በአማራ ክልል በሰባት ወራት ለዓባይ ግድብ ከ 32 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በአማራ ክልል ለዓባይ ግድብ ግንባታ በሰባት ወር ውስጥ ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የክልሉ የህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ገለጸ።
የጽህፈት ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ተናኘ አበበ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና ንግድ ባንክ በተገኘው መረጃ ከክልሉ ነዋሪዎች በሰባት ወር ውስጥ ከ32 ሚሊዮን 329ሺ ብር በላይ በቦንድ ግዢ ተሰብስቧል።
ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ በተያዘው በጀት ዓመት ከቀድሞ ዓመታት በተለየ መልኩ ዕቅዱን ከፍ በማድረግ 70 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ አቅዶ እንደነበር አስታውሰው፤ ሆኖም በክልሉ በነበረው ችግር የታሰበውን ያህል መስራት እንዳልተቻለ ተናግረዋል።
ግድቡ የተጀመረበትን 13ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግም 40 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ልዩ እቅድ ታቅዶ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ያሉት አቶ ተናኜ፣ ከክልሉ ወጣቶች እና ሴቶች አደረጃጀቶች ጋር በጋራ በመሆን እቅዱን....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124937

በክልሉ ዘንድሮ 889 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
በክልሉ በበጀት ዓመቱ 889 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ገለጹ። ክልሉ በሌማት ትሩፋትም አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን አስታውቋል።
የቢሮ ኃላፊው አቶ ማስረሻ በላቸው በተለይ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በክልሉ ባሉ ሶስት ሺ 886 የችግኝ ጣቢያዎች አማካኝነት ሀገር በቀልና የውጭ ዝርያ ያላቸው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች ያካተተ የዘር ዝግጅት ተደርጓል።
ኃላፊው እንዳሉት ችግኞቹ የሚተከሉት በሚያዝያና ሐምሌ ወር ላይ ጀምሮ ነው።
አሁን ባለው ሁኔታ ዝግጅቱ በቅርቡ በግምገማ ወደ 26 ሚሊዮን ችግኞች ዝግጅት ተደርጓል። ይህም በየቀኑ ይጨምራል።
አሁን ላይ 40 ሚሊዮን የደንና ጥምር ደን 71 ሚሊዮን የቡና ችግኞች ለሚያዝያና ሐምሌ ተከላ ዝግጅት ተደርጓል። የተለያዩ የደን ዝርያ ያላቸው ሁለት መቶ 60 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ችግኞች በግብርናው ዘርፍ ይተከላሉ።
በሌላ በኩል የሌማት ትሩፋት ስራው ከክልል ምስረታው ጋር አብሮ መጀመሩን የገለጹት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በክልሉ እንደ ሀገር የተያዘው የሌማት ትሩፋት በወተት፣ በዶሮ ስጋ፣በማርና በአሳ ላይ እየተሰራ.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124934

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሰላሳ ዓመታት የተከናወኑ አበይት ሥራዎችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ ተከፈተ
**************
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሰላሳ ዓመታት የተከናወኑ ሥራዎችን የሚያስቃኝ ዓውደ ርዕይ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ የኦሮሞ ባህል ማዕከል ተከፍቷል።
አውደርዕዩ "የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጉዞ" በሚል እስከ መጪው ዓርብ ድረስ እንደሚቆይ ተገልጿል።
በአውደ ርዕዩ በክልል ደረጃ የሚገኙ ሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶችና የሽገር ከተማ አስተዳደር ተሳትፈዋል። አውደ ርዕዩ በክልሉ የኮሙኒኬሽን ቢሮ የተዘጋጀ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዓርብ ይቆያል።
በሳሙኤል ወንደሰን
መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጂንካ ኤርፖርት ያስገነባውን ዘመናዊ የመንገደኞች ማስተናገጃ አሰመረቀ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጂንካ ኤርፖርት ያስገነባውን ዘመናዊ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል እያስመረቀ ይገኛል።
በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታቸው መንግስቴ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ባውዲና የአሪ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ አብርሃም አታን ጨምሮ ሌሎችም የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
እንዲሁም የአሪ ዞን የአገር ሽማግሌዎች፣ የማህበረሰብ ተወካዮች እና የሀይማኖት አባቶችም በስነ-ስርዓቱ ላይ ታድመዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ምክር ቤቱ እንደ ዓባይ ሁሉ ለሀገራዊ አጀንዳዎች ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ
***************
(ኢ ፕ ድ)
እንደ ዓባይ ፕሮጀክት ሁሉ ለትላልቅ ሀገራዊ አጀንዳዎች ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ።
የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የዓባይ ግድብ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የተሳተፉበት የጋራ ፕሮጀክት ነው። ግድቡ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ ብዙ ችግሮችን ሊቀርፍ የሚችል በመሆኑ እስከዛሬ ድረስ ሁሉም ዜጎች በመረባረብ አሻራቸውን እያሳረፉበት ይገኛሉ ብለዋል።
የጋራ ምክር ቤቱም ከግድቡ ግንባታ ጀምሮ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው፤ እንደ ዓባይ ያሉ ዘመን ተሻጋሪ የልማት ሥራዎች ላይ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።
ግድቡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚታይ የልማት ጉዳይ በመሆኑ፤ ከፖለቲካ ውጪ በሆነ እይታ ውስጥ ያለና የሀገር ሀብት ነው ብለዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የግድቡን ግንባታ እየደገፈ ያለውም የጋራ ሀብታችን መሆኑን.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=124946

#የሚኒስትሮች_ምክር_ቤት ውሳኔዎች ‼️
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 28ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
👉 በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የመካከለኛ ዘመን 2017-2021 የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ነው፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚና ፊሲካል ማዕቀፉ የመንግስት በጀት ከማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታው እና የፊሲካል አቅም ጋር ተጣጥሞ እንዲዘጋጅ ለማድረግ፤ ከመንግስት ገቢ አሰባሰብ እና ሀብት አመዳደብ አኳያ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በማመላከት ለቀጣይ በጀት አመት የበጀት ዝግጅት ለማድረግ፤ የመካከለኛ ዘመን የመንግስት ገቢና ወጪ እንዲሁም የፊሲካል ሚዛን የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለመለየት እና ለማመላከት የሚያገለግል ማዕቀፍ በመሆኑ ምክር ቤቱ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
👉በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የተጨማሪ እሴት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ በሀገሪቱ የእኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ የተደረጉ ለውጦችን በህግ ማእቀፉ ውስጥ ማስገባት በማስፈለጉ፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ጫና እንዳያርፍባቸው ለማድረግ የሚያስችል ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብዓቶችን በማከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት ‼️
ዛሬ የረመዳን ወር ጾምን ምክንያት በማድረግ ከ127 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር አስጀምረናል።
በለውጡ መንግስት በጀመርነው የሰው ተኮር ስራችን የህዝባችንን የኑሮ ጫና የማቅለልና አለኝታነታችንን በተግባር የማረጋገጥ በርካታ ስራ በመስራት፣ ማዕድ ብቻ ሳይሆን ለወገኖቻችን ክብር እና ፍቅርን እያጋራን የቆየን ሲሆን በዛሬው ዕለትም ለሁሉም የአዲስ አበባ መስጅዶች የሚከፋፈል ቴምር እና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችን ደግሞ ማዕድ አጋርተናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ