Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️

ዛሬ ማለዳ የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ከቀዳማዊት እመቤት ጃንጃ ሉላ ዳ ሲልቫ ጋር በመሆን በዓድዋ ድል ሃውልት ስር የአበባ ጉንጉን በማኖር የዓድዋ ድል መታሰቢያን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም
«ኩባ ባለፉት ሦስት ዓመታት የቆየውን የኢትዮጵያን ወዳጅነትና አጋርነት በተግባር አጠናክራ አሳይታለች»
- አምባሳደር ገነት ተሾመ (ዶ/ር) በኩባ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር
*****
(ኢ.ፕ.ድ)
ኩባና ኢትዮጵያ ለብዙ ዓመታት የዘለቀውን ወዳጅነትና አጋርነት አጠናክረው መቀጠላቸውን በኩባ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ገነት ተሾመ (ዶ/ር) አስታወቁ።

በኩባ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ገነት ተሾመ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ኩባ የኢትዮጵያ ጥንታዊና ታሪካዊ ወዳጅ ናት። በኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት ወቅት 17 ሺህ ወታደሮችን አሰልፋ ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት መስዋዕትነት እስከመክፈል የደረሰ ድጋፍ አድርጋለች ያሉት አምባሳደሩ፤ ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ አጠቃላይ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ውስጥ የራሷን አስተዋፅዖ ስታደርግ የቆየች ሀገር መሆኗን ገልጸዋል።

ኩባ በአንድ ሀገር ውስጥ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት አያስፈልግም የሚል ጽኑ አቋም አላት ያሉት አምባሳደሩ፤ በኩባ አቋም ኢትዮጵያ የውጭ ጫና ሳያስፈልጋት የራሷን ችግር በራሷ መፍታት የምትችል ሀገር ናት የሚል አቋም በማራመድ የቆየውን ግንኙነት አጠናክራለች ብለዋል። በተለይ ኩባ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን ወዳጅነትና አጋርነት አጠናክራ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://press.et/?p=120970
44ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ተጠናቀቀ
*
*
(ኢ.ፕ.ድ)

44ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ዛሬ ማለዳ ተጠናቋል።

ስብሰባው "ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ስርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣የሕይወት ዘመን፣ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት“ በሚል የአፍሪካ ሕብረት ባዘጋጀው የ2024 መሪ ቃል ሲካሄድ ቆይቷል።

በስብሰባው የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ዲፕሎማቶችና የሕብረቱ ተቋማት አመራሮች ተሳትፈዋል ።

ምክር ቤቱ ከጥር 6 እስከ 17 ቀን 2016 ዓ.ም 47ኛው የአፍሪካ ሕብረት ቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ በተወያየባቸው አጀንዳዎች ላይ ምክክር አድርጓል።

ሌሊቱን በዘለቀው የምክር ቤቱ ስብሰባ የአፍሪካ ሕብረት ተቋማትና አደረጃጀቶች፣በምክር ቤቱ ስር የሚገኙ ኮሚቴዎችና ንዑሳን ኮሚቴዎች እንዲሁም የአጀንዳ 2063 የ10 ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጧል።

ሰላምና ደህንነት፣ ንግድና ትስስር፣ተቋማዊ ማሻሻያዎች፣ትምህርት፣ግብርናና የአየር ንብረት ለውጥ፣ሰብዓዊ መብቶች፣ ስርዓተ ጾታና ወጣቶችን ማብቃት እንዲሁም የተቋማትና አደረጃጀቶች ምርጫ ውይይት ከተደረገባቸው ዋንኛ አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ።

እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ የካቲት 9 እና 10 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚከናወነው 37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎችንም አፅድቋል።

የአፍሪካ ሕብረት ተቋማትና አደረጃጀቶች መግለጫዎችን ጨምሮ የተለያዩ ሁነቶች ዛሬ እንደሚካሄዱ ከሕብረቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 9 እና 10 ቀን 2016 ዓ.ም በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ይካሄዳል።

የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሻሻል ነጻ የቪድዮ ትምህርቶች እየተሰጡ ነው
***
(ኢ.ፕ.ድ)

በተማሪዎች ላይ የሚታየውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሻሻል ነጻ የቪድዮ ትምህርቶች እየተሰጠ መሆኑን ትምህርት ሚንስቴር አስታወቀ።

ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የስድስት ወር አፈጻጸም ሪፖርት ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ እንደ ሀገር ለተፈጠረው የትምህርት ጥራት ስብራት አንዱ ምክንያት ተማሪዎች ትምህርቱ የሚሰጥበት ቋንቋ በቂ እውቀት አለመኖር ነው። በመሆኑም የቋንቋ ችግር በተለይ ከሁለተኛ ደረጃ ጀምሮ ተማሪዎች ያላቸው እውቀት የተገደበ እንዲሆን አደርጓል።

ይህንንም ለመቅረፍ ከአዲሱ ስርዓተ-ትምህርት ጋር የሚስማሙ፤ የተለያዩ ይዘት ያላቸው 305 አጫጭር ትምህርታዊ ቪድዮዎች በፖርታል ዌብ ላይ ተጭነው በነጻ (ያለ ዳታ) ተደራሽ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ ቪዲዮዎቹ እንግሊዝኛ ቋንቋ አፍ መፍቻቸው በሆኑ ባለሙያዎች የተዘጋጁ ሲሆን ስለ ፖርታል ዌቡ አጠቃቀምም ለ4 ሺ 630 የእንግሊዝኛ መምህራን ግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ተከናውኗል።

በዘላቂነት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችግርን ለመቅረፍ እንደ እቅድ ተቀምጦ የነበረው በርካታ የውጪ መምህራንን በድጋፍና በተለያዩ መንገዶቸ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት እንዲያስተምሩ ማድረግ ነበር። ለዚህም ከአምስት የእንግሊዝኛ ቋንቋ አፍ መፍቻቸው ከሆኑ ሀገራት ጋር ውይይቶች እየተደረጉ ቢሆንም በዚህ ወቅት መድረስ አልቻሉም ብለዋል።

በተጨማሪ ሁለተኛ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን አምጥቶ እንዲያስተምሩ ለማድረግ የተጀመሩ እንቅስቀሴዎች ቢኖሩም ግዜ የሚፈልጉ ሆነዋል። በመሆኑም እንደ አማራጭ የተዘጋጁ ቪዲዮችን ተደራሽ ማድረጉ ተመራጭ ሆኗል ነው ያሉት።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአፍ መፍቻ ቋንቋ ከመማር ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍም የትምህርት ሚንስቴር በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ ለ2 ሺ 287 መምህራን የአሰልጣኞች ስልጠና በወሰዱ መምህራን ስልጠና መስጠት ተችሏል፡፡

በቀጣይም ትምህርት ሚንስቴር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ በመማር ማስተማር ሂደት ላይ የሚፈጠሩ ተግዳሮቶችን ለማስወገድ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ሚንስትሩ ጠቁመዋል።

በራስወርቅ ሙሉጌታ
ዘጠነኛውን ሀገር አቀፍ የከተሞች ፎረም ነገ ይጀመራል
******
(ኢ.ፕ.ድ)

ዘጠነኛውን ሀገር አቀፍ የከተሞች ፎረም “የዘመኑ ከተሞች ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በነገው እለት በወላይታ ሶዶ ከተማ ይካሄዳል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ኮሙንኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ ብላቴና ብርሃኑ ፎረሙን አስመልክተው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት ፤ በፎረሙ ከተሞች እርስ በርስ ልምድ የሚለዋወጡበትና የሚተዋወቁበት ነው ፡፡

የወላይታ ሶዶ ከተማ እንግዶችን ለመቀበል በቂ ዝግጅት መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡

በፎረሙ ከ200 በላይ ከተሞች የሚሳተፉ ሲሆን ከ20 ሺህ በላይ ጎብኚዎችም ወደ ከተማዋ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃልም ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

ፎረሙ ከነገው ጀምሮ ለተከታታይ ስምንት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል፡፡

በዳግማዊት አበበ
የካቲት 8/2016 ዓ.ም
መልካም ዕድል
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት‼️

ዛሬ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የብራዚል ኘሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናቺዮ ሉላ ደ ሲልቫን ተቀብያለው። በውይይታችንም የግንኙነታችንን ጥልቀት የሚያንፀባርቁ የተለያዩ የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል። ኢትዮጵያ የተከበረው የብሪክስ ቡድን አባል ሆና በመቀላቀሏ ከብራዚል ጋር ያለን ግንኙነት የበለጠ እንደሚጠናከር እንጠብቃለን። የዛሬው ግንኙነታችንም የፀና ወዳጅነት የመገንባት አንድ ርምጃ ነው።
የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ

#ቻድ
#ፍራቨኮይሰ ቶምባልባዬ

ኢትዮጵያ “የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩትን የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ በማገናኘትና ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም እንዲመጡ አድርጋለች።

በዚሁ መሰረት ግንቦት 1955 ዓ.ም 32 መስራች አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።

ለዚህ ድርጅት እውን መሆን ፊርማቸውን ካኖሩ አገራት መካከል የቀድሞ የቻድ ፕሬዚዳንት ፍራቨኮይሰ ቶምባልባዬ አንዱ ናቸው።

በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱም አማረኛ ነበር።
የሞሪሸየስ ጠቅላይ ሚኒስትር ፕራቪንድ ኩማር ጁግናውት አዲስ አበባ ገቡ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

የሞሪሸስ ጠቅላይ ሚኒስትር ፕራቪንድ ኩማር ጁግናውት በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ አዲስ አበባ ገቡ
**
(ኢ.ፕ.ድ)

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።