የዓድዋ ድል መታሰቢያ ለህዝብ እይታ ክፍት ሆኗል
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ/ር ) በይፋ የተመረቀው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬ ለህዝብ እይታ ክፍት ሆኗል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማችን ነዋሪዎች ከዛሬ ጀምሮ መታሰቢያውን እንዲጎበኙ ባደረጉት ጥሪ መሰረት ነዋሪዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ፡፡
በጉብኝቱ የተሳተፉ ነዋሪዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያ ድሉን በሚመጥን መልኩ መገንባቱን ገልፀው ሌሎችም ሙዚየሙን በአካል በመጎብኘት የጋራ ታሪካችን የሆነውን ዓድዋን በተጨባጭ እንዲገነዘቡ ጥሪ አቅርበዋል::
የካቲት 5 ቀን 2016 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከአፋሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋር ተወያዩ
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃመት ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።
አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ፣ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት በማውሳት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትን በአባልነት እና በአስተናጋጅነት ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
ሙሳ ፋኪ አምባሳደር ታዬ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የተሰማቸው ደስታ ገልፀው ፤ ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ በተለይ፣በአፍሪካ ፀጥታ እና መረጋጋትን በማስፈን ረገድ ያላትን ሚና ክቡር ሙሳ ፋቂ ያደነቁ ሲሆን ተጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የኢጋድ ዋና ፀሃፊ አዲስ አበባ ገቡ
************
(ኢ.ፕ.ድ )
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥት (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በአፍሪካ ህብረት 44ኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ እና በ37ኛው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ዋና ፀሃፊው ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

በመዲናዋ ለኮንስትራክሽን እና ለጭነት ተሽከርካሪዎች የተከለከሉ መንገዶች ይፋ ሆኑ
*****
(ኢ ፕ ድ)
ለአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የትራፊክ ፍሠቱን የተሳለጠ ለማድረግ እንዲቻል ለኮንስትራክሽንና ለጭነት ተሽከርካሪዎች የተከለከሉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ቀደም ሲል በከተማው ላይ በደንብ ተላላፊ አሽከርካሪዎች የተከሰተውን ተመሣሣይ ጥፋት መነሻ አድርጎ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልእክት ማስተላለፋ ይታወሳል።
በመሆኑም የትራፊክ ህግና ደንብን በማስከበር የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ከመከላከል ባሻገር ጤናማ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር እንዲሁም በመዲናዋ በቀጣይ ቀናት ለሚካሔደው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ የፀጥታ አካላት ለሚያከናውኑት የፀጥታ ስራ አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር እንዲቻል ከዚህ በታች በተገለፁት መንገዶች፤
👉 ቦሌ ድልድይ አካባቢ
👉 ከቦሌ ድልድይ እሰከ ሩዋንዳ ድልድይ
👉 ከቦሌ ድልድይ በወሎ ሰፈር ደንበል አደባባይ እስከ መስቀል አደባባይ
👉 ከመስቀል አደባባይ እስከ አራት ኪሎ
👉 ከኡራኤል አደባባይ እስከ አትላስ ሆቴል
👉 ከኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል እስከ ልማት ባንከ
👉 ከአራት ኪሎ እስከ አምባሳደር መናፈሻ
👉 ከብሄራዊ ቴአትር እስከ ሜክሲኮ አደባባይ
👉 ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ አፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት እና
👉 ከአፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት እስከ ቡልጋሪያ ማዞሪያ ባሉት መንገዶች ላይ ተለዋጭ መረጃ እስኪተላለፍ ድረስ የኮንስትራክሽን ከባድ እና የጭነት ተሽከርካሪንዎችን ማሽከርከርም ሆነ ማቆም የተከለከለ መሆኑን በመገንዘብ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ አሳስቧል።
ይህንን ተላልፈው በተገኙት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡
የካቲት 5 ቀን 2016 ዓም

ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከነገ የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል
*****
(ኢ ፕ ድ)
ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከነገ የካቲት 6 ጀምሮ እሰከ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በ84 የፈተና ማዕከላት
እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሰታወቀ።
የፈተና አሰጣጡን ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅ ከዩኒቨርስቲዎች ታዛቢዎች መመደባቸው ተገልጿል።
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጅና(ዶ/ር) የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና በ2015 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በሁሉም የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች ተግባራዊ መደረጉን ጠቅሰው በመውጫ ፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ ቁጥር 919/2014 ድንጋጌ መሠረት ፈተናው በዓመት ሁለት ጊዜ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
የሁለተኛ ዙር ፈተናው በ47 የመንግስት ተቋማት በ84 የፈተና ማዕከላት ይሰጣል።
በመንግስትና ግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149 ሺህ 145 ተፈታኞች በ204 የፈተና ፕሮግራሞች እንደሚፈተኑ ተናግረዋል።
የመውጫ ፈተና አሰጣጡ ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል በሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ታዛቢዎችን መመደባቸውን ገልጸዋል።
ታዛቢዎቹ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተመለመሉ መሆኑን ከትምህርት ሚኒስቴርን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በጅግጅጋ ከተማ ግንባታውን ያስጀመሩት የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከጥቂት ወራት በፊት በእህት ከተማችንና በምስራቋ ጮራ በጅግጅጋ ከተማ ግንባታውን ያስጀመሩት የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ተጠናቅቆ ለከተማዋ አቅመደካማ ነዋሪዎች አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ መሃመድ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እያደረገ የሚገኘው ስራቸውን በማስፋፋት በጅግጅጋ ከተማ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል እንዲገነባ ስላደረጉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል::
የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም

ለአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ተሳታፊ እንግዶች የኃይል አቅርቦቱን አስተማማኝ ለማድረግ ዝግጅት ተደርጓል
******************
(ኢ.ፕ.ድ)
ለ37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 44ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ ያለ ምንም የኃይል መቆራረጥ እንዲጠናቀቅ ለማድረግ የኃይል መስመር የቅድመ ጥገኛ እና ማሻሻያ ስራዎች መከናወናቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
የተሰራው የኃይል መስመር የቅድመ ጥገኛ ስራ ለህብረቱ የስብሰባ አዳራሽ የኃይል አቅርቦት የሚሰጡ አዲስ ሴንተር 5፣ 11፣ 4፣ 15 እና 6 የሚባሉ የኃይል መስመሮች ላይ ያረፉ የዛፍ ቅርንጫፎችን የማስተካከል፣ ያረጁ ፖሎችን የመቀየር እና በጉዳት ምከንያት አገልግሎት አቁሞ የነበረ የመሬት ዉስጥ የኃይል ማስተላለፊያ መስመርን የመጠገን እና ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ እንዲገባ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡
ለአፍሪካ ህብረት እና አካባቢዉ የኃይል አቅርቦት ይሰጥ የነበረ ትራንስፎርመር በባለ 315 ኬቪኤ ትራንስፎርመር የመቀየር እና ተሸከርካሪ በቀላሉ በማያገኘዉ እና ለይታ አመቺ በሆነ መልኩ የማስቀመጥ ስራ ተከናዉኗል፡፡
በአፍሪካ ህብረት ዙሪያ እንዲሁም አካባቢው ላሉ ድርጅቶች እና ለመንገድ መብራት ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚሰጠዉ ”አዲስ ሴንተር አስራ አንድ” የተባለ መስመር በተመሳሳይ የቅድመ ጥገና ስራዎች የተሰሩለት ሲሆን በመንገድ አካፋይ ዉስጥ ባሉ ዛፎች መካከል የሚሄደዉ መስመር ነፃ ወደሆነ ቦታ የማዛወር ስራ ተከናውኗል፡፡
በከተማዋ የህብረቱ ተሰብሳቢ እንግዶች መዳረሻ ለሆኑ ቦታዎች የኃይል አቅርቦቱን አስተማማኝ ለማድረግ ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ሲሆን ከልማት ባንክ እስከ ካዛንቺስ መብራት እንዲሁም ሜክሲኮ አካባቢ በአዲስ መልክ ለሚሰራዉ የእግረኞች መንገድ ኤሌክትሪክ መስመር ተሸካሚ ፖሎችን የማንሳት ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
በተጨማሪም ለስብሰባዉ አገልግሎት የሚሰጡ አራት ግዙፍ ስክሪኖች ከኢትዮ ቴሌኮም በቀረበ ጥያቄ መሰረት ባለ 200 ኬቪኤ ትራንስፎርመሮችን የመትከል ስራ ተከናውኗል፡፡

ከየካቲት 8 እስከ 11 ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከለከለ
********
(ኢ.ፕ.ድ)
በመዲናዋ ከየካቲት 8 ቀን ጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት 2 ሰዓት ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር መከልከሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።
ሞተር ብስክሌት የማሽከርከር ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን የማያካትት መሆኑን የጠቆመው ቢሮውና የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ቢሮው አሳስቧል፡፡