Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
መልካም ዕድል
የሐሮማያ ሐይቅ ተስፋና ስጋት
**************
(ኢ ፕ ድ)
አካባቢው ማራኪ ነው፡፡ በሐሮማያ ሀይቅ ዙሪያ ያሉ እርሻዎች አካባቢውን አረንጓዴ ስጋጃ የተነጠፈ አስመስለውታል፡፡
የአዕዋፋት ድምፅ፣ የጀልባዎች ቀዘፋና የአካባቢው ሥነ ምሕዳር የጎብኝዎችን ቀልብ ይስባል፡፡

በ1996 ዓ.ም ሐይቁ በዓይናችን እያየነው ደረቀ የሚለው ሐሮማያ ሐይቅ አጠገብ በምትገኘው ማያ ከተማ ተወልዶ ያደገው አቶ ረመዳን አሊ፤ በወቅቱ ሐይቁ ሲደርቅ እናትና አባታችንን እንዳጣን ሁላችንም የአካባቢው ነዋሪዎች አዘንን፣ ተከፋን፣ ዳግመኛም ሐይቁ ይመለሳል ብለንም አላሰብንም ይላል፡፡
የአምላክ ሥራ አይታወቅም፤ ያልገመትነው ነገር ተከሰተ፡፡

ሐሮማያ ሐይቅ ከ17 ዓመታት በኋላ ተመልሶ መጣ፡፡ እኛም ዳግም እንደተወለደ ሰው ተደሰትን፣ ጨፍርን፣ እንደ ዓይናችን ብሌን የምናየውን ሐይቅ በደስታ እንባ ተቀበልነው ብሏል፡፡

2012 ዓ.ም ኃይለኛ ዝናብ በመዝነቡ ሐይቁ ተመልሶ እንደመጣ የሚያስታውሰው አቶ ረመዳን፤ በአሁኑ ጊዜም 360 ወጣቶች ተደራጅተው ሐይቁን በማስጎብኘትና ዓሳ በማጥመድ ሥራ ላይ ተሠማርተው እንደሚገኙ ነግሮናል።

ሐይቁ በመመለሱ ደስተኞች ነን። እኛም ሆነ ልጆቻችን ከ17 ዓመታት በኋላ ወደ ቀድሞ ሥራችን ተመልሰናል

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=120863
መንግሥታዊ ያለሆኑ ድርጅቶች ለ28 አቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት አበረከቱ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
ሀቢታት ፎር ሂውማኒቲ ኢትዮጵያና ኤልጂ ኤሌክትሮኒክስ በትብብር በየካና ጉለሌ ክፍለከተሞች ለሚገኙ 28 አቅመ ደካሞች የመኖሪያቤቶችና ልዩ ልዩ አገልግሎት መስጫዎችን አበረከቱ።

በመርሀግብሩ የተገኙት በኢትዮጵያ የኮሪያ አምባሳደር ሚስተር ጃንግ ካንግ እንዳሉት ኢትዮጵያ ለኮሪያ የዋለችውን ነፍስ እስከመስጠት የደረሰ ውለታ አትረሳም።

አሁን ኮሪያ በተራዋ ከኢትዮጵያ ጋር የሚኖራትን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ድጋፎች የምትቀጥል ይሆናል።

የሀቢታት ፎር ሂውማኒቲ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ዳይሬክተርና የተቋሙ የአፍሪካ ህብረት ተወካይ አቶ ይጥና ተካልኝ እንዳሉት፤ ተቋሙ የኮሪያ ዘማች ቤተሰቦችን ጨምሮ ብዙዎችን ከጉስቁልና እንዲላቀቁ ያስቻለ ነው።

ተቋሙ ባለፉት 29 ዓመታት 165ሺህ ቤተሰቦችን ወይም 826ሺህ ሰዎችን ተጠቃሚ ማድረግ የቻለ ሲሆን በዛሬው ፕሮጀክትም 28 ቤቶችን ሰርቶ አስረክቧል።

በዳግማዊት ግርማ
የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ

#ማውረሥ_ያመጎ

ኢትዮጵያ “የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩትን የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ በማገናኘትና ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም እንዲመጡ አድርጋለች።

በዚሁ መሰረት ግንቦት 1955 ዓ.ም 32 መስራች አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።
ለዚህ ድርጅት እውን መሆን ፊርማቸውን ካኖሩ አገራት መካከል የቀድሞ የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ማውረሥ ያመጎ አንዱ ናቸው።

በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱም አማረኛ ነበር።
መብረቅ ክፍለጦር በወሰደው ርምጃ የሸኔ የሽብር ቡድኑ ዋና ዋና አመራሮቹ ተመቱ
*****************
(ኢ.ፕ.ድ)
መብረቅ ክፍለ ጦር ሰሞኑን ባደረገው ዘመቻ የአሸባሪው ሸኔ አመራሮችና አባላት ሲመቱ መገናኛ ሬዲዮን ጨምሮ በርካታ የጦር መሳሪያ እና ተተኳሽች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ ቄለም ፣ ግራይ ሶንካና አቦቴ አካባቢ የሸኔ ሽብር ቡድን ላይ በተሰነዘረ ማጥቃት ጃል አብዲ፣ ጃል ጉርሜሳ፣ ጃል በዳሳ ተስፋዬና ጃል ገመቹ የተባሉ አራት ዋና ዋና አመራሮቹ ተገድለዋል።

የመብረቅ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ሌተናል ኮሎኔል ንጉሴ ጥላሁን እንዳሉት፤ ከአመራሮቹ መደምሰስ ባለፈ በርካታ አባላቱ ሙት ሆነው በአካባቢው ይንቀሳቀስ የነበረው የሽብር ቡድኑ የመገናኛ ሬድዮ፣ መሳሪያና ተተኳሽ በመማረክ አቅሙን ማንኮታኮት ተችሏል።

ምክትል አዛዡ ጨምረው እንዳስረዱት ከመሳሪያና ተተኳሾች ባለፈ የተለያዩ ቁሳቁሶች የተማረኩበት ሲሆን በዚህኛው ዘመቻ በርካታ ሃይል ለማሰለፍ የሞከረው ሸኔ ከፍተኛ ምት ደርሶበታል።

ለሽብር ቡድኑ መደምሰስ የአካባቢው ማህበረሰብ ከክፍለ ጦሩ ጋር በቅንጅት መስራቱ ከፍተኛ ሚና እንደነበረው የክፍለጦሩ አመራሮች በአስተያየታቸው መግለጻቸውን ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
በትግራይ ክልል ለተከሠተው ድርቅ የተቀናጀ ርብርብ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ
***********
(ኢ.ፕ.ድ)
በትግራይ ክልል ለተከሰተው ድርቅ ሁሉም አካላት ችግሩን ለመሻገር በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ፡፡

በሰው፣ በእንስሳትና በእጽዋት ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን በምልከታ ማረጋገጡን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገልጿል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታ በተመለከተ በምልከታ ያረጋገጠውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በትግራይ ክልል ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ከፍተኛ ጉዳት ማስከተሉን መመልከቱን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢና የልዑካን ቡድኑን የመሩት ዲማ ነገዎ (ዶ/ር) አመልክተዋል፡፡

ሰብአዊ ችግሩን ክልሉ ብቻውን የሚወጣው ባለመሆኑ ሁሉም ወገኑን የሚታደግበት ሁኔታ መኖር አለበት ብለዋል፡፡

እናቶች፣ ሕጻናትና አዛውንቶች ከቀዬአቸው ተፈናቅለው በመጠለያ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡

አካባቢው ኮቪድ፣ የአምበጣ ወረርሽኝ፣ ሁለት ዓመትም በጦርነት ያሳለፈ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ሕዝቡ ችግር ውስጥ እንዳለ በመስክ ምልከታ፣ ተጎጂዎችን አመራሮችንና ገለልተኛ አካላትን በማነጋገር የችግሩን ስፋት መገንዘብ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም ሕዝቡ ወደ ቀዬው ተመልሶ እስኪቋቋም ድረስ ተከታታይና ዘላቂነት ያለው ድጋፍ ስለሚፈልግ ሁሉም አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዘላለም ግዛው
የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ‼️
#ግብጽ
#ጋማል_አብዱል_ናስር

ኢትዮጵያ “የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩትን የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ በማገናኘትና ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም እንዲመጡ አድርጋለች።

በዚሁ መሰረት ግንቦት 1955 ዓ.ም 32 መስራች አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።

ለዚህ ድርጅት እውን መሆን ፊርማቸውን ካኖሩ አገራት መካከል የቀድሞ የግብጽ ፕሬዝዳንት ጋማል አብዱል ናስር አንዱ ናቸው።

በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱም አማረኛ ነበር።
ኢትዮጵያና ሊቢያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
****
(ኢ ፕ ድ)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሊቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ ኢሳ ጋር በዛሬው እለት ተወያይተዋል።

ውይይቱ የተካሄደው ከአፍሪካ ህብረት 44ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን ነው ብሏል።

ሁለቱ ወገኖች ከዚህ ቀደም የነበሩ የግንኙነት አሰራሮችን ለመገምገምና የፖለቲካ ምክክር ስርዓት ለመፍጠር ተስማምተዋል።

በተጨማሪም በአቬሽን እና የስራ ስምሪት ዘርፎች ትብብርን ለማጠናከርም ከመግባባት ላይ ደርሰዋል።

የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
ለአፍሪካ ህብረት ጉባኤ መሪዎች አዲስ አበባ መግባት ጀመሩ
*****
(ኢ ፕ ድ)

የኮትዲቯር ምክትል ፕሬዝዳንት ቲሞኮ ሚዬሊ ኮኔ በ37ኛ የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ቦሌ አለማቀፍ አየርማረፊያ ሲደርሱም የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዷለም አቀባበል አድርገውላቸዋል።

37ኛው የአፍሪካ ኅብረት አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ በመጪው ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
ኖርዌይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ጠንካራ ግንኙነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለፀች
******
(ኢ ፕ ድ)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከኖር የልማት ሚኒስትር አኔ ቤዝ ቲቭነሪም ጋር በሁለትዮሽና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።

በውይይታቸውም በአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ በደን ልማት፣ በትምህርት፣ በግብርና ዘርፍና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

አምባሳደር ታዬ ኖርዌይ በሁኔታዎች የማትቀየር የኢትዮጵያ ጠንካራ ወዳጅ አገር መሆኗን ገልፀዋል።

ኖርዌይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቆየ ጠንካራ ግንኙነት አጠናክራ እንደምትቀጥልም ሚኒስትሯ ገልፀዋል።

ሁሉቱ ሚኒስትሮች ሁለቱ አገራት በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያም መክረዋል።

የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ወደ አፍሪካ ኅብረት መዲና እንኳን ደኅና መጣችሁ" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ የስትራቴጂያዊ አጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ
*****
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የስትራቴጂያዊ አጋርነት ስምምነት ተፈራርመዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ እና የደቡብ አፍሪካ አቻቸው ናሌዲ ፓንዶር ስምምነቱን ዛሬ ከ44ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን በተካሄደ ስነ ስርዓት ላይ ፈርመዋል።

ስትራቴጂያዊ አጋርነቱ በፀረ-አፓርታይድ ትግል ወቅት የተፈጠረውን ጠንካራ ወዳጅነት መሰረት ያደረገ ፖለቲካዊ ትብብርን ለማሳደግና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ለማስፋት ያለመ ነው።

ስምምነቱ በተለያዩ መስኮች ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማስፋትና ለማጠናከር ያለመ ነውም ተብሏል።

በባለብዙ ወገን መድረኮች ላይ በጋራ ጥቅም ጉዳዮች ላይ ትብብር ማድረግ ከስምምነቱ ዋና ዓላማዎች አንዱ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
አምባሳደር ታዬአጽቀሥላሴ ከቤኒን አቻቸው ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል
***
(ኢ ፕ ድ)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከቤኒን አቻቸው ኦሉሸጉን ባካሪ ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በውይይቱ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ቤኒን በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያላትን የማይናወጥ ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

ኦሉሼጉን ባካሪ በበኩላቸው ቤኒን በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ልምድ መቅሰም ትፈልጋለች ብለዋል።

የፖለቲካ ግንኙነቶችን ወደ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለማሳደግ ትክክለኛው ጊዜ አሁን እንደሆነም ተስማምተዋል።

የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
ለአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የሀገራት መሪዎች አዲሰ አበባ እየገቡ ነው‼️

በ37ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ሩሴል ዲላሚኒ፤  የሴራሊዮን ምክትል ፕሬዝዳንት መሀመድ ዡሌ ዣሎህ፤ የቻድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሱክሴ ማስራ፤ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ቦላ አህመድ ቲኑቡ፤ የቶጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ቶሜጋህ ዶግቤ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።

የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም