Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሲንጋፖር በብሔራዊው የእፅዋት ማዕከል ባህላዊውን እፅዋት የመሰየም ሥነሥርዓት ተካፍለዋል፤ 'አራንዳ ዐቢይ አሕመድ ዝናሽ ታያቸው' የተሰኘ የኦርኪድ አበባ በስማቸው ተሰይሞላቸዋል። ይህንን ስነስርዓት በፎት‼️

ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ-ጉባኤ ተጠናቀቀ
**
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ-ጉባኤ ተጠናቀቀ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ የምልዓተ - ጉባኤውን መጠናቀቅ በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የሚተላለፉ መልዕክቶች ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉና ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸው እንዲሁም በጥብቅ የሚያወግዛቸው መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ለቤተክርስቲያንና ለሀገራችን ህዝቦች ጠቃሚ ውሳኔ አሳልፏል ብለዋል በመግለጫቸው፡፡

በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተመሥርቶ አባታዊ ምክርና ተግሣጽ ማስተላለፍ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው መሆኑን አንስተው ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የሚተላለፉ መልዕክቶች ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉና ቅዱስ ሲኖዶስ የማይቀበላቸው እንዲሁም በጥብቅ የሚያወግዛቸው ናቸው ብለዋል፡፡

ወደ ፊት እንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ወጥ የሆነ የመግለጫ አሰጣጥና የትምህርተ ወንጌል ተልእኮ ሕገ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምልዐተ ጉበኤ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ መወሰኑንም ጠቁመዋል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ ላይ በሰፊው ተወያይቶ ሊሻሻሉ የሚገባቸው ሀሳቦችን ለሚመለከተው የመንግስት ተቋም መላኩን ገልጸዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊትም የተሰጡ የማሻሻያ ሐሳቦች በአዋጁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟልም ነው ያሉት በመግለጫቸው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲገባ መወሰኑን ገልጸዋል፡፡

ለአፈጻጸም እንዲያመችም የተዘጋጀው መዋቅራዊ አደረጃጀት በሕገ ቤተ ክርስቲያኑና በቃለ ዓዋዲው ተካቶ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ መወሰኑን ጠቁመዋል፡፡

በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽህፈት ቤት ተዘጋጅቶ የቀረበው የ2017 ዓ.ም ዓመታዊ በጀት ጸድቆ ሥራ ላይ እንዲውልም ቅዱስ ሲኖዶስ መወሰኑን አስታውቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከእስያ ጉብኝታቸው ማምሻውን በመመለስ የሶስት ቀናት የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን ካጠናቀቁት የሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ተወካዮች ልዑክ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ በቤቶች ልማት፣ በቱሪዝምና በግብርና በተለይም በሀገር ውስጥ የማዳበሪያ ምርት ላይ ያተኮረ ነበር።

ሰባ ዘጠኝ ኢንቨስተሮችን ያካተተው ከፍተኛ ልዑክ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሳዑዲ አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሰልማን በህዳር ወር በሳዑዲ - አፍሪካ ጉባኤ ወቅት ያደረጉትን የሁለትዮሽ ውይይት ተከትሎ መከናወኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓም
በመዲናዋ በኮሪደር ልማት ስራ በመልማት ላይ ያሉ አከባቢዎች በምሽት‼️
ለደቡብ ሱዳን ዲፕሎማቶች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ
*
**
(ኢ ፕ ድ)

የደቡብ ሱዳን ዲፕሎማቶች በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትብብር የተዘጋጀላቸውን የሶስት ቀናት ስልጠና መርሃ ግብር በተሳካ ሁኔታ አጠናቀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በስልጠናው ማጠናቀቂያ ስነ-ስርዓት ላይ ስልጠናው ዲፕሎማቶቹ በቀጣይ በስራቸው የሚያጋጥሟቸውን ውስብስብ ፈተናዎች ለመገንዘብና ለመፍታት ጠቃሚ ክህሎት እንዲኖራቸው ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀ እንደሆነም ገልጸዋል።

መሰል ስልጠናዎች በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል ያለውን የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ሚና ይኖራቸዋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ አምባሳደር ናታሊና ኤድዋርድ ሙዩ በበኩላቸዉ ስልጠናውን ላዘጋጁት የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን አመስግነዋል።

ዲፕሎማቶቹ ስልጠናውን በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቃቸው የምስክር ወረቀት እንደተበረከተላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓም