Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ዘጠነኛውን ሀገር አቀፍ የከተሞች ፎረም ነገ ይጀመራል
******
(ኢ.ፕ.ድ)

ዘጠነኛውን ሀገር አቀፍ የከተሞች ፎረም “የዘመኑ ከተሞች ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በነገው እለት በወላይታ ሶዶ ከተማ ይካሄዳል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ኮሙንኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ ብላቴና ብርሃኑ ፎረሙን አስመልክተው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት ፤ በፎረሙ ከተሞች እርስ በርስ ልምድ የሚለዋወጡበትና የሚተዋወቁበት ነው ፡፡

የወላይታ ሶዶ ከተማ እንግዶችን ለመቀበል በቂ ዝግጅት መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡

በፎረሙ ከ200 በላይ ከተሞች የሚሳተፉ ሲሆን ከ20 ሺህ በላይ ጎብኚዎችም ወደ ከተማዋ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃልም ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

ፎረሙ ከነገው ጀምሮ ለተከታታይ ስምንት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል፡፡

በዳግማዊት አበበ
የካቲት 8/2016 ዓ.ም
መልካም ዕድል
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️

ዛሬ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የብራዚል ኘሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናቺዮ ሉላ ደ ሲልቫን ተቀብያለው። በውይይታችንም የግንኙነታችንን ጥልቀት የሚያንፀባርቁ የተለያዩ የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል። ኢትዮጵያ የተከበረው የብሪክስ ቡድን አባል ሆና በመቀላቀሏ ከብራዚል ጋር ያለን ግንኙነት የበለጠ እንደሚጠናከር እንጠብቃለን። የዛሬው ግንኙነታችንም የፀና ወዳጅነት የመገንባት አንድ ርምጃ ነው።
የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ

#ቻድ
#ፍራቨኮይሰ ቶምባልባዬ

ኢትዮጵያ “የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩትን የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ በማገናኘትና ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም እንዲመጡ አድርጋለች።

በዚሁ መሰረት ግንቦት 1955 ዓ.ም 32 መስራች አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።

ለዚህ ድርጅት እውን መሆን ፊርማቸውን ካኖሩ አገራት መካከል የቀድሞ የቻድ ፕሬዚዳንት ፍራቨኮይሰ ቶምባልባዬ አንዱ ናቸው።

በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱም አማረኛ ነበር።
የሞሪሸየስ ጠቅላይ ሚኒስትር ፕራቪንድ ኩማር ጁግናውት አዲስ አበባ ገቡ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

የሞሪሸስ ጠቅላይ ሚኒስትር ፕራቪንድ ኩማር ጁግናውት በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ አዲስ አበባ ገቡ
**
(ኢ.ፕ.ድ)

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
ለአቶ ደመቀ መኮንን የጀግና ሽልማት ተበረከተላቸው
******
(ኢ.ፕ.ድ)

የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን የሰቆጣ ቃልኪዳን የጀግና ሽልማት ተበረከተላቸው።

አቶ ደመቀ መኮንን ይህን የጀግና ሽልማት ያገኙት ከ37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ጎን ለጎን በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል እየተካሄደ ባለው የስርአተ ምግብ ከፍተኛ መድረክ ላይ ነው።

ለሽልማቱ ያበቃቸውም ለሰቆጣ ቃልኪዳን እውን መሆንና ገቢራዊነት ላደረጉት ጥረትና ቁርጥ የአመራር ብቃት ነው ተብሏል ።

በተለይ ደግሞ የሰቆጣ ቃልኪዳን ከተፈረመበት ግዜ ጀምሮ ላለፉት አስራ አምስት አመታት ፕሮግራሙ እንዲሳካ ያደረጉት የፖለቲካ አመራር ለሽልማቱ አብቅቷቸዋል ተብሏል ።

አቶ ደመቀ የእውቅና ሽልማቱን ከተረከቡ በኃላ ባደረጉት ንግግር አሁንም ድረስ የመቀንጨርና ሌሎችም ከስርአተ ምግብ ጋር የተያያዙ ችግሮች በመኖራቸው የሰቆጣ ቃልኪዳንን በተጨማሪ ወረዳዎች ማስፋት ያስፈልጋል ብለዋል።

ለዚህም የልማት አጋሮችና የግሉ ሴክተር ትብብር ወሳኝ ነው ብለዋል።

ከአቶ ደመቀ መኮንን በተጨማሪ ለወይዘሮ ፍሬአለም ሽባባው፣ ዶ/ር ተከስተ አድማሱ እና ለዶክተር ሊያ ታደስ በየደረጃው ለሰቆጣ ቃልኪዳን እውን መሆን ላደረጉት ጥረት ተመሳሳይ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

በአስናቀ ፀጋዬ
የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም
የሞሪታኒያ ኘሬዝደንት ሞሃመድ ኦውልድ ኤል ጋዞኒ አዲስ አበባ ገቡ
******
(ኢ.ፕ.ድ)

የሞሪታኒያ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ኦውልድ ኤል ጋዞኒ በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶች እና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳሙኤል ፆኮአኔ ማትኬን አዲስ አበባ ገቡ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳሙኤል ፆኮአኔ ማትኬን በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግብርና ሚኒስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ጀሲካ አሉፖ አዲስ አበባ ገቡ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ጀሲካ አሉፖ በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶች እና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።