የይርጋ ጨፌ የቡና ምርምር ተቋም ለማቋቋም የድጋፍ ማሰባሰቢያ ሲምፖዚየም ይካሄዳል
**************
(ኢ.ፕ.ድ)
የይርጋ ጨፌ የቡና ምርምር ተቋም ለማቋቋም ያለመ ሲምፖዚየም የካቲት 28 በሀዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡና ማህበር ፕሬዚዳንት ሁሴን አንቦ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለፁት፤ ኢትዮጵያ በቡና ምርት የምትታወቅ ቢሆንም በዘርፉ የሚጠበቀዉን ያህል ውጤት አልተገኘም።
በመሆኑም በዘርፉ ከምርት እስከ ገበያ ድረስ የሚገጥሙትን ችግሮች ለመፍታት ያለመ የልህቀት ማእከል ማቋቋም እንዳስፈለገ አስረድተዋል።
ሲምፓዚየሙ ለማእከሉ ማስገንቢያ የሚሆን ድጋፍ ለማሰባሰብ ያለመ ሲሆን የቡና አልሚዎችን ጨምሮ የተለያዩ በዘርፍ የተሰማሩ አካላት ይሳተፋሉ ተብሏል።
አመለወርቅ ከበደ
የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም

የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ‼️
#ጋና
#ክዋሜ_ንክሩማ
ኢትዮጵያ “የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩትን የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ በማገናኘትና ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም እንዲመጡ አድርጋለች።
በዚሁ መሰረት ግንቦት 1955 ዓ.ም 32 መስራች አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።
ለዚህ ድርጅት እውን መሆን ፊርማቸውን ካኖሩ አገራት መካከል የቀድሞ የቀድሞ የጋና ፕሬዚዳንት ክዋሜ ንክሩማ አንዱ ናቸው።
በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱም አማረኛ ነበር።

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
የብራዚል ቀዳማዊት እመቤት ጃንጃ ሉላ ዳ ሲልቫ ከክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር በመሆን የተስፋ ብርሃን እና የመቅደላ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የምገባ ማዕከላትን እንዲሁም በክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ የተገነባዉን የዘውዲቱ መሸሻ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን ጎብኝተዋል።
በቀጣይም የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ይበልጥ አጠናክረን በትብብር አብረን ለመስራት የሚያስችለንን ውይይትም አድርገናል::
የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም
የብራዚል ቀዳማዊት እመቤት ጃንጃ ሉላ ዳ ሲልቫ ከክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር በመሆን የተስፋ ብርሃን እና የመቅደላ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የምገባ ማዕከላትን እንዲሁም በክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ የተገነባዉን የዘውዲቱ መሸሻ የህጻናት ማሳደጊያ ማዕከልን ጎብኝተዋል።
በቀጣይም የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ይበልጥ አጠናክረን በትብብር አብረን ለመስራት የሚያስችለንን ውይይትም አድርገናል::
የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ም
የአፍሪካ አባቶችን ይተዋወቁ‼️
#ጊኒ
#ሴኮ_ቱሬ
ኢትዮጵያ “የሞኖሮቪያ” እና “የካዛብላንካ” ቡድን በሚል ተከፍለው የነበሩትን የአፍሪካ አገሮች አዲስ አበባ ላይ በማገናኘትና ልዩነቶችን በማለዘብ ወደ አንድ የጋራ አቋም እንዲመጡ አድርጋለች።
በዚሁ መሰረት ግንቦት 1955 ዓ.ም 32 መስራች አገሮች የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በይፋ አቋቁመዋል።
ለዚህ ድርጅት እውን መሆን ፊርማቸውን ካኖሩ አገራት መካከል የቀድሞ የጊኒ ፕሬዚዳንት ሴኮ ቱሬ አንዱ ናቸው።
በወቅቱ ድርጅቱ ሲመሰረት የመመስረቻ ሰነዱ በአራት ቋንቋዎች ተጽፎ በ32 አገራት መሪዎች የተፈረመ ሲሆን፤ ከአራቱ ቋንቋ አንዱ አማረኛ ነበር።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ
***
(ኢ.ፕ.ድ)
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ እና ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር ጋር በዛሬው እለት ተወያይተዋል።
አምባሳደር ታዬ ለልዑካን ቡድኑ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ሂደት ላይ ገለፃ የሰጡ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት በስምምነቱ አፈፃፀም ላይ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
አክለውም የሽግግር ፍትህ እና ብሔራዊ ምክክር ሂደት ዝግጅቶች ያሉበትን ደረጃም አብራርተዋል።
በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከስዋቲኒ አቻቸው ፎሊል ሻካንቱ ጋር ተወያዩ
******
(ኢ ፕ ድ)
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከስዋቲኒ አቻቸው ፎሊል ሻካንቱ ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያዩ።
በሁለትዮሽ፣ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ማዕቀፍ በተመለከተ የልምድ ልውውጥ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ መክረዋል። ሁለቱ አገሮች በመካከላቸው የንግድ ግንኑኝነት ለመመስረት ከመግባባት ደርሰዋል።
የልዑካን ቡድኑ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉብኝት አድርጓል።

ኢትዮጵያና ካናዳ ያላቸውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በትኩረት ይሰራሉ
*****
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያና ካናዳ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በትኩረት እንደሚሰሩ የሁለቱ ሀገራት የፓርላማ አባላት ገለጹ፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የካናዳ የፓርላማ አባላት በሁለቱ ሀገራት ሁለንተናዊ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡
የቋሚው ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ፈትሂ ማህዲ እንዳሉት፣ የውይይቱ ዓላማ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ነው፡፡
የኢትዮጵያና የካናዳ ዲፕሎማሲያዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ከተመሰረተ ግማሽ ክፍለ ዘመናት ማስቆጠሩን ተናግረዋል።
የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ መሆኑንም አክለዋል፡፡
ይህ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢንቨስትመንትና በአየር ንብረት ለውጥ ዘርፎች እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡
ድህነት ቅነሳ፣ ምግብ ዋስትና፣ ግብርና እና ዘላቂ ልማት ደግሞ ሌላኛው የሁለቱ ሀገራት የትብብር መስክ መሆኑን አመልክተዋል።
በቀጣይም ግንኙነታቸውን በማህበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል፡፡
የካናዳ የፓርላማ አባል አሚና ገርባ በበኩላቸው፤ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር የሚያስችል ፍሪያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ በቀጣይም ካናዳ ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች ትብብሯን አጠናክራ የምትቀጥል መሆኑን አመልክተዋል፡፡