ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለ2016 የዒድ አል አድሃ በዓል ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ካነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች ‼️
👉 ነቢዩ ኢብራሂም በአላህ ትእዛዝ ልጃቸውን ለመሥዋዕትነት ያዘጋጁበት፤ ጽናታቸው ተፈትኖ ያሸነፉበት በዓል ነው፣
👉 ማንኛውም ፈተና በጽናት ካለፉት ዋጋው ከፈተናው በላይ መሆኑን እንማርበታለን፣
👉 ኢትዮጵያን ታላቅና የበለጸገች ሀገር ለማድረግ ስንነሣ ፈተናው ከባድ እንደሚሆን እናምን ነበር፣
👉 ነቢዩ ኢብራሂም ልጃቸው ኢስማኤልን ሳይሆን በምትኩ ከአላህ የተሰጣቸውን በግ ሠዉተዋል፣
👉 የሕዝባችንን ዘላቂ ጥቅሞች ለማስከበርና ከዛሬው የተሻለ ነገን ለመፍጠር ስንል፣ ብዙ ነገሮችን ሠዉተናል፤ ከምንወደው አካባቢ ወደ ሌላ ሄደናል፣
👉 ያለ መሥዋዕትነት የሚያድግ ሕዝብ፣ ያለ መሥዋዕትነት የሚበለጽግ ሀገር የለም፣
👉 የኮሪደር ልማቱን በዚህ መልኩ በመሥዋዕትነት ነው የሠራነው፡፡ ፍሬው ግን እጅግ ጣፋጭ መሆኑን አይተናል፣
👉 ሰላማችንን ለማስፈን ነፍጥን መጣል፤ ከጫካ መውጣትና የራስን ዋሻ ትቶ ወደ መስኩ መውጣትን ይፈልጋል፣
👉 ሁላችንም ለመሥዋዕትነት ከተዘጋጀን የማይሳካ የሰላም መንገድ የለም፣
👉 እንደ ልጅ ያሳደግናቸው ብዙ ልማዶች፣ ጠባዮች፣ አመለካከቶች፣ ርእዮተ ዓለሞችና አካሄዶች አሉን፡፡ እነርሱን ለሀገርና ለሕዝብ ጥቅም ስንል ለመሠዋት ዝግጁ ከሆንን፣ ውጤቱ ከሰላም በላይ ነው፣
👉 ምክክር የሚሳካው የተሻለ ሐሳብና የላቀ ዕውቀት በማዋጣት ብቻ አይደለም፤ ሌላ ወሳኝ ነገር ይፈልጋል፡፡ እርሱም መሥዋዕትነት ነው፣
👉 ከእኔ የተሻለ ሐሳብና ልምድ፣ ዕውቀትና ጥበብ ሊኖር ይችላል ብለን ማመንና መቀበል አለብን፣
👉 ልክ ልኩን ከመንገር፤ ነጥብ ከማስቆጠር፤ ጀግና ጀግና ከመጨዋት የወጣ ትኁት ሰብእና መያዝ አለብን፣
👉 እንደ ነቢዩ ኢብራሂም ያሳደግናቸውን ብቻ ሳይሆን አብረውን ያደጉትን ብዙ ጠባዮች ለመሠዋት መዘጋጀትን ይጠይቃል፣
👉 መሥዋዕትነት የሚከፍሉ ዜጎች በበዙ ቁጥር፣ ምክክር የላቀ ውጤት ያስገኛል፡፡
👉 የኮሪደር ልማታችን በየከተሞቻችን እንዲስፋፋ፤ ሰላማችን የጸና እና የማይደፈርስ እንዲሆን፤ ሀገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ተካሂዶ እንዲሳካ - ያሳደግናቸውንና ያደጉብንን አንዳንድ ነገሮች መሥዋዕት ለማድረግ እንዘጋጅ፣
👉 ከጠመንጃ ወደ ማጨጃ እንዛወር፡፡ ከዲሞትፈር ወደ ምክክር እንምጣ፡፡ ከብሔር ግጭት ወደ ሐሳብ ፍጭት እንሻገር፡፡ የምንወደውን፣ የምንፈልገውንና ያሳደግነውን እንኳን ቢሆን ለሀገር ስንል ለመሠዋት እንዘጋጅ፡፡
መልካም በዓል ይሁን፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ስኔ 8 ቀን 2016 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በ850 ሚሊዮን ብር የተገዙ ዘመናዊ የርጭት አውሮፕላኖችን ስራ አስጀመሩ
*******
(ኢ ፕ ድ)
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በ850 ሚሊዮን ብር የተገዙ አምስት ዘመናዊ የርጭት አውሮፕላኖች (ኤር ትራክተርስ) በይፋ ስራ አስጀምረዋል።
ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝና ሌሎች አደጋዎችን ለመቆጣጠር የራሷ የኬሚካል ርጭት አውሮፕላኖች ስላልነበራት ለኪራይ እስከ 13 ቢሊየን ብር ወጪ ስታደርግ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በራሷ አቅም የአደጋ መቆጣጠሪያ የኬሚካል ርጭት አውሮፕላኖች እንዲኖራት ይደረጋል ማለታቸው ይታወሳል።
ይህን ተከትሎም መንግሥት አምስት ዘመናዊ የኬሚካል ርጭትን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ ዘመናዊ ኤር ትራክተሮችን ግዥ ፈጽሞ በዛሬው ዕለት በይፋ ስራ አስጀምሯል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በዚህ ወቅት፥ ከዚህ ቀደም የአንበጣ ወረርሽኝ፣ የደን ቃጠሎና የግሪሳ ወፍን መቆጣጠር የሚያስችል ሀገራዊ አቅም ባለመኖሩ በሰው ኃይል በባህላዊ መንገድ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል ብለዋል።
በሰሜን ተራሮችና በባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ቃጠሎ ባጋጠመ ጊዜ ኢትዮጵያ በልመና እና በኪራይ ከሌሎች አገራት የርጭት አውሮፕላኖችን በማምጣት ስትጠቀም መቆየቷን አውስተዋል።
አሁን ላይ መንግስት አደጋን በራስ የመቋቋምና ፈጣን ምላሽ የመስጠት አካል ያደረገውን የአምስት ኤር ትራክተሮች ( የርጭት አውሮፕላኖችን) ገዝቶ ወደ ስራ ማስገባቱንም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የኤር ትራክተር ባለቤት መሆኗ የጸረ አረምና ጸረ ተባይ የኬሚካል ርጭትን፣ የበረሃ አንበጣ መከላከልን፣ የስንዴና መሰል ሰብሎች የዋግ በሽታን ለመከላከል ትልቅ ሀገራዊ አቅም መሆኑን ገልጸዋል።
አውሮፕላኖቹ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙና ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የመስጠት አቅም ያላቸው በመሆናቸው እንደ እሳት ያሉ እና ሎሎች የተፈጥሮ አደጋዎች በፍጥነት ምላሽ መስጠት እንደሚያስችሉም አንስተዋል።
አውሮፕላኖቹ ከኢትዮጵያ ባለፈም ለጎረቤት ሀገርና ለሌሎችም ጥቅም መስጠት የሚችሉ ናቸው ብለዋል።
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ እውቀትና ቴክኖሎጂ የግብርና መር ስራን ለመተግበር በሂደት ላይ መሆኗን አንስተዋል።
ከ2011 ሰኔ ወር ጀምሮ የተከሰተው የበረሃ አንበጣ በስምንት ክልሎች 235 ወረዳዎችን ማዳረሱንና ሰፊ ጉዳት ማስከተሉን ጠቅሰው፥ የራሳችን የኬሚካል ርጭት አውሮፕላን ባለመኖሩ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራውም ሶስት ዓመት መውሰዱን ተናግረዋል።
በኪራይ ለመጡ አውሮፕላኖችና ለኬሚካል ርጭት 13 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉን አውስተው፥ አሁን ላይ በ850 ሚሊዮን ብር 5 ኤር ትራክተሮችን በመግዛት ሀገራዊ አቅም መፈጠሩን ገልጸዋል።
ይህም ተጋላጭነትን ለመቀነስ፣ አደጋ ሲፈጠርም ፈጣን ምላሽ ለመስጠትና ለሌሎች ተቋማትና ሀገራት እንድንደርስ የሚያስችል ነው ብለዋል።
ሀገር በቀሉ ናሽናል ኤርዌይስ ኤር ትራክተሮቹን የማስተዳደር ስራውን በጨረታ መረከቡን ጠቅሰዋል።
ከመደበኛ ስራቸው በተጓዳኝ ለሰፋፊ የንግድ እርሻ ልማት የኬሚካል ርጭት፣ ለእሳት አደጋና ሌሎችም ስራዎች በኪራይ ጥቅም ላይ ውለው ከፍተኛ ገቢ እንዲያስገኙ የሚያደርግ ስራ መጀመሩንም ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ለአብነትም ከኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽንና ከኦሮሚያ ምርጥ ዘር ድርጅት ጋር አውሮፕላኖቹን ለርጭት መጠቀም የሚያስችል ስምምነት ዛሬ ተፈርሟል።
ሰኔ 8 ቀን 2016 ዓም

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት‼️
እንኳን ለዒድ አል አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!
ኢድ አል አድሃ (አረፋ)በሙስሊም ማኅበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ክብር ያለው በዓል ነው። ዐቅሙና ሁኔታው የፈቀደላቸው ምዕመናን የሐጅ ሥነ ሥርዓትን በመፈጸም ያከብሩታል። ሌሎች ደግሞ በየሀገራቸው በጋራ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ በጸሎት፣ በመደጋገፍና በአብሮነት ያከብሩታል። በሀገራችንም ሙስሊሞች በዓሉን በጸሎት፣ ማዕድን በማጋራት እንዲሁም በደስታ በፍቅር ተጋግዘው ሲያሳልፉ እየያን አድገናል። አብረንም አክብረናል።
የዘንድሮ በዓል ሲከበር ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን በመጠየቅና በመደገፍ እንዲሁም ዐቅመ ደካሞችን በመንከባከብ እንደሚሆን አምናለሁ።
በዚሁ አጋጣሚ የሀገራችን ሙስሊም ማኅበረሰብ የመደጋገፍ ባህል ከተረጂነት ለመላቀቅ ለምናደርገው ትግል ወሳኝ ዕሴት ነው። እርስ በእርሳችን በመደጋገፍ በተረጂነት ከመታወቅ መውጣት አለብን። ለዚህ ደግሞ በበዓል ጊዜ የምናደርገውን መደጋገፍ የዘወትር ተግባር ማድረግ ነው።
እንደ ሀገር ላለፍንባቸው ችግሮቻችን መፍትሔ የሆነው የሽግግር ፍትሕ እና መፃዒ አብሮነታችንን ለማጎልበት ወሳኝ ለሆነው የሀገራዊ የምክክር ውጤታማነት ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የበኩሉን ሀገራዊ ኃላፊነት እንዲወጣ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ ማቅረብ እፈልጋለሁ። በድጋሚ እንኳን ለኢድ አል አድሃ (አረፋ)በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ፣ በዓሉ የሰላም የፍቅር የደስታ የአንድነት በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ሩሲያ ቭላዲቮስቶክ ገባ
******************
(ኢ ፕ ድ)
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ የልዑክ ቡድን ሩሲያ ቭላዲቮስቶክ ከተማ ገብቷል።
የልኡክ ቡድኑ በብሪክስ ሃገራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ዓለም አቀፍ ፎረም ላይ ይሳተፋል።
ከሰኔ 9 እስከ 12/2016 በሚካሔደውና ዎርልድ ማጆሪቲ ፎር መልቲፖላር ኦርደር በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ፎረም ላይ አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ በብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ፣ በብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ ዶክተር ሰማ ጥሩነህ ይሳተፋሉ።
የልኡክ ቡድኑ ከፎረሙ ጎን ለጎን የብሪክስ አባል ሃገራት ከሆኑ አቻ የፓርቲ አመራሮች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚካሔድም የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም

በአረፋ በዓል የሚታየው መደጋገፍ እንዲጎለብት ሕዝበ ሙስሊሙ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል
**************
(ኢ ፕ ድ)
የአረፋ በዓል መገለጫ የሆነው መደጋገፍና መረዳዳት እሴት እንዲጎለብት ሕዝበ ሙስሊሙ ሃይማኖታዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዚዳንቱ አማካሪና የውጭ ግንኙነት ኃላፊና የታሪክ ተመራማሪ አደም ካሚል ገለጹ።
አደም ካሚል የ1445ኛው የዒድ አልአደሃ(አረፋ) በዓልን አስመልክተው ለኢፕድ፤ የአረፋ በዓል የጋራ የሆኑ ማህበራዊ እሴቶች የሚበለጽጉበት፣ አብሮነት፣ መደጋገፍ፣ መረዳዳትና መተሳሰብ የሚጎለብቱበት በመሆኑ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከበር አቅመ ደካሞችንና ረዳት የሌላቸውን በማገዝ ሊሆን ይገባል።
እንደ አደም ካሚል ገለጻ፤ የዒድ አልአድሃ አረፋ በዓል በእምነቱ አስተምህሮ መሠረት ነብዩ ኢብራሂም የአሏህ ትዕዛዝን ለመፈጸም በፍጹም ትህትና እና ታዛዥነት ልጃቸው እስማኤልን ለመሥዋዕትነት ያቀረቡበት በዓል ነው። በዚህም በዓሉ ሲከበር ከራስ በላይ ለሌሎች በማሰብ ለመሥዋዕትነት ከቀረበው ለተቸገሩ ወገኖች ማካፈል......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130015

አውሮፕላኖቹ ከኢትዮጵያ አልፎ ለጎረቤት ሀገራት አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ናቸው
*****
(ኢ ፕ ድ)
የአሰሳና የርጭት አውሮፕላኖቹ ከኢትዮጵያ አልፎ ለጎረቤት ሀገራት አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ መሆናቸውን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ግብርናውን ለማዘመንና ምርትን ለማሳደግ በትኩረት እየሠራች ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የስንዴና ሌሎች ሰብሎች ላይ በአንበጣ፣በግሪሳ ወፍና በተምች እየተጠቃች ትገኛለች። እነዚህን ተባዮች ሙሉ ለሙሉ ማስቀረት የማይቻል ቢሆንም የመቀነስና ለመከላከል የሚያስችል አቅም መፍጠር አስፈላጊ ነዉ።
የርጭትና የአሰሳ አውሮፕላኖችን እየተከራዩ ለመከላከል ከመሞከር ይልቅ የራስ አቅም ማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በ850 ሚሊዮን ብር ወጪ አምስት አውሮፕላኖች.......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130019