Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በአዲስ አበባ ከተማና በተለያዩ ክልልች የ8ኛ ክፍል ፈተና መሰጠት ጀመረ
****************
(ኢ ፕ ድ)
አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ክልልች 2016 ዓም የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀምሯል።

በዛሬው ዕለትም በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር፣ በኦሮሚያ፣ አፋር፣ አማራ፣ ጋምቤላ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች እየተሰጠ ይገኛል።

ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና በአፋር ክልል መሰጠት መጀመሩን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱ ሀሰን ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በክልሉ የ8ኛ ክፍል ፈተና በ104 የፈተና ጣቢያዎች ለ10 ሺህ 179 ተማሪዎች እየተሰጠ ይገኛል፡፡

የፈተና ጣቢያዎችን የመለየት፣ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የመፍጠርና ለተማሪዎች ኦረንቴሽን በመስጠት ፈተናው መጀመሩን ገልጸዋል፡፡ ፈተናው ዛሬ እና ነገ ይሰጣል።

የማህበረሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ከኩረጃ ነጻ የሆኑና በውጤታቸው ብቻ የሚያልፉ ተማሪዎችን ለማፍራት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

በአዲስ አበባ ሁለት ሺህ 200 ፈታኞች፣ 700 ሱፐር ቫይዘሮች በ182 የፈተና ጣቢያዎች ፈተናው እየተሰጠ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮው አስታውቋል።

በሄለን ወንድምነው
ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓም
የውሃ ሀብትን በዘላቂነት አልምቶ ለመጠቀም በቅንጅት መሥራት ይገባል
***************
(ኢ ፕ ድ)
የውሃ ሀብትን በዘላቂነት አልምቶ ለመጠቀም የጋራ እቅድ ማውጣት በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ የብሔራዊ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የብሔራዊ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር አስተባባሪ ብዙነህ አስፋው (ዶ/ር) በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን ወደ መሬት አውርዶ ለመተግበር የተፋሰስ ስትራቴጅክ እቅድ ወሳኝ ነው፡፡

ውሃን በፍትሀዊነት ለመጠቀም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ እቅድ አውጥተው በቅንጅት ሊሠሩ ይገባል፡፡

የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርና ተጠቃሚነትን እውን ለማድረግ የዓባይ፣ የአዋሽ፣ የስምጥ ሸለቆ፣ የዋቤ ሸበሌ፣ የገናሌ ዳዋና የኦሞ ጊቤ ተፋሰሶች ስትራቴጅክ እቅድ ወጥቶ መጽደቁን ገልጸው፤ በዚህም መሠረት በሀገሪቱ ካሉት ተፋሰሶች 75 በመቶ የሚሆኑት ስትራቴጂክ እቅድ አላቸው ብለዋል፡፡

በቀጣይም የተከዜንና የመረብ ተፋሰሶችን ስትራቴጂክ እቅድ በማውጣት የማስጸደቅ ሥራ በሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንደሚሠራ......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129696
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰብሳቢነት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ100 ቀናት ግምገማ ቁልፍ የሆኑ ሴክተሮችን አፈፃፀም በጥልቀት በመመልከት ማካሄድ ጀምሯል።

ከግምገማ መድረኩ በተጓዳኝ ከ2010 እስከ 2015 ዓመተ ምህረት የተላለፉ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎችን የያዘ መፅሃፍ ይፋ ሆኗል።

ይህ መፅሃፍ በተጠቀሰው ዘመን የተላለፉ የፖሊሲ ውሳኔዎችን በዝርዝር ያመለክታል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ክፍል የሚያከናውነው የመሰነድ ተግባር አንዱ የሆነው ይህ መፅሃፍ ለታሪክ ስነዳ እና መረጃውን ለሚሹ ሁሉ ጠቃሚ የሆነ የሰነድ ዝግጅት ስራ አካል ነው።

ዛሬ ይፋ የሆነው መፅሃፍ ውስን ቅጂዎች ለፌደራል እና ለክልል ተቋማት የሚሰራጩ ሲሆን መረጃውን ለሚፈልጉ ሁሉ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ድረገጽ ላይ የሚጫን ይሆናል።

ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓም
የክብር ዶክተር አርትስት አሊ ቢራ ፋውንዴሽን ሰኔ 16 ቀን 2016 ለህዝብ ይፋ ይደረጋል
******************
( ኢ ፕ ድ)
የክብር ዶክተር አርትስት አሊ ቢራ ፋውንዴሽን የምሰረታ ይፋ ማድረጊያ መረሐግብር ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ደራራ ከተማ በሰጡት መግለጫ፣ ፋውንዴሽኑ በሀገር ውስጥና በውጭ ከተመሠረተ ዓመት ቢሆነውም የክብር ዶክተር አርትስት አሊ ቢራ ፋውንዴሽን ሰኔ 16 ቀን 2016 ለህዝብ ይፋ ይደረጋል።

አርትስቱ በህይወት እያለ ባህልንና ማህበራዊ ጉዳዮችን በዜማና በጥበብ ለህዝብ ሲያደርስ መቆየቱን አስታውሰው ፋውንዴሽኑ የአርቲስቱን ስራዎች ለማስቀጠል እንደምሰራ ገልፀዋል።ቢሮው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

የፋውንዴሽኑ ዳይሬክተር አቶ አሳድ ፋህሚ በበኩላቸው የፋውንዴሽኑ ዋና አላማ የአርትስት አሊ ቢራን ሥራዎችና ራዕዎችን ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ነው ብለዋል።

በዚህም መሠረት ኪነጥበብን ማጎልበት፣ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ማስፋፋት፣ የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል፣ በጎ ሥራዎችን ማከናወን ላይ በትኩረት መሥራት የፋውንዴሽኑ አላማ መሆኑ ተናግረዋል።

የአርትስቱ ባለቤትና የፋውንዴሽኑ መስራች ወ/ሮ ኢሊሊ ማርቆስ ቢራ በበኩላቸው ፋውንዴሽኑ አልሞ የተነሳው አርትስቱ በህይወት እያለ መሥራት የሚፈልጋቸውን ስራዎች እውን ማድረግ ነው።

ይህ እንድሳካ ሀገር ውስጥ ውጭ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል።

በወይንሸት ካሳ
ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓም
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከሩሲያ አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ተወያዩ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከሩሲያ አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ከብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን በብሪክስ ማዕቀፍ ስር ትብብራቸውን ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማስፋት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ሰኔ 2016 ዓም