Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ወደ አፍሪካ ኅብረት መዲና እንኳን ደኅና መጣችሁ" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ የስትራቴጂያዊ አጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ
*****
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የስትራቴጂያዊ አጋርነት ስምምነት ተፈራርመዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ እና የደቡብ አፍሪካ አቻቸው ናሌዲ ፓንዶር ስምምነቱን ዛሬ ከ44ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን በተካሄደ ስነ ስርዓት ላይ ፈርመዋል።

ስትራቴጂያዊ አጋርነቱ በፀረ-አፓርታይድ ትግል ወቅት የተፈጠረውን ጠንካራ ወዳጅነት መሰረት ያደረገ ፖለቲካዊ ትብብርን ለማሳደግና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ለማስፋት ያለመ ነው።

ስምምነቱ በተለያዩ መስኮች ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማስፋትና ለማጠናከር ያለመ ነውም ተብሏል።

በባለብዙ ወገን መድረኮች ላይ በጋራ ጥቅም ጉዳዮች ላይ ትብብር ማድረግ ከስምምነቱ ዋና ዓላማዎች አንዱ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
አምባሳደር ታዬአጽቀሥላሴ ከቤኒን አቻቸው ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል
***
(ኢ ፕ ድ)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከቤኒን አቻቸው ኦሉሸጉን ባካሪ ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በውይይቱ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ቤኒን በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያላትን የማይናወጥ ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

ኦሉሼጉን ባካሪ በበኩላቸው ቤኒን በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ልምድ መቅሰም ትፈልጋለች ብለዋል።

የፖለቲካ ግንኙነቶችን ወደ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለማሳደግ ትክክለኛው ጊዜ አሁን እንደሆነም ተስማምተዋል።

የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
ለአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የሀገራት መሪዎች አዲሰ አበባ እየገቡ ነው‼️

በ37ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ሩሴል ዲላሚኒ፤  የሴራሊዮን ምክትል ፕሬዝዳንት መሀመድ ዡሌ ዣሎህ፤ የቻድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሱክሴ ማስራ፤ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ቦላ አህመድ ቲኑቡ፤ የቶጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ቶሜጋህ ዶግቤ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።

የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
የብራዚል ፕሬዝዳንት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
***

(ኢ ፕ ድ)

የብራዚል ፕሬዝዳንት ሊዊዝ ኢናሲዬ ሉላ ዳ ሲልቫ ማምሻውን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንት ሉላ ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።

የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም
«አፍሪካ የቴክኖሎጂ ሽግግር በማምጣት በዓለም የንግድ እንቅስቃሴ ያላትን ድርሻ ልታሳድግ ይገባል»
– አልበርት ሙቻንጋ
የአፍሪካ ኅብረት የኢኮኖሚ ልማት፣ ቱሪዝም፣ ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ማዕድን ኮሚሽነር
************
(ኢ.ፕ.ድ)
ከዓለም የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ የአፍሪካ ድርሻ 2 ነጥብ 8 በመቶ ብቻ በመሆኑ ሀገራት የቴክኖሎጂ ሽግግር በማምጣት ድርሻቸውን ለማሳደግ ሊሠሩ ይገባል ሲሉ የአፍሪካ ኅብረት የኢኮኖሚ ልማት፣ ቱሪዝም፣ ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ማዕድን ኮሚሽነር አልበርት ሙቻንጋ ገለጹ።

ኮሚሽነር አልበርት ሙቻንጋ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት፤ የዓለም ኢኮኖሚ ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ ቢመጣም ከዓለም የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ የአፍሪካ ድርሻ 2 ነጥብ 8 በመቶ ብቻ ነው።

በመሆኑ ሀገራት ይህንን በመገንዘብ የቴክኖሎጂ ሽግግር በማምጣት ድርሻቸውን ለማሳደግ ሊሠሩ ይገባል።

ይህም የሚያሳየው የአፍሪካ ሀገራት ምርትን በበቂ መጠን እያመረቱ ላለመሆኑ ማሳያ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፤ በመሆኑም የግብርና ምርትን ማሳደግ፣ የተቀነባበሩና እሴት የተጨመረባቸው...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=120946
«ዓድዋ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ አፍሪካውያንን አንድ ያደረገ ድል ነው» አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ
– የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
*************
(ኢ.ፕ.ድ)
የዓድዋ ድል በዓለም ዙሪያ የሚገኙ አፍሪካውያንን ቀጣይነት ባለው መልኩ አንድ በማድረግ በኩል ትልቁን ድርሻ መውሰዱን አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።

በ37ኛው አፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔና በ44ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ለመታደም አዲስ አበባ የገቡ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶችና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከጉብኝቱ በኋላ ለእንግዶቹ ባደረጉት የእራት ግብዣ ላይ እንደተናገሩት፤ በዓድዋ ድል የተስተዋለው ታሪክ የአፍሪካን ፅናትና ጥንካሬ የሚያመለክት እንደሆነ አብራርተዋል።

ድሉ ለቅኝ ግዛት ተቃውሞ ትልቅ ሚና የተጫወተና የፓን አፍሪካኒዝምን ዕድገት ያሳየ ነው ብለውም፤ በዚህም በዓለም...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=120955
በክልሉ አንድ ሚሊዮን የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መጽሀፍ ተሰራጭቷል
****************
(ኢ ፕ ድ)
ከአሥር ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ መምህራን ሥልጠና ተሰጥቷል

በ2016 የትምህርት ዘመን አንድ ሚሊዮን የሁለተኛ ደረጃ የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የመማሪያ መጽሀፍ ለትምህርት ቤቶች ማሰራጨት መቻሉን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

በክልሉ ከአሥር ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ የትምህርት ቤት አመራሮችና መምህራን ሥልጠና ተሰጥቷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ በክልሉ አንድ ሚሊዮን የሁለተኛ ደረጃ የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የመማሪያ መጽሐፍት ተሰራጭቷል።

አሁን ባለው ሁኔታ አንድ መጽሐፍ ለአራት ተማሪዎች ይዳረሳል ያሉት አቶ አንተነህ፤ በክልሉ የትምህርት ጥራት ለማሻሻልና የመማሪያ ግብዓት ማሟላት እንዲቻል በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል።

አቶ አንተነህ አክለውም፤ በክልሉ 50 መምህራን በሀገር አቀፍ ደረጃ ከዋና መጽሐፍ አዘጋጆች ሥልጠና በመውሰድ ከአስር ሺህ 500 በላይ ለሁለተኛ ደረጃ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች በሦስት ምዕራፍ የአሠልጣኞች ሥልጠና ሰጥተዋል ብለዋል።

በተጨማሪም የመምህራን የአቅም ውስንነት ለመሙላት በየደረጃው ይዘትን መሠረት ያደረገ ሥልጠና መሰጠቱን አቶ አንተነህ …….

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=120975
የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ አዲስ አበባ ገቡ
*********
(ኢ.ፕ.ድ)
የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የቱሪዝም ሚኒስትር ክብርት አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።

የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት መሪዎች የካቲት 9 እና 10 2016ዓ.ም. የሚካሄደው 37ኛው መደበኛ መሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው።

የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️

ዛሬ ማለዳ የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ከቀዳማዊት እመቤት ጃንጃ ሉላ ዳ ሲልቫ ጋር በመሆን በዓድዋ ድል ሃውልት ስር የአበባ ጉንጉን በማኖር የዓድዋ ድል መታሰቢያን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም