Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኢትዮ-ቱርክ የኢንቨስትመንትና ቢዝነስ ፕሮሞሽን መድረክ እየተካሄደ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮ-ቱርክ የኢንቨስትመንትና ቢዝነስ ፕሮሞሽን መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በፎረሙ ላይ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነርና የተርክየ ዛካርያ ከተማ 23 የንግድ ባለቤቶች ተገኝተዋል።

በፎረሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀና አርአያ ስላሴ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያና ተርክየ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት አላቸው።

ከ100 በላይ የተርክየ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ተሰማርተው ይገኛሉ። ውጤታማም ናቸው።

ተጨማሪ ኢንቨስተሮች ቢመጡ ተጠቃሚ ይሆናሉ ያሉት ኮሚሽነሯ፣ ኢትዮጵያ ላለፉት አምስት አመታት የኢቨስትመንት ፖሊሲዋን አሻሽላለች። የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እየተካሄደ መሆኑንም አንስተዋል።

ኢትዮጵያ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት አለት ያሉት ኮሚሽነር ሀና፣ የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ የንግድ ልውውጥ ማደግ፣ የሰለጠነ ወጣት የሰው ሃይል መኖር፣ የኢትዮጵያ መንግስት ለንግድና ኢንቨስትመንት የሰጠው ትኩረትና ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እንደ መግቢያ በር መሆኗ በኢትዮጵያ ለሚሰማሩ ኢንቨስተሮች ተጨማሪ እድሎች ናቸው ብለዋል።

በኢትዮጵያ የተርክየ አምባሳደር እና የአፍሪካ ህብረት ቋሚ ተወካይ በረክ ባራን በበኩላቸው፣ የተርክየ መርህ የጋራ ተጠቃሚነት ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያና ተርክየ የቆየና ትልቅ የዲፕሎማሲ ግንኙነት አላቸው። የሁለቱን ሀገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት በንግድ ልውውጥ ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ጥንታዊ የዲፕሎማሲ መዲና ናት ያሉት አምባሳደሩ፣ በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የዲፕሎማሲ መዲና መሆኗን፤ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኤምባሲና አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ እ ንደሆነችም ገልጸዋል።

ይህም ተርክየ ከአፍሪካ ጋር ለመስራት ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው አንስተዋል።

በሞገስ ጸጋዬ
የካቲት 7 ቀን 2016 ዓም
በዞኑ ከ3 ነጥብ 6 ቢሊዮን በላይ ብር የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷል
***************
(ኢ ፕ ድ)
በዞኑ ከ3 ነጥብ 6 ቢሊዮን በላይ ብር የኢንቨስትመንት ፈቃድ ላስመዘገቡ ባለሀብቶች ፈቃድ መሰጠቱን የወላይታ ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደሥራ የማይገቡ ኢንቨስተሮች ለልማት የተሰጣቸውን መሬት እንደሚነጠቁ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፡፡

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙዔል ፎላ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በተያዘው ዓመት ስድስት ወራት ውስጥ በዞኑ ከ3 ቢሊዮን 680 ሚሊዮን ብር በላይ ያስመዘገቡ ኢንቨስትመንቶች ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡

እነዚህ ኢንቨስትመንቶች ፈቃድ እንዲያገኙ ከሚመለከተው አካል ጋር በጋራ ተሠርቷል፡፡

ፈቃድ የተሰጣቸው የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች 53 የሚደርሱ መሆናቸውን የተናገሩት አስተዳዳሪው፤ ከኢንቨስትመንቶቹ ውስጥ ወደሥራ የገቡ እና በሂደት ላይ የሚገኙ ስለመኖራቸውም አብራርተዋል፡፡ ወደ ዞኑ የሚፈሰው የኢንቨስትመንት ፍላጎት ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል ሲሉም አብራርተዋል፡፡

ኢንቨስትመንቶቹ በገጠር እርሻ፤ በከተማ አገልግሎት ዘርፍ፣ በአነስተኛና መካከለኛ አምራች እና በከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ ጭምር የተሠማሩ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል፡፡ የአካባቢው ተወላጅ ዲያስፖራዎች አብዛኛውን የኢንቨስትመንት ክፍል እንደሚሸፍኑም

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=120887
በአዲስ አበባ በስድስት ወራት ከሁለት ሺህ 800 በላይ የትዳር ፍቺ ተመዝግቧል
************
(ኢ.ፕ.ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 6 ወራት ሁለት ሺህ 813 ፍቺዎች እና 16 ሺህ 933 ጋብቻዎች መመዝገባቸውን የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ለኢፕድ በላኩት መግለጫ እንደገለጹት፤ ዘንድሮ በ6 ወራት ብቻ ከተመዘገበው ጠቅላላ ኩነት 181 ሺህ 983 ልደት፣ 16 ሺህ 933 ጋብቻ፣ 2 ሺህ 813 ፍቺ እና 8 ሺህ 761 ሞት ተመዝግቧል።

በሳሙኤል ወንድወሰን
የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ያልተፈቀደ አገልገሎት ሲሰጡ በተገኙ 125 ማሳጅ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ
******
(ኢ ፕ ድ)

ባለፉት ስድስት ወራት በመዲናዋ ከተቀመጠው የአገልግሎት ደረጃ ዉጪ አገልግሎት ሲሰጡ በተገኙ 125 ማሳጅ ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን የማሳጅ ቤቶችን ህጋዊነት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሰፋ ተሬሳ እንደተናገሩት፤ ማሳጅ ቤቶች ለማህበረሰቡ መጤ ባህል ከማውረስ ባሻገር አምራቹን ዜጋ ወዳልተፈለገ መንገድ እንዲገባ እያደረጉ ናቸው።

በማሳጅ ቤቶች ላይ የሚደረገው የቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ እደሚቀጥል ገልጸዋል።

በባለስልጣኑ የምግብና ጤንነት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ሚሬሳ ሚዴቅሳ በወቅቱ እንደገለጹት ባለፉት ስድስት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ161 ማሳጅ ቤቶች ላይ ቁጥጥርና የክትትል ስራ ተሰርቷል።

በቁጥጥር ስራው 125 ማሳጅ ቤቶች ከተቀመጠው የአገልግሎት ደረጃ ዉጪ አገልግሎት ሲሰጡ የተገኙ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 76 የጹሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሁም 49 ማሳጅ ቤቶች እንዲታሸጉ ተደርጓል ብለዋል።

በአማን ረሺድ
የካቲት 7 ቀን 2016 ዓም
የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ‼️

#ቀዳማዊ_ኃይለሥላሴ

የግንቦት 1955 ዓ.ም.32 መስራች አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።

ለዚህ ድርጅት እውን መሆንም ኢትዮጵያ በመሪዋ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የመሪነት ሚና ተጫውታለች።

በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱ አማረኛ ነበር።
ኢትዮጵያና አንጎላ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ
***
(ኢ.ፕ.ድ)

ከ44ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን ኢትዮጵያና አንጎላ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ እና የአንጎላው አቻቸው ቴት አንቶኒዮ ተፈራርመዋል።

በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ፍሰሀ ሻውል እንደገለፁት፤ በሀገራቱ መካከል የተፈረመው ስምምነት ሁለት አይነት ይዘት አለው።

የመጀመሪያው ለተቋማት ህጋዊ ማዕቀፍ የሚሰጥ አጠቃላይ የትብብር ስምምነት መሆኑን ጠቅሰው ሁለተኛው የፓለቲካ ምክክር ስምምነት መፈራረማቸውን ገልጸዋል።

ሁለቱ ሀገራት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተለያዩ መስኮች ለመተባበር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር በማድረግ ወደ ፊት ተጨማሪ ስምምነት ለማድረግ መስማማታቸውም ተገልጿል።

በተጨማሪም አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከዝምባብዌ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ፌድሪክ ሻቫ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን መድረክን ተባብሮ ለማዘጋጀት መመካከራቸውን ጠቅሰው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን አምባሳደር ታዬ ገልጸዋል።

ሁለቱ ሀገራት በግብርና ቱሪዝም በሌሎች ዘርፎችም ለመስራት መነጋገራቸውም ተገልጿል።

44ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።

በማርቆስ በላይ
የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ‼️

#አህመድ_አሂድጆ

ኢትዮጵያ “የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩትን የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ በማገናኘትና ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም እንዲመጡ አድርጋለች።

በዚሁ መሰረት ግንቦት 1955 ዓ.ም. 32 መስራች አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።

ለዚህ ድርጅት እውን መሆን ፊርማቸውን ካኖሩ አገራት መካከል የካሜሮን የቀድሞ ፕሬዝዳንት አህመድ አሂድጆ አንዱ ናቸው።

በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱም አማረኛ ነበር።
መልካም ዕድል
የሐሮማያ ሐይቅ ተስፋና ስጋት
**************
(ኢ ፕ ድ)
አካባቢው ማራኪ ነው፡፡ በሐሮማያ ሀይቅ ዙሪያ ያሉ እርሻዎች አካባቢውን አረንጓዴ ስጋጃ የተነጠፈ አስመስለውታል፡፡
የአዕዋፋት ድምፅ፣ የጀልባዎች ቀዘፋና የአካባቢው ሥነ ምሕዳር የጎብኝዎችን ቀልብ ይስባል፡፡

በ1996 ዓ.ም ሐይቁ በዓይናችን እያየነው ደረቀ የሚለው ሐሮማያ ሐይቅ አጠገብ በምትገኘው ማያ ከተማ ተወልዶ ያደገው አቶ ረመዳን አሊ፤ በወቅቱ ሐይቁ ሲደርቅ እናትና አባታችንን እንዳጣን ሁላችንም የአካባቢው ነዋሪዎች አዘንን፣ ተከፋን፣ ዳግመኛም ሐይቁ ይመለሳል ብለንም አላሰብንም ይላል፡፡
የአምላክ ሥራ አይታወቅም፤ ያልገመትነው ነገር ተከሰተ፡፡

ሐሮማያ ሐይቅ ከ17 ዓመታት በኋላ ተመልሶ መጣ፡፡ እኛም ዳግም እንደተወለደ ሰው ተደሰትን፣ ጨፍርን፣ እንደ ዓይናችን ብሌን የምናየውን ሐይቅ በደስታ እንባ ተቀበልነው ብሏል፡፡

2012 ዓ.ም ኃይለኛ ዝናብ በመዝነቡ ሐይቁ ተመልሶ እንደመጣ የሚያስታውሰው አቶ ረመዳን፤ በአሁኑ ጊዜም 360 ወጣቶች ተደራጅተው ሐይቁን በማስጎብኘትና ዓሳ በማጥመድ ሥራ ላይ ተሠማርተው እንደሚገኙ ነግሮናል።

ሐይቁ በመመለሱ ደስተኞች ነን። እኛም ሆነ ልጆቻችን ከ17 ዓመታት በኋላ ወደ ቀድሞ ሥራችን ተመልሰናል

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=120863
መንግሥታዊ ያለሆኑ ድርጅቶች ለ28 አቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት አበረከቱ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
ሀቢታት ፎር ሂውማኒቲ ኢትዮጵያና ኤልጂ ኤሌክትሮኒክስ በትብብር በየካና ጉለሌ ክፍለከተሞች ለሚገኙ 28 አቅመ ደካሞች የመኖሪያቤቶችና ልዩ ልዩ አገልግሎት መስጫዎችን አበረከቱ።

በመርሀግብሩ የተገኙት በኢትዮጵያ የኮሪያ አምባሳደር ሚስተር ጃንግ ካንግ እንዳሉት ኢትዮጵያ ለኮሪያ የዋለችውን ነፍስ እስከመስጠት የደረሰ ውለታ አትረሳም።

አሁን ኮሪያ በተራዋ ከኢትዮጵያ ጋር የሚኖራትን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ድጋፎች የምትቀጥል ይሆናል።

የሀቢታት ፎር ሂውማኒቲ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ዳይሬክተርና የተቋሙ የአፍሪካ ህብረት ተወካይ አቶ ይጥና ተካልኝ እንዳሉት፤ ተቋሙ የኮሪያ ዘማች ቤተሰቦችን ጨምሮ ብዙዎችን ከጉስቁልና እንዲላቀቁ ያስቻለ ነው።

ተቋሙ ባለፉት 29 ዓመታት 165ሺህ ቤተሰቦችን ወይም 826ሺህ ሰዎችን ተጠቃሚ ማድረግ የቻለ ሲሆን በዛሬው ፕሮጀክትም 28 ቤቶችን ሰርቶ አስረክቧል።

በዳግማዊት ግርማ
የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ

#ማውረሥ_ያመጎ

ኢትዮጵያ “የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩትን የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ በማገናኘትና ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም እንዲመጡ አድርጋለች።

በዚሁ መሰረት ግንቦት 1955 ዓ.ም 32 መስራች አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።
ለዚህ ድርጅት እውን መሆን ፊርማቸውን ካኖሩ አገራት መካከል የቀድሞ የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ማውረሥ ያመጎ አንዱ ናቸው።

በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱም አማረኛ ነበር።
መብረቅ ክፍለጦር በወሰደው ርምጃ የሸኔ የሽብር ቡድኑ ዋና ዋና አመራሮቹ ተመቱ
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
መብረቅ ክፍለ ጦር ሰሞኑን ባደረገው ዘመቻ የአሸባሪው ሸኔ አመራሮችና አባላት ሲመቱ መገናኛ ሬዲዮን ጨምሮ በርካታ የጦር መሳሪያ እና ተተኳሽች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ ቄለም ፣ ግራይ ሶንካና አቦቴ አካባቢ የሸኔ ሽብር ቡድን ላይ በተሰነዘረ ማጥቃት ጃል አብዲ፣ ጃል ጉርሜሳ፣ ጃል በዳሳ ተስፋዬና ጃል ገመቹ የተባሉ አራት ዋና ዋና አመራሮቹ ተገድለዋል።

የመብረቅ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ሌተናል ኮሎኔል ንጉሴ ጥላሁን እንዳሉት፤ ከአመራሮቹ መደምሰስ ባለፈ በርካታ አባላቱ ሙት ሆነው በአካባቢው ይንቀሳቀስ የነበረው የሽብር ቡድኑ የመገናኛ ሬድዮ፣ መሳሪያና ተተኳሽ በመማረክ አቅሙን ማንኮታኮት ተችሏል።

ምክትል አዛዡ ጨምረው እንዳስረዱት ከመሳሪያና ተተኳሾች ባለፈ የተለያዩ ቁሳቁሶች የተማረኩበት ሲሆን በዚህኛው ዘመቻ በርካታ ሃይል ለማሰለፍ የሞከረው ሸኔ ከፍተኛ ምት ደርሶበታል።

ለሽብር ቡድኑ መደምሰስ የአካባቢው ማህበረሰብ ከክፍለ ጦሩ ጋር በቅንጅት መስራቱ ከፍተኛ ሚና እንደነበረው የክፍለጦሩ አመራሮች በአስተያየታቸው መግለጻቸውን ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
በትግራይ ክልል ለተከሠተው ድርቅ የተቀናጀ ርብርብ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
በትግራይ ክልል ለተከሰተው ድርቅ ሁሉም አካላት ችግሩን ለመሻገር በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ፡፡

በሰው፣ በእንስሳትና በእጽዋት ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን በምልከታ ማረጋገጡን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገልጿል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታ በተመለከተ በምልከታ ያረጋገጠውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በትግራይ ክልል ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ከፍተኛ ጉዳት ማስከተሉን መመልከቱን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢና የልዑካን ቡድኑን የመሩት ዲማ ነገዎ (ዶ/ር) አመልክተዋል፡፡

ሰብአዊ ችግሩን ክልሉ ብቻውን የሚወጣው ባለመሆኑ ሁሉም ወገኑን የሚታደግበት ሁኔታ መኖር አለበት ብለዋል፡፡

እናቶች፣ ሕጻናትና አዛውንቶች ከቀዬአቸው ተፈናቅለው በመጠለያ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡

አካባቢው ኮቪድ፣ የአምበጣ ወረርሽኝ፣ ሁለት ዓመትም በጦርነት ያሳለፈ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ሕዝቡ ችግር ውስጥ እንዳለ በመስክ ምልከታ፣ ተጎጂዎችን አመራሮችንና ገለልተኛ አካላትን በማነጋገር የችግሩን ስፋት መገንዘብ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም ሕዝቡ ወደ ቀዬው ተመልሶ እስኪቋቋም ድረስ ተከታታይና ዘላቂነት ያለው ድጋፍ ስለሚፈልግ ሁሉም አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዘላለም ግዛው
የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ‼️
#ግብጽ
#ጋማል_አብዱል_ናስር

ኢትዮጵያ “የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩትን የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ በማገናኘትና ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም እንዲመጡ አድርጋለች።

በዚሁ መሰረት ግንቦት 1955 ዓ.ም 32 መስራች አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።

ለዚህ ድርጅት እውን መሆን ፊርማቸውን ካኖሩ አገራት መካከል የቀድሞ የግብጽ ፕሬዝዳንት ጋማል አብዱል ናስር አንዱ ናቸው።

በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱም አማረኛ ነበር።
ኢትዮጵያና ሊቢያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
****
(ኢ ፕ ድ)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሊቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ ኢሳ ጋር በዛሬው እለት ተወያይተዋል።

ውይይቱ የተካሄደው ከአፍሪካ ህብረት 44ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን ነው ብሏል።

ሁለቱ ወገኖች ከዚህ ቀደም የነበሩ የግንኙነት አሰራሮችን ለመገምገምና የፖለቲካ ምክክር ስርዓት ለመፍጠር ተስማምተዋል።

በተጨማሪም በአቬሽን እና የስራ ስምሪት ዘርፎች ትብብርን ለማጠናከርም ከመግባባት ላይ ደርሰዋል።

የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
ለአፍሪካ ህብረት ጉባኤ መሪዎች አዲስ አበባ መግባት ጀመሩ
*****
(ኢ ፕ ድ)

የኮትዲቯር ምክትል ፕሬዝዳንት ቲሞኮ ሚዬሊ ኮኔ በ37ኛ የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ቦሌ አለማቀፍ አየርማረፊያ ሲደርሱም የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም አቀባበል አድርገውላቸዋል።

37ኛው የአፍሪካ ኅብረት አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ በመጪው ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም