Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#ዲፕሎማሲያችን_ለብሔራዊ_ጥቅማችን

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጀት ጋር በመተባበር "ዲፕሎማሲያችን ለብሔራዊ ጥቅማችን" በሚል መሪ ሀሳብ በሳይንስ ሙዚየም ያዘጋጀው የፎቶግራፍ አውደርዕይ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መጎብኘቱን ቀጥሏል።

በዛሬው ዕለት ከሆለታ ከተማ ሳደሞ ቀበሌ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተወጣጡ ተማሪዎች፣ ከከፍተኛ 12 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የመጡ ተማሪዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስተባባሪነት ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የተወከሉ ሰራተኞች አውደርዕዩን እየጎበኙ ይገኛሉ።

በተስፋ ፈሩ
የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም
የመሪዎችና የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔዎችን በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት አድርጎ ወደ ሥራ መግባቱን ግብረ ኃይሉ አስታወቀ
*******
(ኢ.ፕ.ድ)

37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 44ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት አድርጎ ወደ ሥራ መግባቱን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ።

የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብረ ኃይል እስከአሁን ድረስ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከናወኑ የፀጥታ ስራዎች ስኬታማ መሆናቸውን ገምግሞ፤ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔም በሰላም እንዲጠናቀቅ በርካታ የፀጥታ ኃይል አሰማርቶ በቴክኖሎጂ የታገዘ የፀጥታና ደኅንነት ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ ገልጿል።

በተከታታይ እየተካሄደ ያለው የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ የተቀናጀ ኦፕሬሽን አዲስ አበባ ከተማ ፍፁም ሰላማዊ ሆና እንድትቀጥል ያስቻለና አሁን ላይም የከተማዋ ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ መቀጠሉን በግምገማ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለጫው አመላክቷል።

ግብረ-ኃይሉ ባካሄደው ግምገማ እስከአሁን ለተገኘው ሰላም እና በተካሄደው ኦፕሬሽን ለተገኘው ውጤት የህዝቡ ተሳትፎ ከፍተኛ ነበር ብሏል መግለጫው።

አዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካ ሕብረት እና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ በመሆኗ ፀጥታዋ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል ግብረ-ኃይሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ መግለጫው አንስቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እንደ ሀገር ሁሉም የፀጥታ መዋቅር የሚመለከተውን የሥራ ድርሻ ወስዶ አካባቢውን ፍፁም ሰላማዊ ለማድረግ በኃላፊነትና በተጠያቂነት የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ መግለጫው ጨምሮ ገልጿል።

በጉባዔው ላይ የሚታደሙ እንግዶችን በኢትዮጵያዊ ወግና ባህል በመቀበል እና በማስተናገድ በቆይታቸው ጊዜ በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ፤ ካረፉባቸው ሆቴሎች ወደ መሰብሰቢያ አዳራሽ በሚሄዱበት ወቅት ሰላም ወዳዱ ሕዝባችን በባለቤትነት የሚጠበቅበትን የዜግነት ድርሻውን በኃላፊነት እንዲወጣና ለፀጥታ አካላት እያደረገ ያለውን ቀና ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል።

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል
የካቲት 05 ቀን 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለህዝብ እይታ ክፍት ሆኗል
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ/ር ) በይፋ የተመረቀው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ ለህዝብ እይታ ክፍት ሆኗል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማችን ነዋሪዎች ከዛሬ ጀምሮ መታሰቢያውን እንዲጎበኙ ባደረጉት ጥሪ መሰረት ነዋሪዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ፡፡

በጉብኝቱ የተሳተፉ ነዋሪዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያ ድሉን በሚመጥን መልኩ መገንባቱን ገልፀው ሌሎችም ሙዚየሙን በአካል በመጎብኘት የጋራ ታሪካችን የሆነውን ዓድዋን በተጨባጭ እንዲገነዘቡ ጥሪ አቅርበዋል::

የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከአፋሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋር ተወያዩ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃመት ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።
አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ፣ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት በማውሳት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትን በአባልነት እና በአስተናጋጅነት ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
ሙሳ ፋኪ አምባሳደር ታዬ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የተሰማቸው ደስታ ገልፀው ፤ ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ በተለይ፣በአፍሪካ ፀጥታ እና መረጋጋትን በማስፈን ረገድ ያላትን ሚና ክቡር ሙሳ ፋቂ ያደነቁ ሲሆን ተጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም
የኢጋድ ዋና ፀሃፊ አዲስ አበባ ገቡ
************
(ኢ.ፕ.ድ )
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥት (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በአፍሪካ ህብረት 44ኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ እና በ37ኛው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ዋና ፀሃፊው ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።
የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም
በመዲናዋ ለኮንስትራክሽን እና ለጭነት ተሽከርካሪዎች የተከለከሉ መንገዶች ይፋ ሆኑ
*****
(ኢ ፕ ድ)
ለአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የትራፊክ ፍሠቱን የተሳለጠ ለማድረግ እንዲቻል ለኮንስትራክሽንና ለጭነት ተሽከርካሪዎች የተከለከሉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ቀደም ሲል በከተማው ላይ በደንብ ተላላፊ አሽከርካሪዎች የተከሰተውን ተመሣሣይ ጥፋት መነሻ አድርጎ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልእክት ማስተላለፋ ይታወሳል።

በመሆኑም የትራፊክ ህግና ደንብን በማስከበር የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ከመከላከል ባሻገር ጤናማ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር እንዲሁም በመዲናዋ በቀጣይ ቀናት  ለሚካሔደው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ የፀጥታ አካላት ለሚያከናውኑት የፀጥታ ስራ አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር እንዲቻል ከዚህ በታች በተገለፁት መንገዶች፤

👉 ቦሌ ድልድይ አካባቢ

👉 ከቦሌ ድልድይ እሰከ ሩዋንዳ ድልድይ

👉 ከቦሌ ድልድይ በወሎ ሰፈር  ደንበል አደባባይ እስከ መስቀል አደባባይ

👉 ከመስቀል አደባባይ እስከ አራት ኪሎ

👉 ከኡራኤል አደባባይ እስከ አትላስ ሆቴል

👉 ከኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል እስከ ልማት ባንከ

👉 ከአራት ኪሎ እስከ አምባሳደር መናፈሻ

👉 ከብሄራዊ ቴአትር እስከ ሜክሲኮ አደባባይ

👉 ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ አፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት እና

👉 ከአፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት እስከ ቡልጋሪያ ማዞሪያ ባሉት መንገዶች ላይ ተለዋጭ መረጃ እስኪተላለፍ ድረስ የኮንስትራክሽን ከባድ እና የጭነት ተሽከርካሪንዎችን ማሽከርከርም ሆነ ማቆም የተከለከለ መሆኑን በመገንዘብ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ አሳስቧል።

ይህንን ተላልፈው በተገኙት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

የካቲት 5 ቀን 2016 ዓም
ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከነገ የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል
*****
(ኢ ፕ ድ)
ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከነገ የካቲት 6 ጀምሮ እሰከ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በ84 የፈተና ማዕከላት
እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሰታወቀ።

የፈተና አሰጣጡን ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅ ከዩኒቨርስቲዎች ታዛቢዎች መመደባቸው ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጅና(ዶ/ር) የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና በ2015 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በሁሉም የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች ተግባራዊ መደረጉን ጠቅሰው በመውጫ ፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ ቁጥር 919/2014 ድንጋጌ መሠረት ፈተናው በዓመት ሁለት ጊዜ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

የሁለተኛ ዙር ፈተናው በ47 የመንግስት ተቋማት በ84 የፈተና ማዕከላት ይሰጣል።

በመንግስትና ግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149 ሺህ 145 ተፈታኞች በ204 የፈተና ፕሮግራሞች እንደሚፈተኑ ተናግረዋል።

የመውጫ ፈተና አሰጣጡ ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል በሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ታዛቢዎችን መመደባቸውን ገልጸዋል።

ታዛቢዎቹ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተመለመሉ መሆኑን ከትምህርት ሚኒስቴርን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም
በጅግጅጋ ከተማ ግንባታውን ያስጀመሩት የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከጥቂት ወራት በፊት በእህት ከተማችንና በምስራቋ ጮራ በጅግጅጋ ከተማ ግንባታውን ያስጀመሩት የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ተጠናቅቆ ለከተማዋ አቅመደካማ ነዋሪዎች አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ መሃመድ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እያደረገ የሚገኘው ስራቸውን በማስፋፋት በጅግጅጋ ከተማ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል እንዲገነባ ስላደረጉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል::

የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም