Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳሙኤል ፆኮአኔ ማትኬን አዲስ አበባ ገቡ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳሙኤል ፆኮአኔ ማትኬን በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግብርና ሚኒስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ጀሲካ አሉፖ አዲስ አበባ ገቡ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ጀሲካ አሉፖ በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶች እና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
የዙምባቡዌ ፕሬዝዳንት ኢመርሰን ማናንጋዋ አዲስ አበባ ገቡ
**********
(ኢ.ፕ.ድ)
የዙምባቡዌ ፕሬዝዳንት ኢመርሰን ማናንጋዋ በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል
የይርጋ ጨፌ የቡና ምርምር ተቋም ለማቋቋም የድጋፍ ማሰባሰቢያ ሲምፖዚየም ይካሄዳል
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የይርጋ ጨፌ የቡና ምርምር ተቋም ለማቋቋም ያለመ ሲምፖዚየም የካቲት 28 በሀዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡና ማህበር ፕሬዚዳንት ሁሴን አንቦ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለፁት፤ ኢትዮጵያ በቡና ምርት የምትታወቅ ቢሆንም በዘርፉ የሚጠበቀዉን ያህል ውጤት አልተገኘም።

በመሆኑም በዘርፉ ከምርት እስከ ገበያ ድረስ የሚገጥሙትን ችግሮች ለመፍታት ያለመ የልህቀት ማእከል ማቋቋም እንዳስፈለገ አስረድተዋል።

ሲምፓዚየሙ ለማእከሉ ማስገንቢያ የሚሆን ድጋፍ ለማሰባሰብ ያለመ ሲሆን የቡና አልሚዎችን ጨምሮ የተለያዩ በዘርፍ የተሰማሩ አካላት ይሳተፋሉ ተብሏል።

አመለወርቅ ከበደ
የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም
የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ‼️
#ኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
#ጆሴፍ ካሳ-
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲርል ራማፎሳ አዲስ አበባ ገቡ
***
(ኢ.ፕ.ድ)

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲርል ራማፎሳ በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ክብርት ኢ/ር አይሻ መሀመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ‼️

#ጋና
#ክዋሜ_ንክሩማ

ኢትዮጵያ “የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩትን የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ በማገናኘትና ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም እንዲመጡ አድርጋለች።

በዚሁ መሰረት ግንቦት 1955 ዓ.ም 32 መስራች አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።

ለዚህ ድርጅት እውን መሆን ፊርማቸውን ካኖሩ አገራት መካከል የቀድሞ የቀድሞ የጋና ፕሬዚዳንት ክዋሜ ንክሩማ አንዱ ናቸው።

በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱም አማረኛ ነበር።
የቱኒዚያ ጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ ሃቻኒ አዲስ አበባ ገቡ
***
(ኢ.ፕ.ድ)

የቱኒዚያ ጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ ሃቻኒ በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትሯ ኢ/ር አይሻ መሀመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️

የብራዚል ቀዳማዊት እመቤት ጃንጃ ሉላ ዳ ሲልቫ ከክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር በመሆን የተስፋ ብርሃን እና የመቅደላ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የምገባ ማዕከላትን እንዲሁም በክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ የተገነባዉን የዘውዲቱ መሸሻ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን ጎብኝተዋል።

በቀጣይም የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ይበልጥ አጠናክረን በትብብር አብረን ለመስራት የሚያስችለንን ውይይትም አድርገናል::
የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም
የጂቡቲ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌህ አዲስ አበባ ገቡ
***
(ኢ.ፕ.ድ)

የጂቡቲ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌህ በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ፕሬዝዳንቱ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተቀብለዋቸዋል ።
የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ‼️

#ጊኒ
#ሴኮ_ቱሬ

ኢትዮጵያ “የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩትን የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ በማገናኘትና ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም እንዲመጡ አድርጋለች።

በዚሁ መሰረት ግንቦት 1955 ዓ.ም 32 መስራች አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።

ለዚህ ድርጅት እውን መሆን ፊርማቸውን ካኖሩ አገራት መካከል የቀድሞ የጊኒ ፕሬዚዳንት ሴኮ ቱሬ አንዱ ናቸው።

በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱ አማረኛ ነበር።
የብሩንዲ ፕሬዝዳንት ኤቫሪስቴ ዳይሺሚዬ አዲስ አበባ ገቡ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

የብሩንዲ ፕሬዝዳንት ኤቫሪስቴ ዳይሺሚዬ በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግብርና ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ
******
(ኢ.ፕ.ድ)

የኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶች እና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
የሊቢያ ፕሬዝዳንታዊ ም/ቤት ፕሬዝዳንት መሀመድ የኑስ አል መንፊ አዲስ አበባ ገቡ
****
(ኢ.ፕ.ድ)

የሊቢያ ፕሬዝዳንታዊ ም/ቤት ፕሬዝዳንት መሀመድ የኑስ አል መንፊ በ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግብርና ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ
***
(ኢ.ፕ.ድ)

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ እና ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር ጋር በዛሬው እለት ተወያይተዋል።

አምባሳደር ታዬ ለልዑካን ቡድኑ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ሂደት ላይ ገለፃ የሰጡ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት በስምምነቱ አፈፃፀም ላይ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

አክለውም የሽግግር ፍትህ እና ብሔራዊ ምክክር ሂደት ዝግጅቶች ያሉበትን ደረጃም አብራርተዋል።

በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከስዋቲኒ አቻቸው ፎሊል ሻካንቱ ጋር ተወያዩ
******
(ኢ ፕ ድ)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከስዋቲኒ አቻቸው ፎሊል ሻካንቱ ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያዩ።

በሁለትዮሽ፣ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ማዕቀፍ በተመለከተ የልምድ ልውውጥ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ መክረዋል። ሁለቱ አገሮች በመካከላቸው የንግድ ግንኑኝነት ለመመስረት ከመግባባት ደርሰዋል።

የልዑካን ቡድኑ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉብኝት አድርጓል።

የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም
የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፌሊክስ ትሺሴኬዲ አዲስ አበባ ገቡ
*****
(ኢ ፕ ድ)

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፌሊክስ ትሺሴኬዲ በ37ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል ።

ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢ/ር አይሻ መሀመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም