Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሻሻል ነጻ የቪድዮ ትምህርቶች እየተሰጡ ነው
***
(ኢ.ፕ.ድ)

በተማሪዎች ላይ የሚታየውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሻሻል ነጻ የቪድዮ ትምህርቶች እየተሰጠ መሆኑን ትምህርት ሚንስቴር አስታወቀ።

ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የስድስት ወር አፈጻጸም ሪፖርት ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ እንደ ሀገር ለተፈጠረው የትምህርት ጥራት ስብራት አንዱ ምክንያት ተማሪዎች ትምህርቱ የሚሰጥበት ቋንቋ በቂ እውቀት አለመኖር ነው። በመሆኑም የቋንቋ ችግር በተለይ ከሁለተኛ ደረጃ ጀምሮ ተማሪዎች ያላቸው እውቀት የተገደበ እንዲሆን አደርጓል።

ይህንንም ለመቅረፍ ከአዲሱ ስርዓተ-ትምህርት ጋር የሚስማሙ፤ የተለያዩ ይዘት ያላቸው 305 አጫጭር ትምህርታዊ ቪድዮዎች በፖርታል ዌብ ላይ ተጭነው በነጻ (ያለ ዳታ) ተደራሽ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ ቪዲዮዎቹ እንግሊዝኛ ቋንቋ አፍ መፍቻቸው በሆኑ ባለሙያዎች የተዘጋጁ ሲሆን ስለ ፖርታል ዌቡ አጠቃቀምም ለ4 ሺ 630 የእንግሊዝኛ መምህራን ግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ተከናውኗል።

በዘላቂነት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችግርን ለመቅረፍ እንደ እቅድ ተቀምጦ የነበረው በርካታ የውጪ መምህራንን በድጋፍና በተለያዩ መንገዶቸ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት እንዲያስተምሩ ማድረግ ነበር። ለዚህም ከአምስት የእንግሊዝኛ ቋንቋ አፍ መፍቻቸው ከሆኑ ሀገራት ጋር ውይይቶች እየተደረጉ ቢሆንም በዚህ ወቅት መድረስ አልቻሉም ብለዋል።

በተጨማሪ ሁለተኛ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን አምጥቶ እንዲያስተምሩ ለማድረግ የተጀመሩ እንቅስቀሴዎች ቢኖሩም ግዜ የሚፈልጉ ሆነዋል። በመሆኑም እንደ አማራጭ የተዘጋጁ ቪዲዮችን ተደራሽ ማድረጉ ተመራጭ ሆኗል ነው ያሉት።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአፍ መፍቻ ቋንቋ ከመማር ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍም የትምህርት ሚንስቴር በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ ለ2 ሺ 287 መምህራን የአሰልጣኞች ስልጠና በወሰዱ መምህራን ስልጠና መስጠት ተችሏል፡፡

በቀጣይም ትምህርት ሚንስቴር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ በመማር ማስተማር ሂደት ላይ የሚፈጠሩ ተግዳሮቶችን ለማስወገድ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ሚንስትሩ ጠቁመዋል።

በራስወርቅ ሙሉጌታ
ዘጠነኛውን ሀገር አቀፍ የከተሞች ፎረም ነገ ይጀመራል
******
(ኢ.ፕ.ድ)

ዘጠነኛውን ሀገር አቀፍ የከተሞች ፎረም “የዘመኑ ከተሞች ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በነገው እለት በወላይታ ሶዶ ከተማ ይካሄዳል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ኮሙንኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ ብላቴና ብርሃኑ ፎረሙን አስመልክተው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት ፤ በፎረሙ ከተሞች እርስ በርስ ልምድ የሚለዋወጡበትና የሚተዋወቁበት ነው ፡፡

የወላይታ ሶዶ ከተማ እንግዶችን ለመቀበል በቂ ዝግጅት መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡

በፎረሙ ከ200 በላይ ከተሞች የሚሳተፉ ሲሆን ከ20 ሺህ በላይ ጎብኚዎችም ወደ ከተማዋ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃልም ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

ፎረሙ ከነገው ጀምሮ ለተከታታይ ስምንት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል፡፡

በዳግማዊት አበበ
የካቲት 8/2016 ዓ.ም
መልካም ዕድል
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️

ዛሬ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የብራዚል ኘሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናቺዮ ሉላ ደ ሲልቫን ተቀብያለው። በውይይታችንም የግንኙነታችንን ጥልቀት የሚያንፀባርቁ የተለያዩ የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል። ኢትዮጵያ የተከበረው የብሪክስ ቡድን አባል ሆና በመቀላቀሏ ከብራዚል ጋር ያለን ግንኙነት የበለጠ እንደሚጠናከር እንጠብቃለን። የዛሬው ግንኙነታችንም የፀና ወዳጅነት የመገንባት አንድ ርምጃ ነው።
የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ

#ቻድ
#ፍራቨኮይሰ ቶምባልባዬ

ኢትዮጵያ “የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩትን የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ በማገናኘትና ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም እንዲመጡ አድርጋለች።

በዚሁ መሰረት ግንቦት 1955 ዓ.ም 32 መስራች አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።

ለዚህ ድርጅት እውን መሆን ፊርማቸውን ካኖሩ አገራት መካከል የቀድሞ የቻድ ፕሬዚዳንት ፍራቨኮይሰ ቶምባልባዬ አንዱ ናቸው።

በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱም አማረኛ ነበር።
የሞሪሸየስ ጠቅላይ ሚኒስትር ፕራቪንድ ኩማር ጁግናውት አዲስ አበባ ገቡ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

የሞሪሸስ ጠቅላይ ሚኒስትር ፕራቪንድ ኩማር ጁግናውት በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ አዲስ አበባ ገቡ
**
(ኢ.ፕ.ድ)

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
ለአቶ ደመቀ መኮንን የጀግና ሽልማት ተበረከተላቸው
******
(ኢ.ፕ.ድ)

የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን የሰቆጣ ቃልኪዳን የጀግና ሽልማት ተበረከተላቸው።

አቶ ደመቀ መኮንን ይህን የጀግና ሽልማት ያገኙት ከ37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ጎን ለጎን በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል እየተካሄደ ባለው የስርአተ ምግብ ከፍተኛ መድረክ ላይ ነው።

ለሽልማቱ ያበቃቸውም ለሰቆጣ ቃልኪዳን እውን መሆንና ገቢራዊነት ላደረጉት ጥረትና ቁርጥ የአመራር ብቃት ነው ተብሏል ።

በተለይ ደግሞ የሰቆጣ ቃልኪዳን ከተፈረመበት ግዜ ጀምሮ ላለፉት አስራ አምስት አመታት ፕሮግራሙ እንዲሳካ ያደረጉት የፖለቲካ አመራር ለሽልማቱ አብቅቷቸዋል ተብሏል ።

አቶ ደመቀ የእውቅና ሽልማቱን ከተረከቡ በኃላ ባደረጉት ንግግር አሁንም ድረስ የመቀንጨርና ሌሎችም ከስርአተ ምግብ ጋር የተያያዙ ችግሮች በመኖራቸው የሰቆጣ ቃልኪዳንን በተጨማሪ ወረዳዎች ማስፋት ያስፈልጋል ብለዋል።

ለዚህም የልማት አጋሮችና የግሉ ሴክተር ትብብር ወሳኝ ነው ብለዋል።

ከአቶ ደመቀ መኮንን በተጨማሪ ለወይዘሮ ፍሬአለም ሽባባው፣ ዶ/ር ተከስተ አድማሱ እና ለዶክተር ሊያ ታደስ በየደረጃው ለሰቆጣ ቃልኪዳን እውን መሆን ላደረጉት ጥረት ተመሳሳይ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

በአስናቀ ፀጋዬ
የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም
የሞሪታኒያ ኘሬዝደንት ሞሃመድ ኦውልድ ኤል ጋዞኒ አዲስ አበባ ገቡ
******
(ኢ.ፕ.ድ)

የሞሪታኒያ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ኦውልድ ኤል ጋዞኒ በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶች እና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።