Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰብሳቢነት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ100 ቀናት ግምገማ ቁልፍ የሆኑ ሴክተሮችን አፈፃፀም በጥልቀት በመመልከት ማካሄድ ጀምሯል።

ከግምገማ መድረኩ በተጓዳኝ ከ2010 እስከ 2015 ዓመተ ምህረት የተላለፉ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎችን የያዘ መፅሃፍ ይፋ ሆኗል።

ይህ መፅሃፍ በተጠቀሰው ዘመን የተላለፉ የፖሊሲ ውሳኔዎችን በዝርዝር ያመለክታል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ክፍል የሚያከናውነው የመሰነድ ተግባር አንዱ የሆነው ይህ መፅሃፍ ለታሪክ ስነዳ እና መረጃውን ለሚሹ ሁሉ ጠቃሚ የሆነ የሰነድ ዝግጅት ስራ አካል ነው።

ዛሬ ይፋ የሆነው መፅሃፍ ውስን ቅጂዎች ለፌደራል እና ለክልል ተቋማት የሚሰራጩ ሲሆን መረጃውን ለሚፈልጉ ሁሉ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ድረገጽ ላይ የሚጫን ይሆናል።

ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓም
የክብር ዶክተር አርትስት አሊ ቢራ ፋውንዴሽን ሰኔ 16 ቀን 2016 ለህዝብ ይፋ ይደረጋል
******************
( ኢ ፕ ድ)
የክብር ዶክተር አርትስት አሊ ቢራ ፋውንዴሽን የምሰረታ ይፋ ማድረጊያ መረሐግብር ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ደራራ ከተማ በሰጡት መግለጫ፣ ፋውንዴሽኑ በሀገር ውስጥና በውጭ ከተመሠረተ ዓመት ቢሆነውም የክብር ዶክተር አርትስት አሊ ቢራ ፋውንዴሽን ሰኔ 16 ቀን 2016 ለህዝብ ይፋ ይደረጋል።

አርትስቱ በህይወት እያለ ባህልንና ማህበራዊ ጉዳዮችን በዜማና በጥበብ ለህዝብ ሲያደርስ መቆየቱን አስታውሰው ፋውንዴሽኑ የአርቲስቱን ስራዎች ለማስቀጠል እንደምሰራ ገልፀዋል።ቢሮው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

የፋውንዴሽኑ ዳይሬክተር አቶ አሳድ ፋህሚ በበኩላቸው የፋውንዴሽኑ ዋና አላማ የአርትስት አሊ ቢራን ሥራዎችና ራዕዎችን ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ነው ብለዋል።

በዚህም መሠረት ኪነጥበብን ማጎልበት፣ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ማስፋፋት፣ የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል፣ በጎ ሥራዎችን ማከናወን ላይ በትኩረት መሥራት የፋውንዴሽኑ አላማ መሆኑ ተናግረዋል።

የአርትስቱ ባለቤትና የፋውንዴሽኑ መስራች ወ/ሮ ኢሊሊ ማርቆስ ቢራ በበኩላቸው ፋውንዴሽኑ አልሞ የተነሳው አርትስቱ በህይወት እያለ መሥራት የሚፈልጋቸውን ስራዎች እውን ማድረግ ነው።

ይህ እንድሳካ ሀገር ውስጥ ውጭ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል።

በወይንሸት ካሳ
ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓም
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከሩሲያ አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ተወያዩ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከሩሲያ አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ከብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን በብሪክስ ማዕቀፍ ስር ትብብራቸውን ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማስፋት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ሰኔ 2016 ዓም
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ከሀምሌ 3 ጀምሮ በወረቀትና በኦንላይን ይሰጣል
******
(ኢ ፕ ድ)

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ከሀምሌ 3 ቀን 2016 ዓም ጀምሮ በወረቀትና በኦንላይን እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሰታወቀ።

የአገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ፣ በሰጡት መግለጫ፤ ከትግራይ ክልል ውጭ ባሉት ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሐምሌ 3 እስከ 5 ቀን 2016 ዓ.ም፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ከሀምሌ 9 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ድረሰ ፈተናውን እንደሚወስዱ አስታውቀዋል፡፡

የዘንድሮው ፈተና በወረቀትና በኦንላይን ጭምር እንደሚሰጥም ገልጸዋል፡፡

የትግራይ ክልልን ጨምሮ 701ሺህ 489 የሚሆኑ ተማሪዎች የሚፈተኑ ሲሆን፤ በማህበራዊ ሳይንስ 369 ሺህ 60፣ በተፈጥሮ ሳይንስ 332ሺህ 429 ተማሪዎች ለፈተናው እንደሚቀመጡ ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ ውስጥም 99 በመቶ ያህሉ ተፈታኞች በመጀመሪው ዙር የሚፈተኑ ሲሆን፤ ወደ አንድ በመቶ የሚጠጉ ተማሪዎች በተለይ በጸጥታ ችግር ትምህርት ቀድመው ባለመጀመራቸው ምክንያት በሁለተኛው ዙር እንዲፈተኑ የሚያስችሉ ዝግጅቶች ማደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

የዘንድሮው ፈተና እንደ ቀድሞው በወረቀት ብቻ ሳይሆን በኦንላይንም እንደሚሰጥ ጠቅሰዋው ከኦንላይን የፈተና አሰጣጥ አኳያ በፌዴራልና በክልል ደረጃ በተቋቋመ ኮሚቴ አማካኝነት ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በአዲሱ ገረመው

ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓም
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕዝብ በዓላት እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ አጸደቀ
*******
(ኢ ፕ ድ)

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባው የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አጽድቋል።

በተመሳሳይ ሶስት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል።

ረቂቅ አዋጁን በዝርዝር ሲመለከቱ የነበሩት የጤና፣ ማህበራዊ ልማትና ስፖርት ጉዳዮች እና የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች በጋራ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

የውሳኔ ሀሳቡን ያቀረቡት የጤና፣ ማህበራዊ ልማትና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ወርቀስሙ ማሞ፤ አዋጁ ላይ የተካተቱ ዋና ዋና ሀሳቦችን በዝርዝር አቅርበዋል።

የሕዝብ በዓላት ለዜጎች ሥነ-ምግባርና ስነ-ልቦና ግንባታ እንዲሁም ለሀገርና ለህዝብ ያላቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ከፍተኛ ስለመሆኑ በውሳኔ ሀሳቡ ተብራርቷል።

የሕዝብ በዓላት ኃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ታሪካዊ እሴታቸውን ጠብቀው በሰላም በድምቀት እና የዜጎችን የእርስ በእርስ መልካም ግንኙነትና መተሳሰብ በሚያጎለብት ሁኔታ እንዲከበሩ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ሰብሳቢዋ ገልጸዋል።

የህዝብ በዓላት አከባበርና ሥርዓት ኃይማኖታዊና ባህላዊ ይዘታቸውን ጠብቀው ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሸጋገር ያለው አስተዋፅዎና ለሀገራዊ ዕድገት ወሳኝ ሚና ያላቸው በመሆኑ ከመንግስት የሚጠበቀውን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ እንዲሁም በቂ የሚዲያ ሽፋን የሚሰጥ እንደሆነም በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ተብራርቷል።

ነባሩ የሕዝብ በዓላትና የዕረፍት ቀን መወሰኛ አዋጅ የሕዝብ በዓላት ሲከበሩ ጥቅም ሊያስገኙ በሚችሉ መልኩ በድምቀት የሚከበሩበትን ዝርዝር የአከባበር ሥነ-ሥርዓት አለማስቀመጡም ተመላክቷል፡፡

ይህ አዋጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕዝብ በዓላትና የበዓላትን አከባበር የሚመለከት ሲሆን፤ ክልሎች በራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ህግ አውጥተው በክልል ደረጃ የሚከበሩት መወሰን እንደሚችሉ ገልፀዋል።

በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመስልና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራቱን ከምክር ቤቱ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓም
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሦስተኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ሆናለች
****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢንቨስትመንት ከባቢ ሁኔታን ማሻሻል በመቻሉ በ2016 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሦስተኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆን መቻሏን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ሐና አርዓያሥላሴ እንደገለጹት፤የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንቨስትመንት ከባቢ ሁኔታን ለማሻሻል ብዙ የአሠራር ማሻሻያዎችና ለውጦች አድርጓል፡፡

የኢንቨስትመንት ከባቢ ሁኔታን ማሻሻል በመቻሉ እየተገባደደ ባለው የ2016 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሦስተኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለመሆን በቅታለች፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት በምሥራቅ አፍሪካ ቁጥር አንድ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆን መቻሏን አውስተው፤ በቀጣይ ተጨማሪ ኢንቨስትመንቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ጠንካራ ሥራ እየተሠራ ስለመሆኑም ገልጸዋል፡፡

እንደ ኮሚሽነር ሐና ገለጻ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንቨስትመንት ከባቢ ሁኔታን ለማሻሻል ብዙ የአሠራር ማሻሻያዎችና ለውጦች ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በዋናነት መሠረተ ልማት ላይ የተደረጉ ኢንቨስትመንቶች.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን https://press.et/?p=129735
ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት በጋራ ለማደግ የሚያስችል ነው
***************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት ከቀጣናው ሀገሮች ጋር በጋራ ለማደግ የሚያስችል መሆኑን የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጀማል የሱፍ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጀማል የሱፍ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት በቀጣናው ሀገራት ብዙ ዕድሎችን ይፈጥራል፡፡

በተለይ ሀገሮቹ በጋራ ችግር ፈቺ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ምርምሮችን በመስራት በጋራ ለማደግ ያስችላቸዋል።

በምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በተለይ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ያለውን የረዥም ጊዜ ልምድ በመጠቀም የአካባቢውን አርሶ አደርና የማህበረሰቡን ፍላጎት መሠረት በማድረግ ችግር ፈቺ የምርምር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ስርጸት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኘ ጀማል (ዶ/ር) ገልጸው፤ይሁንና ዩኒቨርሲቲው የሚሠራውን.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129736