Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሦስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዜጎች ከፍሎራይድ የጸዳ ውሃ አያገኙም
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)

በስምጥ ሸለቆ አካባቢ የሚኖሩ ሦስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዜጎች ከፍሎራይድ የጸዳ ውሃ እንደማያገኙ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጸ።

በሚኒስቴሩ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ሐይማኖት በለጠ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ከ12 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በስምጥ ሸለቆና በፍሎራይድ በተጠቃ አካባቢ ይኖራሉ። ከዚህ ውስጥ …
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106501
የኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀል ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያስችላል
*************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ የብሪክስ የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት ካገኘ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ እንደሚሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ እና እስያ ጥናትና ምርምር ማዕከል መምህር ዶክተር ሳሙኤል ተፈራ ተናገሩ።

ዶክተር ሳሙኤል ተፈራ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ብሪክስ ውስጥ ያሉ ሀገራት ከዓለም ኢኮኖሚ 31 ነጥብ ሰባት በመቶ …
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=106485
ግብርና ሚኒስቴር 33 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው የወተት ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን ለክልሎች በድጋፍ አበረከተ
****************
(ኢ ፕ ድ)

ግብርና ሚኒስቴር 33 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው ሰባት የወተት ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን ለክልሎች በድጋፍ አበረከተ።

ተሽከርካሪዎቹ ከዓለም ባንክ በድጋፍ የተገኙ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን የወተት ግብይትን በማሳለጥ የሌማት ትሩፋትን ከግብ እንዲደርስ የሚያግዙ መሆናቸውም ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ያበረከታቸውን ተሽከርካሪዎች ድጋፍ የተደረገላቸው የክልል ግብርና እና እንስሳት ሃብት ቢሮ ሃላፊዎች ተረክበዋል።

ተሽከርካሪዎቹ በድጋፍ የተበረከቱትም ለኦሮሚያ፣ ለአማራ፣ ለደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች እንዲሁም ለሲዳማ ክልሎች መሆኑ ተገልጿል።

ተሽከርካሪዎቹ በአንድ ጊዜ 10 ሺህ ሊትር የወተት ምርቶችን ማሰባሰብ እና በተፈለገበት ቦታ ማድረስ የሚችሉ መሆናቸው ተጠቅሷል።

ተሽከርካሪዎቹ ወተት በስፋት የሚያመርቱ አካባቢዎች ላይ አገልግሎት እንዲሰጡ እንደሚደረጉም ተመላክቷል።
በርክክቡ ወቅት ባለፈው በጀት ዓመት በአገር አቀፍ ደረጃ 8 ነጥብ 6 ቢሊዮን ሊትር ወተት መመረቱ ገልጸዋል።

ይህ የሆነው የእንስሳት ማሻሻያ፣ ዝርያ ማሻሻል እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን መጠቀም በመቻሉ እንደሆነ ተመላክቷል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ በመጪዎቹ ዓመታትም በአገር አቀፍ ደረጃ 11 ቢሊዮን ሊትር ወተት በዓመት ለማምረት ዕቅድ ስለመያዙም ተጠቁሟል።
ነሀሴ 1 ቀን 2015 ዓም
ህገ መንግስትና ሌሎች የህግ ማዕቀፎች ላይ ያተኮረ የሁለቱ ክልሎች የአመራሮች ዉይይት እየተካሄደ ነዉ
****************
(ኢ ፕ ድ)
አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እና የነባሩ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልሎች አመራሮች በህገ መንግስት እና በሌሎችም የህግ ማዕቀፎች ዙሪያ ዉይይት እየተካሄደ ነዉ።
በመድረኩ የክልል ማዕከል ፣የሁለቱም ክሌሎች ዞኖች እና የልዩ ወረዳዎች ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ እንደሚገኙ ከክልሉ የመንግስት ኮምንኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ነሀሴ 1 ቀን 2015 ዓም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️

ዛሬ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲትን በጽ/ቤታችን ተቀብያለሁ። የጋራ ቀጠናዊ ጥቅም ያለን ጎረቤቶች እንደመሆናችን መጠን ትብብራችንን ያለማቋረጥ እናጠናክራለን።
የከንቲባ አደነች አቤቤ መልዕክት ‼️

“ተግዳሮቶች ያልበገረው ለውጥ” ብለን የጀመርነውን የ2015 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማችንን ዛሬ አጠናቅቀናል።

በ2015 በጀት ዓመት ውጤት ያገኘንባቸው ስራዎቻችን የምንረካባቸው ሳይሆኑ የጀመርናቸውን በማስፋት የነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል፣ ለኑሮ ምቹ፣ ተወዳዳሪና የኢትዮጵያ ብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ከተማ ለመገንባት ይበልጥ ተነሳሽነት የፈጠርንባቸው ነበሩ።

የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓታችንን ቀልጣፋና ፍትሃዊ ለማድረግ የጀመርናቸው የሪፎርም ስራዎችን በማጠናከር፣ ፍትሐዊ አገልግሎት ለህዝባችን ለማድረስ፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በማስተካከልና አገልግሎት አሰጣጣችንን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ረገድ መሻሻል ቢኖርም በቀጣይ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራው ስራ ይሆናል።

ለውጡ ህዝብ ፈልጎ ያመጣውና የሚደግፈው በመሆኑ ተግዳሮት የሚያደናቅፈው አልሆነም።

እኛም ይህን የህዝባችንን እምነት ጉልበት በማድረግ፣ የአመራራችንን አቅም በማጎልበት እና ለህዝብ የሚወግኑ ተቋማትን እየገነባን የነዋሪዎች የዘመናት ጥያቄ የሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እና የኑሮ ጫናን የሚያቀሉ ፕሮጀክቶች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተን መስራታችንን እንቀጥላለን።

የከተማችንን ሰላም ለማስከብር ከሰላም ወዳዱ ህዝባችን ጋር በመሆን ነዋሪዎቻችን በሰላም ወጥተው በሰላም የሚገቡባት ከተማ መሆኗ ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ ለፀረ ሰላም ኃይሎች በእብሪት የሚመጣ ስልጣን እንደሌለ አሁንም ከተማችን ጥሩ ማሳያ ትሆናለች።

ጽንፈኝነትና አክራሪነት በተግባር በህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነት የተሸነፈባት፣ ሰላምዋ በዘላቂነት በህዝብ ተሳትፎ የተረጋገጠላትና ለሁሉም የምትመች፣ እንደስምዋ የተዋበች አዲስ አበባን እውን ለማድረግ በትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን።

ነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ል