Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በ16 ሚሊየን ዶላር በጀት የአፍሪካ ሚኒ ግሪድ ፕሮግራም ተጀምሯል
*****
(ኢ ፕ ድ)
በ16 ሚሊየን ዶላር በጀት 624 ኪሎዋት ሀይል በማመንጨት 32ሺ ግለሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የአፍሪካ ሚኒ ግሪድ ፕሮግራም ተጀምሯል።

ግሎባል ኢንቫሮመንት ፋሲሊቲ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የአፍሪካ ሚኒ ግሪድ ፕሮግራም አስጀመረ

የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ እንደገለጹት ብሔራዊ ኤሌክትርፍኬሽን ፕሮግራም ተቀርፆ በመንቀሳቀስ በ2030 ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

ብሄራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም 35 በመቶ ከመስመር ውጭ (off grid) ለመሸፈን የታለመ በመሆኑ፤ መሰል ፕሮጀክቶች ፕሮግራሙን ለማሳካት ጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የአፍሪካ ሚኒግሪድ ፕሮጀክት 16 ሚሊየን ዶላር የተመደበለት፤ ሲሆን 624 ኪሎዋት ሀይል በማመንጨትና 32ሺ ግለሰቦችን ተጠቃሚ በማድረግ፤ 120 ሰዎች የስራ እድልን ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ የአየር ንብረትን ለመከላከል ሚና እንዳለው ጠቅሰው፤ በዚህ ስራ ከ16ሺ ቶን በላይ የካርበን ልቀትን ለመቀነስ እንደሚረዳና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል
*******
(ኢ ፕ ድ)

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከጥቅምት 28ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ ቀደም ሲል በስራ ላይ በነበረበት ዋጋ እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ::
"ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በቱሪዝም ዘርፍ ይበልጥ ለመሥራት ቁርጠኛ ናት"
-ሚስተር ሺን ኪንሚን በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ምክትል ኃላፊ
******
(ኢ ፕ ድ)

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በቱሪዝም ዘርፍ ይበልጥ ለመሥራት ቁርጠኛ ናት ሲሉ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ምክትል ኃላፊ ሚስተር ሺን ኪንሚን ገለጹ፡፡ ሚስተር ሺን ኪንሚን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ ቻይና በቱሪዝም ዘርፍ እስካሁን ካከናወነቻቸው የትብብር ሥራዎች በላቀ ሁኔታ በጋራ ለመሥራት ዝግጁ ናት።

ቻይናና ኢትዮጵያ በዘርፉ ውጤታማ ሥራዎች ለማከናወን እርስ በእርሳቸው የሚማሩበት ዕድል አላቸው ያሉት ሚስተር ሺን፤ የቻይና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ኢትዮጵያን ከ30 ሀገራት መካከል አዲስ መዳረሻ አድርጎ መሰየሙ በዘርፉ በጋራ ለመሥራት ያለውን ፍላጎት ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በቱሪዝም ዘርፉ ቻይና ኢትዮጵያን ተመራጭ ማድረጓ በርካታ ቻይናውያን ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ያበረታታል ሲሉ አስረድተዋል። አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን የአፍሪካ መዲናና የቻይና መግቢያ በር ናት ያሉት ሚስተር ሺን በከተማዋ ያለውን የኢኮ-ቱሪዝም ሥፍራዎች ማስፋፋት ለዘርፉ ዕድገት.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113229
የነዳጅ ድጎማ ያለአግባብ በተጠቀሙ ሁለት ሺህ 102 አሽከርካሪዎች ላይ ርምጃ ተወሰደ
****
(ኢ ፕ ድ)
በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አገልግሎት ሳይሰጡ የነዳጅ ድጎማ ያለ አግባብ የተጠቀሙ ሁለት ሺህ 102 አሽከርካሪዎች ገንዘቡን እንዲመልሱ መደረጉን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር የብሔራዊ የታለመለት ነዳጅ ድጎማ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሰልማን መሀመድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ሚኒስቴሩ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት ሳይሰጡ የተጠቀሙትን የነዳጅ ድጎማ ተመላሽ የሚያደርጉበት አሠራር አለው።

በዚህ መነሻ መሠረት በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አገልግሎት ሳይሰጡ የነዳጅ ድጎማውን ያለአግባብ የተጠቀሙ ሁለት ሺህ 102 አሽከርካሪዎች ከአራት ሚሊዮን 416 ሺህ 143 ብር እንዲመልሱ ተደርጓል፡፡

በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በኩል እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም በተደረገ ቁጥጥር ከአንድ ሺህ 318 ተሽከርካሪዎች ሁለት ሚሊዮን 767 ሺህ በላይ ብር ተመላሽ እንዲያደርጉ ተደርጓል ያሉት አቶ ሰልማን፤ ተሽከርካሪዎቹ ተመላሽ ያደረጉት አገልግሎት....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113234
በክልሉ የአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ተኪ ምርቶችን ለማምረት ታቅዷል
****
(ኢ ፕ ድ)

በ2016 በጀት ዓመት አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ተኪ ምርቶችን ለማምረት መታቀዱን የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በአማራ ክልል የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተጀመረ ጀምሮ በዘርፉ በርካታ ውጤቶችን ማስገኘት እንደቻለ ተገልጿል፡፡ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ተፈሪ ታረቀኝ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አዳዲስ የሀገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስተሮችን መሳብ፣ የተኪ ምርቶችን ምርት ማሳደግ፣ ነባር ኢንዱስትሪዎች ላይ ያሉ ማነቆዎችን መፍታት የሚሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጓል፡፡

በንቅናቄው በ2015 በጀት ዓመት በአጠቃላይ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ በተኪ ምርት በማዘጋጀት የውጭ ምንዛሬን ማዳን የተቻለ ሲሆን፤ በ2016 በጀት ዓመት በተኪ ምርቶች አማካኝነት ከአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113230
የውሃ ሀብት ልማትንና አጠቃቀምን በማዘመን ከኢኮኖሚ ችግሮች ለመውጣት ትኩረት ያሻል
*****
(ኢ ፕ ድ)

የውሃ ሀብት ልማትንና አጠቃቀምን በማዘመን ከኢኮኖሚ ችግሮቻችን ለመላቀቅ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ምህንድስና መምህርና ተመራማሪ በፕሮፌሰር መኮንን አያና አስታወቁ፡፡

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ምህንድስና መምህርና ተመራማሪ በፕሮፌሰር መኮንን አያና በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ የውሃ ሀብት ዝናብ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ይህን በዝናብ ጥገኛ የሆነ የውሃ ሀብት አጠቃቀምን በማዘመን ከኢኮኖሚ ችግሮች ለመውጣት ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የውሃ ሀብትና የምግብ ሰብል የማምረት አቅማችን ዝናብ ላይ የተመሠረተ ነው ያሉት ፕሮፌሰሩ፤ ይህን በዝናብ ላይ የተመሠረተ በውሃ ሀብታችን በልማትና አጠቃቀሙን በማዘመን ከብዙ ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻችን መውጣት ይገባል ብለዋል፡፡

ውሃን በትክክል የማልማት አቅም በመገንባት ከብዙ ችግሮች መላቀቅ የሚቻል መሆኑን ተገንዝቦ በልዩ ትኩረት መሥራት እንደሚያስፈልግ አመልክተው፤ በውሃ ዙሪያ የሚሠሩ ተቋማትን.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113231
በኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሁለት ሺህ 802 ጨረታዎች ወጥተዋል
*****
(ኢ ፕ ድ)

በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ሁለት ሺህ 802 ጨረታዎች መውጣታቸውን የግዢና ንብረት ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ 161 የፌዴራል ተቋማት በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ግዢ ለመፈጸም ዕቅድ ማቅረባቸውም ተጠቁሟል፡፡

የግዢና ንብረት ባለሥልጣን ኤሌክትሮኒክስ ግዢ ላይ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ትናንት ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ የተገኙት የግዢና ንብረት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀጂ ኢብሳ እንደገለጹት፤ በተያዘው በጀት ዓመት የፌዴራል መሥሪያ ቤቶች ግዢ ሙሉ ለሙሉ በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ብቻ ይፈጸማል። በዚህ መነሻነትም በኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሁለት ሺህ 802 ጨረታዎች ወጥተዋል፡፡

ከ 169 የፌዴራል ተቋማት 161 ተቋማት በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ግዢ ለመፈጸም ዕቅድ ማቅረባቸውን ጠቁመው፤ ቀሪዎቹ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሥርዓቱን.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113251
ሚኒስቴሩ ነባርም ሆኑ አዲስ ነጋዴዎች ፈቃድ እንዲወስዱ አሳሰበ
****
(ኢ ፕ ድ)

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጫት የወጪ ንግድ ሥራ ፈቃድ አውጥተው የሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎችም ሆኑ ወደ ንግዱ መግባት የሚፈልጉ ነጋዴዎች ሚኒስቴሩ ባዘጋጀው አዲስ የቅድመ ፈቃድ ብቃት መስፈርት መሠረት እስከ ህዳር 15 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ፈቃድ እንዲወስዱ አሳሰበ፡፡

ኢትዮጵያ ከጫት ምርት የምታገኘው የውጭ ምንዛሪ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን በመግለጫው ያስታወቀው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፤ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ነጋዴዎች ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ በመላካቸው፣ የንግድ ሥራ ፈቃድን ለሌላ ወገን በማስተላለፍ ሥራ ላይ መሳተፋቸውና፣ የኮንትሮባንድ ንግድ ከልክ በላይ መስፋፋት የጫት ወጪ ንግድ ገቢ በእጅጉ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113252
የዘውዲቱ ሆስፒታል ማስፋፊያ ግንባታ በአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር እየተከናወነ ነው
***
(ኢ ፕ ድ)

የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ማስፋፊያ ፕሮጀክት በአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር እየተከናወነ እንደሚገኝ የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ማስፋፊያ ግንባታው 33 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱ ተገልጿል፡፡

በትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተወካይ አርክቴክት ነጋሽ መሐመድ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የዘውዲቱ ሆስፒታል ማስፋፊያ የሆስፒታሎችን ግንባታ ደረጃ ባሟላ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል።

የሆስፒታሉ የማስፋፊያ ፕሮጀክት በአንድ ሺህ ስምንት መቶ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ እየተከናወነ መሆኑን የገለጹት አርክቴክት ነጋሽ፤ ከአንድ ዓመት በፊት የተጀመረው የማስፋፊያ ግንባታው አፈጻጸም ከ33 ነጥብ ሶስት በመቶ በላይ መድረሱን አስታውቀዋል።

የግንባታው ሂደት አምስተኛ ወለል ላይ መድረሱን የገለጹት ተወካዩ፤ ግንባታው ስምንት ወለሎች የሚኖሩት በመሆኑ ቀሪ ሦስት ወለሎችን ሥራ በፍጥነት....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113253
የወተት ምርትን ለማሳደግ የሚረዳ የዝርያ ማሻሻያ መመሪያ ተግባራዊ ሊደረግ ነው
*****
(ኢ ፕ ድ)

የወተት ምርትን ለማሳደግ የሚረዳ ሀገር አቀፍ የወተት ላም ዝርያ ማሻሻያ መመሪያ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሚኒስቴሩ የእንስሳትና ዓሣ መሪ ሥራ አስፈጻሚና የወተት ሀብት ልማት ዴስክ ኃላፊ አቶ ለማ ገመዳ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የወተት ምርትን ለማሳደግ የሚረዳ ወጥ የሆነ ሀገር አቀፍ የወተት ላም ዝርያ ማሻሻያ መመሪያ ተዘጋጅቷል።

የወተት ምርት ላይ ያተኮረ የሥነ-ተዋልዶ ባዮቴክኖሎጂ ዘዴዎች አተገባበር የሚል መመሪያ በማዘጋጀት ለተለያዩ ክልሎች መላኩን አመላክተዋል። መመሪያውን ለማዘጋጀት አንድ ዓመት ያክል ጊዜ የወሰደ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ለማ፤ መመሪያው ከክልል እስከ ወረዳ ተግባራዊ እንዲሆን ለ300 ባለሙያዎች ሥልጠና ተሰጥቷል ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ለማ ገለጻ፤ ከዚህ ቀደም በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ የወተት ላም ዝርያ ማሻሻያ መመሪያ ባለመኖሩ የወተት ምርትን በሚፈለገው መጠን ማሳደግ አልተቻለም፡፡ አሁን የተዘጋጀው መመሪያ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=113254
አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከተሰናባቹ የተመድ የልማት ፕሮግራም ተወካይ ቱርሃን ሳልህ ጋር ተወያዩ
******
(ኢ ፕ ድ)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ቆይታቸው ካጠናቀቁት የተመድ የልማት ፕሮግራም ተወካይ ቱርሃን ሳልህን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

የተመድ የልማት ፕሮግራም ተወካይ ቱርሃን ሳልህ በበኩላቸው፤ ድርጅቱ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እና ከብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ጋር በአቅም ግንባታ ላይ በቅርበት ሲሰራ መቆየቱን በውይይቱ ተገልጿል።

የተመድ የልማት ፕሮግራም በአገሪቱ የተለያዩ ተቋማት አቅም በማሳደግ ረገድ ያለውን ሚና አሰታወሰው፣ መንግሥት ከተመድ የልማት ፕሮግራም (UNDP) ጋር ላለው ግንኙነት ትልቅ ቦታ እንደሚሰጥ አምባሳደሩ ገልጸዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ የተመድ የልማት ፕሮግራም በኢትዮጵያ ከአራት ዓመታት በላይ በተለያዩ ተቋማት አቅም ግንባታ ላይ ሲሰሩ የቆዩትን ቱርሃን የግል አመራር አድንቀው ለቀጣይ የስራ ጊዜ መመኘታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም