።
ለምክር ቤቱ ከቀረበው ረቂቅ በጀት ውስጥ ከፌደራል መንግስት ከሚገኝ ግምጃ ቤት 26 ቢሊየን 557 ሚሊየን 842ሺ 230 ብር መሆኑም ተመላክቷል።
ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም