የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት‼️
እንኳን ለዒድ አል አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!
ኢድ አል አድሃ (አረፋ)በሙስሊም ማኅበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ክብር ያለው በዓል ነው። ዐቅሙና ሁኔታው የፈቀደላቸው ምዕመናን የሐጅ ሥነ ሥርዓትን በመፈጸም ያከብሩታል። ሌሎች ደግሞ በየሀገራቸው በጋራ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ በጸሎት፣ በመደጋገፍና በአብሮነት ያከብሩታል። በሀገራችንም ሙስሊሞች በዓሉን በጸሎት፣ ማዕድን በማጋራት እንዲሁም በደስታ በፍቅር ተጋግዘው ሲያሳልፉ እየያን አድገናል። አብረንም አክብረናል።
የዘንድሮ በዓል ሲከበር ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን በመጠየቅና በመደገፍ እንዲሁም ዐቅመ ደካሞችን በመንከባከብ እንደሚሆን አምናለሁ።
በዚሁ አጋጣሚ የሀገራችን ሙስሊም ማኅበረሰብ የመደጋገፍ ባህል ከተረጂነት ለመላቀቅ ለምናደርገው ትግል ወሳኝ ዕሴት ነው። እርስ በእርሳችን በመደጋገፍ በተረጂነት ከመታወቅ መውጣት አለብን። ለዚህ ደግሞ በበዓል ጊዜ የምናደርገውን መደጋገፍ የዘወትር ተግባር ማድረግ ነው።
እንደ ሀገር ላለፍንባቸው ችግሮቻችን መፍትሔ የሆነው የሽግግር ፍትሕ እና መፃዒ አብሮነታችንን ለማጎልበት ወሳኝ ለሆነው የሀገራዊ የምክክር ውጤታማነት ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የበኩሉን ሀገራዊ ኃላፊነት እንዲወጣ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ ማቅረብ እፈልጋለሁ። በድጋሚ እንኳን ለኢድ አል አድሃ (አረፋ)በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ፣ በዓሉ የሰላም የፍቅር የደስታ የአንድነት በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
ሰኔ 8 ቀን 2016 ዓም

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ሩሲያ ቭላዲቮስቶክ ገባ
******************
(ኢ ፕ ድ)
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ የልዑክ ቡድን ሩሲያ ቭላዲቮስቶክ ከተማ ገብቷል።
የልኡክ ቡድኑ በብሪክስ ሃገራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ዓለም አቀፍ ፎረም ላይ ይሳተፋል።
ከሰኔ 9 እስከ 12/2016 በሚካሔደውና ዎርልድ ማጆሪቲ ፎር መልቲፖላር ኦርደር በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ፎረም ላይ አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ በብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ፣ በብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ ዶክተር ሰማ ጥሩነህ ይሳተፋሉ።
የልኡክ ቡድኑ ከፎረሙ ጎን ለጎን የብሪክስ አባል ሃገራት ከሆኑ አቻ የፓርቲ አመራሮች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚካሔድም የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም

በአረፋ በዓል የሚታየው መደጋገፍ እንዲጎለብት ሕዝበ ሙስሊሙ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል
**************
(ኢ ፕ ድ)
የአረፋ በዓል መገለጫ የሆነው መደጋገፍና መረዳዳት እሴት እንዲጎለብት ሕዝበ ሙስሊሙ ሃይማኖታዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዚዳንቱ አማካሪና የውጭ ግንኙነት ኃላፊና የታሪክ ተመራማሪ አደም ካሚል ገለጹ።
አደም ካሚል የ1445ኛው የዒድ አልአደሃ(አረፋ) በዓልን አስመልክተው ለኢፕድ፤ የአረፋ በዓል የጋራ የሆኑ ማህበራዊ እሴቶች የሚበለጽጉበት፣ አብሮነት፣ መደጋገፍ፣ መረዳዳትና መተሳሰብ የሚጎለብቱበት በመሆኑ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከበር አቅመ ደካሞችንና ረዳት የሌላቸውን በማገዝ ሊሆን ይገባል።
እንደ አደም ካሚል ገለጻ፤ የዒድ አልአድሃ አረፋ በዓል በእምነቱ አስተምህሮ መሠረት ነብዩ ኢብራሂም የአሏህ ትዕዛዝን ለመፈጸም በፍጹም ትህትና እና ታዛዥነት ልጃቸው እስማኤልን ለመሥዋዕትነት ያቀረቡበት በዓል ነው። በዚህም በዓሉ ሲከበር ከራስ በላይ ለሌሎች በማሰብ ለመሥዋዕትነት ከቀረበው ለተቸገሩ ወገኖች ማካፈል......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130015

አውሮፕላኖቹ ከኢትዮጵያ አልፎ ለጎረቤት ሀገራት አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ናቸው
*****
(ኢ ፕ ድ)
የአሰሳና የርጭት አውሮፕላኖቹ ከኢትዮጵያ አልፎ ለጎረቤት ሀገራት አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ መሆናቸውን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ግብርናውን ለማዘመንና ምርትን ለማሳደግ በትኩረት እየሠራች ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የስንዴና ሌሎች ሰብሎች ላይ በአንበጣ፣በግሪሳ ወፍና በተምች እየተጠቃች ትገኛለች። እነዚህን ተባዮች ሙሉ ለሙሉ ማስቀረት የማይቻል ቢሆንም የመቀነስና ለመከላከል የሚያስችል አቅም መፍጠር አስፈላጊ ነዉ።
የርጭትና የአሰሳ አውሮፕላኖችን እየተከራዩ ለመከላከል ከመሞከር ይልቅ የራስ አቅም ማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በ850 ሚሊዮን ብር ወጪ አምስት አውሮፕላኖች.......
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=130019