Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ 583 ዶክተሮችን አስመረቀ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ በቅድም ምረቃናና ድህረ ምረቃ 583 ዶክተሮችን ዛሬ አስመረቀ።

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አስፋ፣ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ድጉማና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

በ"ሰብስፔሻሊቲ፣ በነርሲንግ ስፔሻሊቲ፣ በፐብሊክ ሄልዝ፣ በሌሎች ዘርፎች አስመርቋል።

የኮሌጁ ፕሮቮስት ዶክተር ሲሳይ ሰርጉ እንዳሉት፤ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ለመስጠት፣ ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ለማፍራት ከመማር ማስተማሩ ጐን ለጐን ችግር ፈቺ ምርምሮችን በመስራት የህክምና አሰጣጡ የዘመነ እንዲሆንና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን እየሰራ ነው።

ኮሌጁ በ35 የስልጠና መርሃግብሮች የህክምና ባለሙያዎችን በማሰልጠን የህክምናው ዘርፍ እንዲዘምን ለማስቻል እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ዶክተር ሲሳይ፣ ለአገሪቱ የጤና ስርአት መሻሻል የበኩሉን ሚና እየተወጣ ነው ብለዋል።

ከሚሰጣቸው የስልጠና መርሃግብሮች ሰባቱ በዚህ አመት የተጀመሩ መሆናቸውን ጠቅሰው በቀጣይነትም ምርምሮችን በመስራት የጤና አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን ይሰራል ብለዋል።

ምሩቃን በቀጣይ በኮሌጁ የቀሰሙትን እውቀት በተግባር በመግለጽ ሙያዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ዶክተር ሲሳይ ጥሪ አቅርበዋል።

ኮሌጁ ያስመረቃቸው በህክምና 395፣ በህብረተሰብ ጤና፣ 78፣ በነርስ 110 በድምሩ 583 ሲሆኑ 185ቱ ሴቶች ናቸው።

ከምሩቃኑ መካክል በተሰጠው አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና 151ዱ በሙሉ ከፍተኛ ነጥብ በማስመዝገብ ማለፋቸው ተገልጿል።

በሞገስ ተስፋ
ሐምሌ 30 ቀን 2015 ዓ.ም
ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ የተሳታፊ ልየታ ሥራ በአስር ቀናት ውስጥ ይጀምራል
*************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ የሚደረገው የተሳታፊ ልየታ ሥራ በአስር ቀናት ውስጥ እንደሚጀምር አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሲዳማ፣ በሐረሪ እና በደቡብ ምዕራብ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ የተሳታፊዎች ልየታ ሥራ በአብዛኛው ተጠናቋል።
በቤኒሻንጉልና በጋምቤላ ክልሎች ወደ ተሳታፊዎች ልየታ …

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106452
ኢትዮጵያ የገዛችው አንድ ሚሊዮን ኩንታል ስኳር በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጅቡቲ ወደብ ይደርሳል
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
ኢትዮጵያ የገዛችው አንድ ሚሊዮን ኩንታል ስኳር በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ጅቡቲ ወደብ የሚደርስ መሆኑን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አስታወቀ።

ተጨማሪ አንድ ሚሊዮን ስኳር ግዢ ለመፈፀም እየተሠራ ነው ተብሏል።
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኮርፖሬት ጉዳዮች ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዘመድኩን ተክሌ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ በ2014 ዓመተ ምህረት የኮቪድ ወረርሽኝ …
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106524
ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች የኮሌራ ክትባት አግኝተዋል
- በሦስት ክልሎች በሚገኙ 35 ወረዳዎች ላይ የአተት በሽታን መቆጣጠር ተችሏል
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
ለአንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ዜጎች የኮሌራ ክትባት መስጠቱን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳወቀ።
ኢንስቲትዩቱ 85 የሕክምና መስጫ ጣቢያዎችን በማቋቋም ሕክምና የመስጠት ተግባር እያከናወነ መሆኑ ተመላክቷል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሀይሉ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የክረምት ወራትን …
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106503
ሦስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዜጎች ከፍሎራይድ የጸዳ ውሃ አያገኙም
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)

በስምጥ ሸለቆ አካባቢ የሚኖሩ ሦስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዜጎች ከፍሎራይድ የጸዳ ውሃ እንደማያገኙ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ።

በሚኒስቴሩ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ሐይማኖት በለጠ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ከ12 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በስምጥ ሸለቆና በፍሎራይድ በተጠቃ አካባቢ ይኖራሉ። ከዚህ ውስጥ …
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106501
የኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀል ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያስችላል
*************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ የብሪክስ የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት ካገኘ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ እንደሚሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ እና እስያ ጥናትና ምርምር ማዕከል መምህር ዶክተር ሳሙኤል ተፈራ ተናገሩ።

ዶክተር ሳሙኤል ተፈራ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ብሪክስ ውስጥ ያሉ ሀገራት ከዓለም ኢኮኖሚ 31 ነጥብ ሰባት በመቶ …
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106485
ግብርና ሚኒስቴር 33 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው የወተት ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን ለክልሎች በድጋፍ አበረከተ
****************
(ኢ ፕ ድ)

ግብርና ሚኒስቴር 33 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው ሰባት የወተት ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን ለክልሎች በድጋፍ አበረከተ።

ተሽከርካሪዎቹ ከዓለም ባንክ በድጋፍ የተገኙ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን የወተት ግብይትን በማሳለጥ የሌማት ትሩፋትን ከግብ እንዲደርስ የሚያግዙ መሆናቸውም ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ያበረከታቸውን ተሽከርካሪዎች ድጋፍ የተደረገላቸው የክልል ግብርና እና እንስሳት ሃብት ቢሮ ሃላፊዎች ተረክበዋል።

ተሽከርካሪዎቹ በድጋፍ የተበረከቱትም ለኦሮሚያ፣ ለአማራ፣ ለደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች እንዲሁም ለሲዳማ ክልሎች መሆኑ ተገልጿል።

ተሽከርካሪዎቹ በአንድ ጊዜ 10 ሺህ ሊትር የወተት ምርቶችን ማሰባሰብ እና በተፈለገበት ቦታ ማድረስ የሚችሉ መሆናቸው ተጠቅሷል።

ተሽከርካሪዎቹ ወተት በስፋት የሚያመርቱ አካባቢዎች ላይ አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚደረጉም ተመላክቷል።
በርክክቡ ወቅት ባለፈው በጀት ዓመት በአገር አቀፍ ደረጃ 8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ሊትር ወተት መመረቱ ገልጸዋል።

ይህ የሆነው የእንስሳት ማሻሻያ፣ ዝርያ ማሻሻል እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን መጠቀም በመቻሉ እንደሆነ ተመላክቷል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ በመጪዎቹ ዓመታትም በአገር አቀፍ ደረጃ 11 ቢሊዮን ሊትር ወተት በዓመት ለማምረት ዕቅድ ስለመያዙም ተጠቁሟል።
ነሀሴ 1 ቀን 2015 ዓም
ህገ መንግስትና ሌሎች የህግ ማዕቀፎች ላይ ያተኮረ የሁለቱ ክልሎች የአመራሮች ዉይይት እየተካሄደ ነዉ
****************
(ኢ ፕ ድ)
አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እና የነባሩ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልሎች አመራሮች በህገ መንግስት እና በሌሎችም የህግ ማዕቀፎች ዙሪያ ዉይይት እየተካሄደ ነዉ።
በመድረኩ የክልል ማዕከል ፣የሁለቱም ክሌሎች ዞኖች እና የልዩ ወረዳዎች ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ እንደሚገኙ ከክልሉ የመንግስት ኮምንኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ነሀሴ 1 ቀን 2015 ዓም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️

ዛሬ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲትን በጽ/ቤታችን ተቀብያለሁ። የጋራ ቀጠናዊ ጥቅም ያለን ጎረቤቶች እንደመሆናችን መጠን ትብብራችንን ያለማቋረጥ እናጠናክራለን።