Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከእስያ ጉብኝታቸው ማምሻውን በመመለስ የሶስት ቀናት የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን ካጠናቀቁት የሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ተወካዮች ልዑክ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ በቤቶች ልማት፣ በቱሪዝምና በግብርና በተለይም በሀገር ውስጥ የማዳበሪያ ምርት ላይ ያተኮረ ነበር።

ሰባ ዘጠኝ ኢንቨስተሮችን ያካተተው ከፍተኛ ልዑክ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሳዑዲ አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሰልማን በህዳር ወር በሳዑዲ - አፍሪካ ጉባኤ ወቅት ያደረጉትን የሁለትዮሽ ውይይት ተከትሎ መከናወኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓም
በመዲናዋ በኮሪደር ልማት ስራ በመልማት ላይ ያሉ አከባቢዎች በምሽት‼️
ለደቡብ ሱዳን ዲፕሎማቶች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ
*
**
(ኢ ፕ ድ)

የደቡብ ሱዳን ዲፕሎማቶች በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትብብር የተዘጋጀላቸውን የሶስት ቀናት ስልጠና መርሃ ግብር በተሳካ ሁኔታ አጠናቀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በስልጠናው ማጠናቀቂያ ስነ-ስርዓት ላይ ስልጠናው ዲፕሎማቶቹ በቀጣይ በስራቸው የሚያጋጥሟቸውን ውስብስብ ፈተናዎች ለመገንዘብና ለመፍታት ጠቃሚ ክህሎት እንዲኖራቸው ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀ እንደሆነም ገልጸዋል።

መሰል ስልጠናዎች በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል ያለውን የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ሚና ይኖራቸዋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ አምባሳደር ናታሊና ኤድዋርድ ሙዩ በበኩላቸዉ ስልጠናውን ላዘጋጁት የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን አመስግነዋል።

ዲፕሎማቶቹ ስልጠናውን በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቃቸው የምስክር ወረቀት እንደተበረከተላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓም
"ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት የሁለትዮሽና ግንኙነት ያድጋል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ
******
(ኢ ፕ ድ)

በአዲሱ የስልጣን ዘመኔ ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት የሁለትዮሽና ግንኙነትና አጋርነት ያድጋል ሲሉ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ገለጹ፡፡

በሕንድ በተካሄደው ምርጫ ናሬንድራ ሞዲ ለሦስተኛ ጊዜ ማሸነፋቸውን ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወቃል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ላስተላለፉላቸው መልዕክት ምሰጋና አቅርበዋል።

ሕንድ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የሁለትዮሽ ግንኙነት ከፍተኛ ትኩረት ትሰጣለችም ብለዋል።

ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓም
#ጽዱኢትዮጵያ #CleanEthiopia

በሰሜን አሜሪካ የአትሌቶች ማህበር አባላት 8 ሺህ300 የአሜሪካን ዶላር ለ“ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” ድጋፍ አደረጉ

👉 እስከ አሁን 29 ሺህ 445 የአሜሪካ ዶላር እንዲሁም 74 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ተሰብስቧል፣
****
(ኢ ፕ ድ)
ለ“ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” በሰሜን አሜሪካ የአትሌቶች ማህበር አባላት 8 ሺህ300 የአሜሪካን ዶላር የገንዘብና አንድ መጸዳጃ ቤት ለመስራት የአይነት ድጋፍ አደረጉ።

ድጋፋቸውን በአሜሪካ የኢትየጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ አስረክበዋል።

የማህበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት አትሌት ሀይሉ መኮንን ኢትዮጵያ በምትፈልጋቸው ወቅት ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የማህበሩ አባላት በተለያዩ አገራዊ ጥሪዎች ላይ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አምባሳደር ስለሺ በቀለ
ጠቅሰው አሁንም ማህበሩ ለ”ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” ኢንሼቲቭ ላደረገው ድጋፍ ያላቸውን ምስጋና አቅርበዋል።

በአሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ለ”ጽዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” እስከ አሁን በአጠቃላይ በጥሬ ገንዘብ 29 ሺህ 445 የአሜሪካ ዶላር እንዲሁም 74 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ተሰብስቧል።

በዓይነት 21 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ 14 መጸዳጃ ቤቶችን ለመስራት ቃል መግባታቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓም
በአማራ ክልል በተደረገ የሰላም ጥሪ ከ10 ሺህ በላይ የታጠቁ ኃይሎች ለሰላም እጃቸውን ሰጥተዋል
****************
(ኢ ፕ ድ)
አማራ ክልል ያደረገውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ ከ10 ሺህ በላይ የታጠቁ ኃይሎች ለሰላም እጃቸውን እንደሰጡ የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ በተሠራው የሕግ ማስከበር ሥራ የስምንተኛ ክፍል ፈተና በሁሉም የወረዳ ማዕከላት መድረሳቸው ተመላክቷል።

የቢሮው ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የነበረውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በተሠራው የሕግ ማስከበር ሥራ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል።

ክልሉ ባደረገው የሰላም ጥሪ መሠረት ለሰላም እጃቸውን የሰጡት ከ10 ሺህ በላይ የታጠቁ ኃይሎች ምክርና ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ትውልድ አካባቢያቸው መመለሳቸውን አስታውቀዋል።

በአንዳንድ አካባቢዎች ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የጽንፈኛ ኃይሎችን እንቅስቃሴ በመግታት ሰላም ለማስፈን በርካታ .....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129406
አሳሳቢው የትራንስፖርት ችግርና የተገልጋዮች መጉላላት
***************
(ኢ ፕ ድ)

መገናኛ እንደ ስሟ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ የከተማዋ ነዋሪዎችን ስታገናኝ ትውላለች። ከፍተኛ የሕዝብና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ከሚያስተናግዱባቸው የከተማዋ ቦታዎች መካከልም አንዷ ናት።

በአሁኑ ወቅት ደግሞ ከኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ ሌላ መልክ እየያዘች መጥታለች። እኔ በቦታው የተገኘሁት አንድ ሰአት ተኩል ሲል ነው። ትራንስፖርት ፈላጊው ሕዝብ ወደ ሥራ አልያም ጉዳዩን ለማስፈጸም በየአቅጣጫው ይጣደፋል።

የትራንስፖርት ጉዳይ ግን ረፋድና አመሻሽ ላይ በአካባቢው ለተገኘ ተመልካች ጭንቅ የሚል ስሜት ይፈጥራል። ለታክሲ ብቻ ሳይሆን ለአውቶቡስና ለሀይገር ተሰልፎ የሚታየው ሰው ለዓይን ይደክማል።

ከረጃጅሞቹ ሰልፎች ወደ መጨረሻ የተሰለፈውን በመጠጋት ስለችግሩ አስተያየቱን እንዲያጋራኝ ጠየኩት። ቃለ አብ እውነቱ ይባላል። የኮንስትራክሽን ባለሙያ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ስድስት ኪሎ አካባቢ በሕንፃ ግንባታ ውስጥ እየሠራ እንደሆነ ነግሮኛል። ሥራዬ በተለያዩ ቦታዎች......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129405