Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ በክልሉ የተከናወኑ የግብርና ስራዎችን አሰመልክተው ለኢፕድ በሰጡት ማብራሪያ ካነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች‼️

👉 ከ10 ሚሊየን ሄክታር የማያንስ ሊታረስ የሚችል መሬት አለ፤

👉 ከዚህ ውስጥ ከለውጡ በፊት ሲታረስ የነበረው ወደ 400ሺ ሄክታር ወደ 900 ሺ ሄክታር ማልማት ተችሏል፣

👉 ተጨማሪ 50ሺ ሄክታር በማልማት በአጠቃላይ ወደ 1 ሚሊዮን ሄክታር ለማሳደግ ይሰራል፣

👉 በክልሉ የተለያዩ ሰብል አይነቶችን ጨምሮ ይመረት የነበረው በዓመት ከ10 ሚሊዮን ኩንታል የማይበልጥ ነበር፣

👉 በአሁኑ ጊዜ ወደ 26 ሚሊዮን ኩንታል የተለያዩ ምርቶችን ማምረት ተችሏል፣

👉 በዘንድሮ ዓመት በጎዴና ሲቲ ዞኖች በ3 ሺ ሄክታር ላይ የሩዝ ምርት ለማምረት በሙከራ ደረጃ እየተሠራ ነው፣

👉 በፌደራል መስኖ እና ቆላማ ሚኒስቴር ድጋፍ ከስምንት ቢሊየን ብር በላይ የመስኖ ፕሮጀክቶች ተጀምረዋል፣

👉 ከግብርናው ጋር ተያይዞ በእንስሳት ሃብትም በጣም ጥሩ እምርታ እየታየ ይገኛል፣

👉 የእንስሳት ኳራንቲን ማዕከላትን ሠርቶ እንስሳት ለውጭ ገበያ እንዲቀርቡ ከማድረግ አንጻር ተግዳሮቶች አሉ፣

ርዕሰ መስተዳድሩ ከኢፕድ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129495
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ውብ_አዲስ‼️

አራት ኪሎ በኮሪደር ልማቱ ወቅትና አሁን‼️
መንግሥት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ተግባራዊ በማድረግ ብዙ ርቀት ተጉዟል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
መንግሥት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ አቅርቦት ተደራሽ በማድረግ፣ የመሠረተ ልማቶችን መልሶ በመገንባትና በጀት በመመደብ የሰላም ስምምነትን ተግባራዊ በማድረግ ብዙ ርቀት መጓዙን የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) ፓርቲ አባል ኮማንደር ገብረመስቀል ገብረሚካኤል ገለጹ።

የትዴፓ ፓርቲ አባል ኮማንደር ገብረመስቀል ገብረሚካኤል ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤መንግሥት የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ብዙ ርቀት ተጉዟል።

በትግራይ ክልል የሰብዓዊ አቅርቦት ተደራሽ በማድረግ፣ የመሠረተ ልማቶችን መልሶ በመገንባት፣ በጀት በመመደብ፣ የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግና ሌሎች ሥራዎችን በማከናወን የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ተፈጻሚ እንዲሆን ብዙ ረቀት ተጉዟል።

በፌዴራል መንግሥት እና በሕወሓት መካከል የተደረገውን የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ተከትሎ መንግሥት ብዙ አወንታዊ ሥራዎች በክልሉ ሠርቷል ያሉት ኮማንደር ገብረመስቀል፤አሁንም መንግሥት ኃላፊነቱን በሚገባ እየተወጣ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129817
በአንድ ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባ ኩባንያ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ፔሪ ሜትር ኮንሰልቲንግና ትሬዲንግ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከአንድ ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ለሚገነባ ኩባንያ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

ኩባንያ ከጤፍ የተለያዩ ስናኮችንና ደረቅ የምግብ ዓይነቶችን በማምረት ወደ አውሮፓ፤ አሜሪካና የሩቅ ምስራቅ ሀገራት ኤክስፖርት እንደሚያደርግ ተገልጿል።

የኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም፣ ባለፉት 3 ዓመታት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለመጨመር የሚያስችሉ የተለያዩ ሪፎርሞች ተተግብረዋል።

ኮርፖሬሽኑ ሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም፤ የኮርፖሬት ሀብት አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አለማየሁ ሰይፉ እና የፔሪ ሜትር ኮንሰልቲንግ ማኔጅንግ ዳይሬክተር ቤተልሄም ጥላሁን ጋር በጋራ አስቀምጠዋል።

ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓም
በክልሉ በአረንጓዴ አሻራ 18 ነጥብ 5 ሚሊዮን የፍራፍሬ ችግኞች ይተከላሉ
***************
(ኢ ፕ ድ)
አማራ ክልል በ2016/17 የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር 18 ነጥብ 5 ሚሊዮን የፍራፍሬ ችግኞችን ለመትከል ማቀዱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ እስመለዓለም ምህረቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ክልሉ ለ2016/17 የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገ ይገኛል።

አማራ ክልል በ2016/17 የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አንድ ነጥብ 59 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል አቅዶ እየሠራ መሆኑን ገልጸው፤ እስካሁን አንድ ነጥብ 34 ቢሊዮን ችግኞችን ለተከላ ዝግጁ በማድረግ የእቅዱን 76 በመቶ ማሳካት መቻሉን አስታውቀዋል።

የሚተከሉት ችግኞች ፍራፍሬ፣ ለደን ሽፋን፣ ለምግብነትና የአፈር ለምነትን የሚጨምሩ እንዲሁም ለአካባቢ ጥበቃ የሚያገለግሉ የዛፍ ዝርያዎች መሆናቸውን አስረድተዋል። አጠቃላይ ከሚተከሉት አንድ ነጥብ 59 ቢሊዮን ችግኞች መካከል 18 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚሆኑት.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129829
በወላይታ ዞን በዘንድሮ ዓመት 162 ሺህ ኩንታል እሸት ቡና ተሰብስቧል
***************
(ኢ ፕ ድ)
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ከመስከረም ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ 162 ሺህ ኩንታል እሸት ቡና መሰብሰቡን የዞኑ ቡናና ቅመማ ቅመም ጽህፈት ቤት ገለጸ። ከዞኑ ስድስት ሺህ ኩንታል የቡና ምርት ለውጭ ገበያ መቅረቡን ተጠቁሟል።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ክፍሌ ካውሌ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጀት እንደገለጹት፤ በዘንድሮ ዓመት የምርት ዘመን ከዞኑ 162 ሺህ ኩንታል እሸት ቡና ተሰብስቧል።

የዞኑን የቡና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የተለያዩ የግብርና ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመው፤ አምራች አርሶ አደሮች ጥራት ያለው ቡና እንዲያዘጋጁ የሚረዱ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል።

ከቡና ወጪ ንግድ ጋር በተያያዘ ከዞኑ ስድስት ሺህ ኩንታል ምርት ለውጭ ገበያ መላክ ተችሏል ሲሉ አስረድተዋል።

ከዓለም የቡና ገበያ መውረድ ጋር ተያይዞ የዞኑ የቡና ገበያም የመቀነስ አዝማሚያ እንዳለው አመላክተው፤ በቀጣይ እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ ወደተለያዩ......

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129825
የኦሮሚያ ክልል ከ413 ሚሊዮን በላይ የሻይ ቅጠል ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት አደረገ
**************
(ኢ ፕ ድ)
የኦሮሚያ ክልል በመጪው ክረምት ወቅት ከ413 ሚሊዮን በላይ የሻይ ቅጠል ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ።

ሀገሪቱ በዘርፉ ከምታገኘው ገቢ 70 በመቶ ያህሉ የሚሸፈነው በክልሉ እንደሆነ ተጠቁሟል።

የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የቡናና ሻይ ዘርፍ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሐመድሳኒ አሚን በክልሉ ያለውን የሻይ ቅጠል ልማት ያለበትን ሁኔታ አስመልክተው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት ማብራሪያ፤ ክልሉ የሻይ ቅጠል ልማትን ጨምሮ በግብርና ውጤቶች ካለው አቅም አንጻር የተለያዩ የግብርና ሥራዎችን በስፋት እያከናወነ ይገኛል።

በክልሉ በክረምት ወቅት ከ413 ሚሊዮን በላይ የሻይ ቅጠል ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል።

በተለይ የሻይ ቅጠልን እንደ አቮካዶና ሌሎች ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የግብርና ምርቶች በስፋት አልምቶ ለሀገር ኢኮኖሚ ለማዋል በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልጸው፤የሻይ ቅጠል ልማት ከተጀመረብት 2013 ዓ.ም ጀምሮ አንደ ሀገር ሁለት ሺህ ሄክታር ብቻ እየለማ ከነበረበት አሁን ላይ አርሶ አደሩን ከኢንቨስተሩ ጋር በማስተሳሰር አቅምን.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=129805
የአማራ ክልል የ2016 የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር በባህርዳር ከተማ ተጀመረ
*********************
(ኢ ፕ ድ)

የአማራ ክልል የ2016 የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሐግብር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ በባህርዳር ከተማ አስጀምረዋል።

በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ፣ የብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ፣ የባህር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማውን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አረጋ ከበደ በማስጀመሪያ ስነ-ስርአቱ ላይ እንደገለጹት የበጎ ፍቃድ አገልግሎቱ ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የበኩሉን መወጣት አለበት።

ዛሬ በባህር ዳር ከተማ የተጀመረው የአቅመ ደካማ ቤቶችን የማደስና የመጠገን ተግባር ሌሎች የልማት ተግባራትን አካቶ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ያለው ለሌለው በማካፈል እርስ በርስ መረዳዳት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ያሉት አቶ አረጋ፣ ለክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባር ስኬታማነት የሁሉም አስተዋጾ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በመሆኑም ባለሃብቱ በገንዘቡ፣ ባለሙያው በእውቀቱ፣ ወጣቱ በጉልበቱ እንዲሁም የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ህዝቡን የማስተባበር የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤት ከማደስ፣ ከመጠገንና በአዲስ መልክ ከመስራት ባለፈ የተለያዩ የልማት ተግባራት ይከናወናሉ ሲሉም ገልጸዋል።

በዋናነት የአካባቢ ጽዳት፣ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር፣ የወባ መከላከል እና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው የልማት ሥራዎች በትኩረት እንደሚሰሩ አመልክተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓም
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️
ዛሬ ጠዋት የጂቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ ከፕሬዚዳንት እስማኤል ዑማር ጉሌ መልዕክት ይዘው መጥተዋል፤ በጽሕፈት ቤታችን ተቀብያለሁ። እንዲህ ያሉት ግንኙነቶች በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ለንግግርና ትብብር አውታር በመሆን የጋራ መግባባትን ያሳድጋሉ።
ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓም